>

መርዛማ ‹‹ዐራሙቻዎች›› (ከይኄይስ እውነቱ)

መርዛማ ‹‹ዐራሙቻዎች››

ከይኄይስ እውነቱ


ቅዱሳን በኪደተ እግራቸው በቀደሷት ኢትዮጵያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታት መርዛማ አራሙቻዎች በቅለውባት በአሁኑ ጊዜ መላ አካሏን ተብትበው ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ላይ ትገኛለች፡፡ በዚህ ጽሑፍ መርዛማ አራሙቻዎች የተባሉት ባጠቃላይ የጐሣ ፖለቲካ አራማጆች ሲሆኑ በዋናነት ግን የሻእቢያ አዋልድ የሆኑት ወያኔ ትግሬ እና ኦነግ፤ የወያኔ አዋልድ የሆኑት ብአዴን፣ የዐቢይ ኦሕዴድና ዛሬ ላይ እየተበታተነ ያለው ደኢሕዴድ እና የነዚህ አባሪ ተባባሪ የሆኑት ‹አጋር› ተብዬዎች ናቸው፡፡ አሁን ላይ ኦነግና ኦሕዴድ÷ ወያኔ ትግሬና ብአዴን አንድ አካል አንድ አምሳል ናቸው፡፡ እነዚህ አራሙቻዎች ባንድነት የጋራ ጠላት አላቸው፡፡ የአማራ ሕዝብ በተለይ፣ ኢትዮጵያ ባጠቃላይ፡፡ ከሥልጣን በስተቀር በሚከተሉት ‹ርእዮት›፣ የጐሣ ፖለቲካ እና መዋቅር፣ ተሠርታ ያደረችን አገር ለማጥፋት ወያኔ ደደቢት ላይ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በጻፈው የ‹ዕዳ ደብዳቤ› (የጐሠኞቹ መተዳሪያ ሰነድ)፣ ንጹሐንን በጭካኔና በግፍ በመግደል፣ የሕግ የበላይነትና ተጠያቂነትን ከኢትዮጵያ ምድር በማጥፋት፣ ብሔራዊ ታሪክን÷ባህልን እና ቅርስን በማጥፋት፣ ብሔራዊ ጥቅምን ለባዕዳን አሳልፎ በመስጠት፣ በንቅዘትና በዝርፊያ፣ ሐሰትንና ቅጥፈትን በማንገሥ፣ አገርንና ሕዝብን በማዋረድ፣ እነዚህንም ነውሮች ተቋማዊ በማድረግ ወዘተ. ልዩነት የላቸውም፡፡ በዓለም አቀፍ ግንኙነትም ረገድ ድንቊርና የጋራ ገንዘባቸው ሆኖ ሥልጣን ላይ ለመቈየት ከሚያደርጉት ማጭበርበሪያ ስልት በስተቀር ልዩነት የላቸውም፡፡ በየትኛውም መመዘኛ ከመካከላቸው አገር ወዳድ አርበኛ የለበትም፡፡ የባንዶችና ከሀዲዎች ስብስቦች ናቸው፡፡ በነገራችን ላይ አድር ባዮችን (ግለሰብም ሆኑ ድርጅቶች) ዘንግቼአቸው አይደለም፡፡ በየዘመናቱና በየሥርዓቱ ኢትዮጵያን ተጣብተዋት የሚኖሩ ያልሻሩ ‹ኮሶዎች› ያልበረሱ ‹መርዞች› ናቸው፡፡ 

ስለሆነም ኢትዮጵያንና ሕዝቧን እታደጋለሁ የሚል ኢትዮጵያዊ ሁሉ የቅደም ተከተል ጉዳይ ካልሆነ በቀር እነዚህ ዐራሙቻዎች የኢትዮጵያ ጠላቶች መሆናቸውን በሚገባ መረዳት ይኖርበታል፡፡ በተለይም በሁሉም አቅጣጫ እልቂት የታወጀበት የአማራው ሕዝብ የዐራሙቻዎቹ ፊታውራሪ የሆነውን ወያኔን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ከፈለገ ሰሚ ባላገኝም ከዓመታት በፊት እንደጮኹት ብአዴን የሚባለውን የወያኔ ድርጅት – የዐራሙቻዎች ሁሉ – ዐረም ከሥሩ መንቀል አለበት፡፡ በድርጅቱ ሥር የተሰባሰቡትን ታኅተ ሰብእ አካይስቶችን መሪ ጀሌ ሳይል ጠራረርጎ ማጥፋት ይኖርበታል፡፡ ‹‹ለእገሌ ስስ ልብ አለኝ›› የሚለውን ፌዝና ኢሕአዴጋዊ እርሾ የሚሰማ ጆሮ የለንም፡፡ የአገሬ የወንዜ ልጅ ነው በሚል አውራጃና ወረዳ÷ ጎጥና ቀበሌ÷ መንደርና ቤተዘመድ የሚቈጥር ካለ ለወያኔ ያደረ ሕዝቡን/ወገኑን ለማስጨረስ የቈረጠ ከሀዲ ቅጥረኛ ነው፡፡ ብአዴን  በአማራ ሕዝብ ጥላቻ ላይ የተመሠረተ አማራን ማጥፊያ የወያኔ ጨንገር ነው፡፡ ከዚህ በላይ ስለ ብአዴን ማንነት በእንክብል ወይም በመርፌ መልክ ይሰጠን ካላለ በስተቀር ሰሚ ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ!!! የደነቈረም ወገኑን እንደሚያስጨርስ ይወቀው፡፡

በመጨረሻም ጊዜ ሰጥቶት የአራሙቻዎቹ ቊንጮ የሆነው ዐቢይ የሚባል ዘረኛ ‹የቀይ ጥቁር› በኢትዮጵያውያን በተለይም በንጹሐን የአማሮች ደም (በሕፃናት፣ እናቶችና አዛውንት ደም) የተጨማለቀ መላ ሰውነቱ በየትኛውም በጎ ሥራ (ምናልባት የሥልጣኑ ጉዳይ አስግቶት መልካም ሊሠራ ቢያስብ እንኳን) ሊጠራ አይችልም፡፡ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር ይህ መሠሪ ዕድል ፈንታው ዕጣ ተርታው ከኢትዮጵያ ከተቈረጠ ከረመ፡፡ እሱም ያሳዳጊዎቹን ዋጋ/ፍርድ መቀበሉ የማይቀር ነው፡፡ 

አምላከ ኢትዮጵያ አጽራረ ኢትዮጵያን ሁሉ ያጥፋልን፡፡ በዓለም ማዕዝናት የምትገኙ አዋልደ ኢትዮጵያ በሙሉ ጸልዩ በእንተ ሰላማ ለብሔረ ኢትዮጵያ፡፡

Filed in: Amharic