>
5:21 pm - Saturday July 20, 9050

የአብይ(ብልጽግና) ምስክሮች  ሃጫሉን በአንድ ወር ሶስት አራት ጊዜ ገደሉት!!! እረ ነፍሱ ትረፍበት!!!  ኤርሚያስ ሽበሺ

የአብይ(ብልጽግና) ምስክሮች  ሃጫሉን በአንድ ወር ሶስት አራት ጊዜ ገደሉት!!! እረ ነፍሱ ትረፍበት!!!
 ኤርሚያስ ሽበሺ


*…. ዳኛዋ:- በእኛ {በኢትዮጵያውያን} አቆጣጠር የመጀመሪያው ወር ምን ይባላል?
ምስክር :- ሰኔ …. 
በእስክንድር ላይ ምስክር እንዲሆኑ ያስለጠኗቸው እንዲህ ናቸው 
የባልደራስ  አመራሮችን የከሰዓት ችሎት በቦታ ተገኝቼ ለመታዘብ ችዬ ነበር፡፡ እስክንድር ላይ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ተብሎ የቀረበው ቀሽም ተዋናይ ኾኖ በመገኘቱ የብልፅግና ምስክሮች ጥሩ ተዋናዮች መኾን እንኳን የማይችሉ፣ አቃቤያኑም ማጣፊያቸው ያጠራቸው መሆናቸውን አስመስክረዋል፡፡ በዛሬው ችሎት የውሸቱን ክስ እውነት አድርጋ ማስመሰል የምትችለው፣ ምርጥ የዐቃቤ ሕግ ምስክር የምታዘጋጀው ሕወሓት በስንት ጣዕሟ ሲያስብል ውሏል፡፡
ምስክሩ በአቃቤ ሕግ የተዘጋጀውን ድርሰት በአንድ ትንፋሽ ፉት ካለ በኃላ የእስክንድር ጠበቆች እና ከምስክሩ ጋር ያደረጉት አውጫጭኝ የተወሰኑትን ጥያቄና መልሶች በዚህ መልኩ አሰናድቻለሁ፡፡ ስታነቡት ቀልድ ቢመስላችሁም እውነት መኾኑን አምናችሁ ነውና በደንብ አንብቡት፡፡
በቅድሚያ በምስጋና ልጀምር በዘመነ ሕወሓት የነበረው ዳኞች ገለልተኛ ሆነው ጉዳዮችን የመዳኘት ችግር በአሁኑ ችሎት በእጥፍ ተሻሽሎ አቃቤ ሕጎች ዳኛ የሚመስሉበት ታሪክ ሆኖ መቅረቱን በደንብ አይቻለሁ፡፡ እስከ ፍጻሜው እንዲህ ከኾነ በዳኞቹ ኩራት እንደሚሰማኝ ለአንባብያን አስቀድሜ አሳውቃለሁ፡፡
ጠበቃ፡- ስም?
ደረጀ ግዛው አቡሽ
ጠበቃ፡- ዕድሜ
35
ጠበቃ፡- አድራሻ?
 አ.አ ቂርቆስ ክ/ከ ወረዳ 01 ባምቢስ
ጠበቃ፡- የሚሰሩት ሥራ?
ግብርና
ጠበቃ፡- ግብርና የት ነው የሚሰሩት?
አዳማ
ጠበቃ፡- አቶ እስክንድር ምን ሲያደርጉ አዩት?
ሲኤምሲ ጀርባ ወሰን አካባቢ ‹‹መጤ መንግሥት እኛን አይመራንም!›› እያሉ አመጽ ሲቀሰቅሱ ነበር፡፡
ጠበቃ፡- መጤ የሚሉት ማንን ነው?
 ዐብይን
ጠበቃ፡- ሌላስ ምን አሉ?
እጁን ወደ ጎንና ጎን እያውለበለበ {ምስክር ቻው የሚለውን እንቅስቃሴ እያሳየ  } ግፉ፣ በርቱ! አለ
ጠበቃ፡- በጊዜው ምን ያህል ሰዎች ናቸው አመጽ ሲያነሳሱ የነበሩት?
በጣም ብዙ ናቸው
ጠበቃ፡- በግምት?
20 ወይም 30
ጠበቃ፡- ወጣቶቹ ምን አረጉ?
አንድ ኤፍ ኤስ አር መኪና እና ቪትስ መኪና አቃጠሉ፡፡ ሱቆችና ባንክ ሰባበሩ፡፡ እኔም ተከትያቸው የተወሰነ መንገድ ሄድኩ፡፡
