>

ኢትዮጵያ ሸብረክ ትል እንደሁ እንጂ አትንበረከክም!!!  [መስፍን ማሞ ተሰማ]

ኢትዮጵያ ሸብረክ ትል እንደሁ እንጂ አትንበረከክም!!!

መስፍን ማሞ ተሰማ

የናዚስት ትህነግ አቅምና የጤዛ ድሎች መሰረት ያለው ትግራይ ውስጥ ሳይሆን አዲስ አበባ፣ ባህር ዳር፣ ጎንደርና ደሴ ነው። ብልፅግና ውስጥ ኮት የገለበጠው የትግራይ ተወላጅ ነው የመቀሌ ጊዜያዊ  መንግሥት ተብሎ ትህነግን ከተንቤን ዋሻ ያወጣውና ዳግማዊ ነፍስ የሰጠው። ብልፅግና ውስጥ ያደባው የኦሮሞ ተወላጅ ኦነግ ነው የመቀሌው ነፍሰ ገዳዮች ፈረስ። የአማራ ተወለጅ የወያኔ የጡት ልጆች ብልፅግና ውስጥ አንገታቸውን የቀበሩ ብአዴናውያን ናቸው የአማራውን ልጅ አስፈጂዎች። ብልፅግና ሆይ ሳይመሽብህ በአስቸኳይ ራስህን አፅዳ!!!
ከአዲስ አበባ እስከ ጎንደር የዘለቀው በትግራይ ተወላጅነታቸው ከኢትዮጵያ ይልቅ “ትግራይ ታሸንፋለች” ብለው በወያኔ የዘር ፀበል የተጠመቁት “ተጋሩ” የተባሉ እስስቶች ናቸው በዚህ ጦርነት በቀዳሚነት የናዚስት ትህነግ የግፍና የበቀል ሰይፍ እጀታዎች።  ባንዳና የባንዳ ፍርፋሪ ለቃሚ ለኢትዮጵያ አዲስ አይደለም። በታሪክ ደጋግመው ተከስተዋል። መቅደላ ድረስ ጠላት መርተው የኢትዮጵያን ንጉሠ ነገሥትን እጅ ለማስያዝ በባንዳ አዝማችነት አገልግለዋል።
በሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያና የጣሊያን ወረራ ዘመን ኢትዮጵያ ዘረ ብዙ በሆኑ ባንዳዎች (በዋናነት ከትግራይ፣ ከአማራ፣ ከኦሮሞ) ለጣሊያን ባንዲራ አድረው ከጣሊያን ጎን ሆነው ኢትዮጵያን ወግተዋል። ነግር ግን ኢትዮጵያን ማንበርክ ወይ መበተን አልቻሉም። ጊዜያዊ ድላቸው በፀሀይ ግለት አንደሚጠፋው እንደ ጠዋት ጤዛ ሆኗል። ምክንያቱም ኢትዮጵያ ሸብረክ ትል እንደሁ እንጂ አትንበረከክምና! ምክንያቱም ኢትዮጵያ ትንገዳገድ ይሆናል እንጂ ከቶም የሚፈርስ ምሶሶ የላትምና!!! ምክንያቱም ኢትዮጵያ ለሉዓላዊነቷና ለክብሯ ደማቸውን የሚያፈሱላት አጥንታቸውን የሚገብሩላት ከጠላቶቿ በአእላፍ እጥፍ ወኔና ጀግንነት የእናትና የወገን ፍቅር ሰብዕና ያላቸው በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነታቸው የማይደራደሩ አናብስት ልጆች አሏትና!!!
ይህ ዘመን ከቀደምቱ የሚለየው የኢትዮጵያ መልክ ያለው ናዚስት ወፋሽስት ትህነግ የተባለው የምድር አሪዎስ የኢትዮጵያን አየር መበከሉ ነው። ባንዳዎቹ ደግሞ  (በዋናነት ከአማራውና ከኦሮሞው) ለትግራይ ናዚስት ወፋሽስት ያደሩ መሆናቸው ነው የዘመናችን እንቆቅልሽና የኢትዮጵያ ፈተና!! ፈተናን መቋቋምና ድል ማድረግ ደግሞ የኢትዮጵያ DNA ልዩ መታወቂያ አሻራዋ ነው።
ይህንን የዚህ ዘመን ፈተናዋና ኢትዮጵያ ድል ስታደርግ ድሏ በናዚስት ወፋሽስት ትህነግና አባሪ ባንዳዎች ላይ ብቻ ሳይሆን ከካርቱም እስከ ካይሮ እስከ ዋሽንግተን እስከ ብራሰልስ እስከ ለንደን እስከ ቪየና የተዘረጋውን የጠላቶቿን ሁሉ የዘመናት ሠንሠለት የሚበጣጥስ ይሆናል!!! ይህ በኢትዮጵያ የምናምን ኢትዮጵያውያን ሁሉ አልፋና ኦሜጋ ዕምነታችን ነው!!!
ይህ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ አልፋና ኦሜጋ ፅናታችን ነው!!!
ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!!! 
ድል ለኢትዮጵያ መከላከያና ሕዝባዊ ሠራዊት!!! 
የናዚስት ትህነግ ሞት ለኢትዮጵያ ትንሳኤ ሀውልት ነው!!!
Filed in: Amharic