>

"የሽግግር ሥልጣን ናፋቂዎች ወደ ቀልባችሁ ተመለሱ...!!!(ያሬድ ሀይለማርያም)

“የሽግግር ሥልጣን ናፋቂዎች ወደ ቀልባችሁ ተመለሱ…!!!”
ያሬድ ሀይለማርያም

ጊዜው ኢትዮጵያን ከመበታተን አደጋ የመታደጊያ እንጂ ስለ ‘ሽግግር መንግስት’ ምስረታ የሚወራበት አይደለም። የኢትዮጵያ ችግር ከሽግግር ምስረታ በላይ ነው።  አገርን የማቆየት ፈተና ውስጥ ገብተናል። ኢትዮጵያ ዙሪያዋን በእሳት ተከባ እየተለበለበች ባለበት በዚህ አስጨናቂ ወቅት ፖለቲከኞቻችን ከየት ወዴት ልትሸጋገሩን ነው ይህን የጨነገፈ ሃሳብ ይዛችሁ በዚህ ፈታኝ ወቅት ብቅ ያላችሁት? ኤርትራን የሸኘንበት የ83ቱ ሽግግር ለኢትዮጵያ ምን ፈየደ ብላችሁ ጠይቁ እንጂ። ገሚሶቻችሁ ያኔም የሽግግሩ ድራማ ተዋናይ ነበራችሁ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ጭንቀት አገራችንን እንዴት ከውጭ ጫና እና ከእኩይ ፓለቲከኞቿ ታድገን ነጻ እናውጣት ነው እንጅ ማን በትረ-ሥልጣኑን ይያዘው አይደለም። የሽግግር ሥልጣን ናፋቂዎች ወደ ቀልባችሁ ተመለሱና ኢትዮጵያ እንደ ሀገር እንድትጸና እና ሰላሟ እንዲመለስ ድርሻችን ምን ይሁን ብላችሁ እራሳችሁን ጠይቁ። ከሥልጣን በፊት ሕዝብና አገር ይቅደሙ!

Filed in: Amharic