ጠበቃ፡- ለምን ተከትለዋቸው ሄዱ?
እንደ እናንተ ዓይነት ጠንካራ፣ ጠንካራ ወጣቶችን ፈልጉ ብለውኝ ስለነበር የሚያደራጁኝ መስሎኝ ነው፡፡
ጠበቃ፡- ቢያደራጆት ኖሮ እርሶም አመጹን ይቀላቀሉ ነበር?
አልቀላቀልም፡፡ ቢያደራጁኝ ግን ሥራ እሰራለሁ ብዬ ነው፡፡
ጠበቃ፡- ሥራ አሎት አይደል፡፡ ያንን ሥራ ትተው እንዴት ሊደራጁ ፈለጉ?
ተጨማሪ ሥራ ካገኘሁ እሰራለሁ፡፡
ጠበቃ፡- እርሻውን ማን ይሰራሎታል?
ሠራተኞች አሉኝ እነሱ ይሰሩታል
ጠበቃ፡- እርሶ ገበሬ ከሆኑ ወቅቱ የእርሻ በመሆኑ ለምን ወደ እርሻዎት አልሄዱም?
በሃጫሉ ሞት ምክንያት መንገድ በመዘጋቱ ከሰኔ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ አልሄድኩም
ጠበቃ፡- ሃጫሉ እኮ ሰኔ 1 አልሞተም
እኔማ የመጣሁት ለሰኔ ሚካኤል ነው
ጠበቃ፡- ሰኔ 1 ብለው ነበር አሁን ደግሞ ለሰኔ ሚካኤል አሉ፡፡ እንደዛም ቢኾን ሃጫሉ በዛን ቀን አልተገደለም፡፡
ዝም ጭጭ
ጠበቃ፡- እስክንድር መች ነው አመጽ ሲያነሳሳ ያገኙት?
ሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ውስጥ
ጠበቃ፡- እስክንድር እርሶ ባሉት ቀንና ሰዓት እኮ ታስሯል፡፡
አቃቤ ሕግ ምላሽ እንዳይሰጡ በማድረግ ጉዳዩ በውስጥ ይጣራልኝ በማለቱ ዳኞቹ ቀኑን እናመሳክራለን ወደ ቀጣይ ጥያቄ ሂዱ ብለው አዘዋል፡፡
ጠበቃ፡- ከዚህ በፊት ፍርድ ቤት መጥተው ያውቃሉ?
አዎ!
ጠበቃ፡- ምን ሊያደርጉ?
እስክንድር ላይ ልመሰክር
ጠበቃ፡- በምን ጉዳይ? የት መሰከሩ?
በዚህ ጉዳይ እዚሁ ችሎት ላይ
ዳኛው፡- {ጣልቃ ገብተው} እንደ እኛ የተሰየሙ ዳኞች ባሉበት ወይስ በቢሮ ውስጥ ነው የመሰከሩት
ሶስት ወይም አራት ዳኞች ባሉበት ሰውም ባለበት እዚሁ ችሎት ውስጥ
ዳኛው፡- እንደ እኛ የህግ ጋወን ልብስ የለበሱ በተሰየሙ ዳኞች ፊት ነው?
ፈርጠም ብለው አዎ!
ጠበቃ፡- እስክንድርን አመጽ ሲያነሳሳ ካዩ በኃላ ወዴት ሄዱ?
ለልጄ ወተት ከተከራየንበት ቦታ ላመጣ
ጠበቃ፡- ስንት ሌትር
በየቀኑ የምናመጣው አንድ ሌትር ነው
ጠበቃ፡- ክፍያ የሚከፍሉት በቀን ወይስ በወር
በወር
ጠበቃ፡- በወር ስንት ይከፍላሉ?
3000 ብር {እንኳን ያኔ አሁን ራሱ አንድ ሌትር ወተት ቦሌ ላይ 48 ብር መኾኑን አንባቢ ይረዳው}
ጠበቃ፡- ዛሬ ቀን ስንት ነው?
16
ጠበቃ፡- ወሩስ?
መስቀል
ዳኛዋ፡- {ግራ ተጋብታ} ትምህርት እስከ ስንት ተምረዋል?
እስከ 8ኛ ክፍል
ዳኛዋ:-በእኛ {በኢትዮጵያውያን} አቆጣጠር የመጀመሪያው ወር ምን ይባላል?
ሰኔ
እንዲህ እየተባለ ችሎቱ እያሳፈረንም እያሳቀንም አመሸ፡፡
ሌሎች ያልጻፍኳቸውን የነበራችሁ አጋሩን፡፡
Filed in: Amharic