>

አቢይ አህመድ ያባለጋቸዉ ኦነግ ሸኔዎች (ሸንቁጥ አየለ)

አቢይ አህመድ ያባለጋቸዉ ኦነግ ሸኔዎች
ሸንቁጥ አየለ

ያልገረፉት ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል እንዲል ዘይቤዉ አቢይ አህመድ ያባለጋቸዉ ኦነግ ሸኔዎች ዛሬ አቢይን ገልብጠዉ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከህዉሃት ጋር ግንባር ቢፈጥሩ አይገርምም።
ከሀጢያት ሁሉ የከፋዉ ሀጢያት እግዚአብሄር የሀገር መሪ ሲያደርገዉ ለሀገር መሪነት ተምኖ ፍትህን  መስራት ያለመቻል ወንጀል ነዉ።
አቢይ አይህመድ ኦነግ ሸኔ ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያዉያንን አንገት እንደ ጎመን ሲቀረድድ ብዙ ከተሞችን ሲያወድም እየተሳልቀ ያባለጋቸዉ ሸኔዎች ዛሬ አንገቱን ሊያንቁ ከወያኔ ጋር ዉል እና ግንባር መስርተዋል።
አቢይ ኦሮሞ ኦሮሞን ከሚገለዉ ብለን ኦነግ ሸኔ ወንጀል ሲሰራ ዝም አልነዉ ብሎ በንጹሃን ኢትዮጵያዉያን ደም ላይ ቀልዶ ቢያልፍም አቢይ ያባለጋቸዉ ኦነግ ሸኔዎች ግን ” አቢይ ኦሮሞ ስለሆነ ” ብለዉ አልማሩትም። ከህዉሃት ጋር ግንባር ፈጠሩበት እንጂ። የአቢይ መንግስት ፍትህ መስራት አያዉቅምና ዛሬም ከህዉሃት ጋር ከወገነዉ ኦነግ ሸኔ ጋር በጎን ይሞዳሞድ ይዟል። ያባለጉት ልጅ ሁል ጊዘእም መቋጫዉ አባቴን ልግደለል መንግስቱን ልዉረስ እንደሆነ የንጉስ ዳዊት ልጅ የአቤሜሌክ ታሪክ አንዱ ማሳያ ነዉ።
እናማ አቢይ አህመድ ለኢትዮጵያ ሲል ሳይሆን ለራሱ መንግስት ሲል በኦነግ ሸኔዎች ላይ መራራ እርምጃ ሲወስድ ወያኔን ነጥሎ መምታት ይችላል።አለዚያ የኦነግ ሸኔና ወያኔ ጥምረት አቢይ አህመድን ከዙፋኑ ጎትቶ እንዲያወርደዉ ይሆናል።
የሆኖ ሆኖ ግን የኢትዮጵያ ጉዳይ በመድሃኒአለም እጅ የተያዘ ነዉና የሚቋጨዉም በመድሃኒዓለም ትዛዝ ይሆናል። ወገኖቼ ምንም እንኳን ጸሀፊ ብሆንም በልብ እንዳኖረዉ እንጅ ዝርዝር እንድጽፍ አልታዘዝኩም እና የመድሃኒዓለምን የማዳን ሂደቱን በደምሳሳዉ አልፈዋለሁ።
Filed in: Amharic