>
5:26 pm - Sunday September 15, 8447

ብርሃነ ገብረክርቶስ....!!! (ከተስፋዬ ገብረአብ )

ብርሃነ ገብረክርቶስ….!!!

ከተስፋዬ ገብረአብ (የደራሲው ማስታወሻ )

ይህ አሁን መንግስት ልመስርት እያለ መከራውን የሚያየው የወያኔ አንባሳደር የሆነ ብርሃነ ገብረክርስቶስ በሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዝብ ከአለቃው መለስ ዜናዊ ጋር እንዴት አመድ እንዳረጉት ላስነብባችሁ።
ሶሎሜ ታደሰ የተባለችን በአንድ ወቅት የተጨበጨበላት የመንግስት ቃል አቀባይን፤ እዛው አሜሪካ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ውስጥ ሆኖ ስትሰራ የመለመላት ይህ ብርሃነ የተባለ ከይሲ ነው።
ሴቴቱ ደሞ ጎበዝ እና ወጣ ያለች ጭንቅ የማታቅ ነገር ናት መስል በብዙ ትታማ ጀመር። እንደውም ከአዜብ  ጋር ጥርስ ተነካክሰው ነበር ሁሉ ይላል፤ መርዘኛው ባለ ብዕር ተስፋዬ ገብረአብ።
ብርሃነ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ እየተመላለሰ ከሰሎሜ ጋር ያበዛ ነበር መሰል፤ የብርሃነ ህጋዊ ሚስት ከአሜሪካ ሆና ጫጫታ ታስነሳለች።
የስራ አጋራቸው ሰይጣን ደሞ ስራውን በደንብ ይሰራላቸዋል መሰል በትዳራቸው መሐል የግዴታውን ግብር በስኬት አጠናቀቀው። የብርሃነ ህጋዊ ሚስት በሶሎሜ ምክንያትና በሰይጣን ረዳትነት በአሜሪካ ፍርድ ቤት ከብርሃነ ጋር ያላትን ትዳር አፈርድሜ ታበላዋለች። ተፋቱ ማለት ነው።
የህውሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ብቻ የሚያቁት በተለይ መለስ እና ስብሃት ነጋ በዋነኝነት የሚቆጣጠሩትን ከትግሉ ጀምሮ በትግራይ ህዝብም ስም ጭምር የተሰበሰበ ሚሊዮን ዶላር አሜሪካ ወደሚገኝ የብርሃነ ገብረክርስቶስ የግል አካውንት ገቢ እየሆነ ይቀመጥ ነበር።
ዛሬ ህዝቢ ትግራይ እያሉ በጦርነት የሚማግዱትን ወጣት ያፈሩላቸውን ታጋይ፤ በስማቸው የሰበሰቡትን ገንዘብ ኢፈርት የተባለ የንግድ ተቋም አቋቋምንበት ብለው ዋሽተው ሲያበቁ ገንዘቡን በዚህ ብርሃነ ገብረክርስቶስ በተባለ ሰው ስም እያስቀምጡ ህዝባችን የሚሉትን ትግራዎይ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ወንድሙ ጋር በድህነት ዳዴ ያስኬዱት ነበር። እነ ብርሃነ ገብረክርስቶስ!
እናም የብርሃነ ገብረክርስቶስ ሚስት የነበረችው ሴት ይህን መጠኑ የሚታወቅ ገንዘብ (250 ሚሊዮን ዶላር) በፈታችው ባሏ ስም በክብር በአሜሪካ ባንክ ውስጥ እንደተቀመጠ ስለምታቅ ከፍችው መፀደቅ በኃላ በቀጥታ በትዳር ዘመኗ አብራ ያፈራችው ሀብት ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ድርሻውን እንዲሰጣት ጠየቀች።
ፍርድ ቤቱ ካሳ ጨምሮ ድርሻዋ እንዲከፈለት ቀጭን ትዕዛዝ አዘዘላት። ድርሻዋን ተቀበልች። እነ መለስ የሚይዙት የሚጨብጡት አጡ። ራሱ መለስ ዜናዊ ቢያናግራት ሊያግባባት ቢሞክር የኢትዮጵያን ህዝብ ብላ (እግርህን ብላ እንደሚባለው) ብላው ላሽ አለች።
እንግዲህ ይህ ብርሃነ የሚሉት ፈጣጣ ነው፤ ይህን የሚያክል ገንዘብ ከደሃ ህዝብና ታጋይ በልቶ እና አስበልቶ  ዛሬ ለኢትዮጵያ መንግስት ምስረታ መከራውን የሚያየው።
እናም በአጭሩ እንዲህ ያለ ሌባ ነው በኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት እያለ መከራውን የሚያየው። በርግጥ ሌላ የሚሰረቅ ካለ ምን ገዶት!
Filed in: Amharic