>
5:16 pm - Sunday May 24, 4848

እኛ ኢትዮጵያኖች እኮ ገራሚ ነን....?!? (ሸንቁጥ አየለ)

እኛ ኢትዮጵያኖች እኮ ገራሚ ነን….?!?

ሸንቁጥ አየለ
 
ፕሮፌሰር ይስሃቅ ዋና ጸረ ኢትዮጵያዊ የወያኔ እና የጸረ ኢትዮጵያዉያን የዉጭ ሀይሎች  ጥምር ሰላይ መሆኑን ኢንጅነር ሀይሉ ሻዉልን ጨምሮ ብዙ ሀይሎች አስረድተው ነበር።ግን ማን ይሰማሃል???
ከበሮ ድለቃ የተሰማበት ቦታ ሁሉ ገብቶ የሚጨፍረዉ ልሂቅ ኢትዮጵያዊ ከቶም ሀገራዊ ጠላትና ወዳጅ የሚባል ወገንን የሚለይበት መርህ የለዉም።ለሃገራቸዉ ብዙ የደከሙትን እና ለኢትዮጵያ መስዋዕት የሆኑትን ከማክበር ይልቅ እንደ ተራራ አሳክሎ ሲክብ የሚዉለዉ በተቀናበረ ፕሮፖጋንዳ ጠላት የሚያቀርበለትን ጸረ ኢትዮጵያዉያንን ነዉ።
ይሄም ከህዝቡ እስከ መሪዉ የሚታይ እጸጽ ነዉ። መንግስቱ ሀይለማሪያም 60ዎቹን የሀገር እንቁዎች እንዲሁም በርካታ ኢትዮጵያዉያን የሀገር ሀብት ምሁራንን በኢሃፓነት በመሳፍንትነት ጥርግ አድርጎ በወያኔ በኦነግ እና በሻቢያ አቀናባሪነት ከገደለ ብኋላ ከብዙ አመታት ጥፋት ብኋላ ተጸጸተ ተብሎ ተጽፎለት ያያሁ ቀን ፈገግ ብያለሁ።
መንጌ “ቆራጡ” በቆራጣ ህሳቤዉ አንድ ትዉልድ ከጨፈጨፈ ብኋላ ” እዉነተኞቹን ኢትዮጵያዉያንን በጸረ ኢትዮጵያዉያን የተንኮል ጉንጉን አጠፋናቸዉ። መረሸን የነበረባቸዉን አጠገባችን አድርገን እዉነተኞቹን ረሸንናቸዉ” ሲል ተናዘዘ አሉ።
ህዝቡም እንዲሁ አይነት ባህሪ አለዉ። በሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ ተሽሞንሙነዉ የሚቀርቡለትን እንጂ እዉነተኛ እንቁዎችን ከቶ አያስተዉልም። ወይም ደግሞ ጥቂት ጉድፍ እየቀባባ የራሱን እንቁ ቀብሮ ባንዳን እንደ አተላ በትከሻዉ  ተሸክሞ መኖርን ይመርጣል።
ይስሃቅ ባንዳ መሆኑን ግን ጥቂቶች ቅንጅትን እንዴት እንዳፈረሰዉ ሳይቀር እያጣቀሱ. ለብዙ ጊዜ ሲገልጹ ነበር።ህዝቤ ግን እዉነትን ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ይስሃቅን ያገር አድባር አድርጎ ሲሸልል ከርሞ ድንገት ዛሬ የይስሃቅ ነገር የተገለጠለት ይመስላል። ሆኖም ያዉ በድንግዝግዝ ይመስላል ነዉ።
ርኩስ ኢሌኒ  vs የአማራ ህዝብ እና ቅድስት ኢትዮጵያን
እሌኒ የተባለች ሴት ላለፉት 30 አመታት በብዙ ሚሊዮን አማሮች ሲጨፈጨፉና ሲፈናቀሉ አስተዉላለች። ሴትዮዋ ተመራማሪ እንደመሆኗ መጠን መረጃዉ አላት። በተለይም ላለፉት አራት አመታት በነገደ አማራ ላይ  በወለጋ በመተከል በልዩ ልዩ የደቡብ እና ኦሮሚያ አካባቢዎች በአማራ ነገድ ላይ የተሰራዉ የዘር ማጥፋትን ተከታትላለች።
አማራ ስጋዉ እስኪበላ በግሬደር በገፍ እንደ ቆሻሻ ተገፍቶ እስኪቀበር ያለዉን ሂደት ሰምታለች አይታለች። ይሄ ሁሉ ሲከናወን እንደ ኦነጋዉያን፡ እንደ ኦህዴዳዉያን ፡ እንደ ህዉሃታዉያን ሁሉ በደስታ እየተፍነከነከች በፍንጭት ጥርሷ የማይነገር ስዉር ፈገግታዋን እየረጨች ትደሰት ነበር። ይሄ ሁሉ ግፍ ሲሰራ አንድም ቀን ይሄን ግፍ ተቃዉማ አታዉቅም ነበር። ምን በወጣት። አማራማ ይለቅ።
ከሸዋ አማሮች ከሸዋ ኦሮሞዎች ከትግራዮች ትዉልድ ያለኝ ዉህድ ኢትዮጵያዊ ነኝ ፡ ከዘረኝነት ነጻ ነኝ ያለችዉ እሌነ አማራ በዘሩ ምክንያት ሲያልቅ በደስታ ትፍነከነክ እንደነበረ ሰሞኑን የተናገረችዉ ንግግር ምስክር ነዉ። እሌኔ የህዉሃትን ቆሻሻ ካንሰር ብሄረተኝነት ተሸክማ ስታበቃ የአማራን ህዝብ ” አማራ ጽንፈኛ ብሄረተኛ” ሆኗል ብላ በአማራ ጠላቶች ፊት ከሰሰችዉ።
እያለቀ ያለዉ የአማራ ህዝብ ግን እንኳን ጽንፈኛ ብሄረተኛ ሊሆን የብሄረተኝነት ሃሁ ገና አልጀመረም። አማራ በዚህ ሁሉ የሞት ጎዞ ዉስጥ የኢትዮጵያን ቅድስና ሙጭኝ እንዳለ ነዉ። ርኩስ ኢሌኒ ግን ቅድስት ኢትዮጵያን ገና አላወቀቻትም።
 እሌኔ በጽንፈኛ ብሄረተኝነት እንዴት የአማራን ህዝብ ልትከሰዉ ቻለች? ለሚለዉ ጥያቄ መልሱ ግን የሴትዮዋ የስነ ልቦና አወቃቀር በፍጹም ጸረ አማራ መሰረት ላይ የቆመ ስለሆነ ነዉ።እንጅማ ከዚህ ለዚህ ህዝብ መቆም ሲገባት ይሄን ህዝብ በማኒፌስቶ፡ በህገ መንግስት እና በፖለቲካ ፕሮግራም በተግባራዊ ደረጃ ካጠፋዉና ካስጠፋዉ ወገን ጋር ወግና ኢትዮጵያን ሙጥኝ ያለዉን አማራን በጽንፈኛ ብሄረተኝነት አትከሰዉም ነበር።
እሌኒ ገ/መድህን የአማራን ህዝብ በጽንፈኛ ብሄረተኝነት እንዴት  ልትከሰዉ ቻለች? 
እሌኒ የተባለች ሴት ላለፉት 30 አመታት በብዙ ሚሊዮን አማሮች ሲጨፈጨፉና ሲፈናቀሉ አስተዉላለች። ሴትዮዋ ተመራማሪ እንደመሆኗ መጠን መረጃዉ አላት። በተለይም ላለፉት አራት አመታት በነገደ አማራ ላይ  በወለጋ በመተከል በልዩ ልዩ የደቡብ እና ኦሮሚያ አካባቢዎች በአማራ ነገድ ላይ የተሰራዉ የዘር ማጥፋትን ተከታትላለች።
አማራ ስጋዉ እስኪበላ በግሬደር በገፍ እንደ ቆሻሻ ተገፍቶ እስኪቀበር ያለዉን ሂደት ሰምታለች አይታለች። ይሄ ሁሉ ሲከናወን እንደ ኦነጋዉያን፡ እንደ ኦህዴዳዉያን ፡ እንደ ህዉሃታዉያን ሁሉ በደስታ እየተፍነከነከች በፍንጭት ጥርሷ የማይነገር ስዉር ፈገግታዋን እየረጨች ትደሰት ነበር። ይሄ ሁሉ ግፍ ሲሰራ አንድም ቀን ይሄን ግፍ ተቃዉማ አታዉቅም ነበር። ምን በወጣት። አማራማ ይለቅ።
ከሸዋ አማሮች ከሸዋ ኦሮሞዎች ከትግራዮች ትዉልድ ያለኝ ዉህድ ኢትዮጵያዊ ነኝ ፡ ከዘረኝነት ነጻ ነኝ ያለችዉ እሌነ አማራ በዘሩ ምክንያት ሲያልቅ በደስታ ትፍነከነክ እንደነበረ ሰሞኑን የተናገረችዉ ንግግር ምስክር ነዉ። እሌኔ የህዉሃትን ቆሻሻ ካንሰር ብሄረተኝነት ተሸክማ ስታበቃ የአማራን ህዝብ ” አማራ ጽንፈኛ ብሄረተኛ” ሆኗል ብላ በአማራ ጠላቶች ፊት ከሰሰችዉ።
እያለቀ ያለዉ የአማራ ህዝብ ግን እንኳን ጽንፈኛ ብሄረተኛ ሊሆን የብሄረተኝነት ሃሁ ገና አልጀመረም። አማራ በዚህ ሁሉ የሞት ጎዞ ዉስጥ የኢትዮጵያን ቅድስና ሙጭኝ እንዳለ ነዉ። ርኩስ ኢሌኒ ግን ቅድስት ኢትዮጵያን ገና አላወቀቻትም።
 እሌኔ በጽንፈኛ ብሄረተኝነት እንዴት የአማራን ህዝብ ልትከሰዉ ቻለች? ለሚለዉ ጥያቄ መልሱ ግን የሴትዮዋ የስነ ልቦና አወቃቀር በፍጹም ጸረ አማራ መሰረት ላይ የቆመ ስለሆነ ነዉ።
እንጅማ ከዚህ ለዚህ ህዝብ መቆም ሲገባት ይሄን ህዝብ በማኒፌስቶ፡ በህገ መንግስት እና በፖለቲካ ፕሮግራም በተግባራዊ ደረጃ ካጠፋዉና ካስጠፋዉ ወያኔ ጋር ወግና ኢትዮጵያን ሙጥኝ ያለዉን አማራን በጽንፈኛ ብሄረተኝነት አትከሰዉም ነበር።
Filed in: Amharic