>

አርበኛ ዘመነ ካሴ መልዕክት -  ለሚመለከተው ሁሉ ....!!! (ወንድወሰን ተክሉ)

አርበኛ ዘመነ ካሴ መልዕክት –  ለሚመለከተው ሁሉ ….!!!
ወንድወሰን ተክሉ


* …የቁስ ሰቀቀናችን ለማርካት ወሎ አልዘመትንም፤ ለጠላት ሰቀቀን ልንሆን እንጅ…!!!”
አርበኛ ዘመነ ካሴ 
 
የኛ ሰቀቀን የአማራ ህዝብ ነጻነት የኢትዮጲያውያን እኩልነት ነው።ደግሞም አድርገነዋል።የመርከብ ተራራ ሰንሰለቶች ይናገሩ ፥የአቃስታ ፥ጊምባና ቱሉ አውሊያ አድባራት ይመስክሩ ጠላትን አናቱን ቀጥቅጠን ሙትና  ቁስለኛውን በሲኖ ትራክ አስጭነነዋል። …………………
ሁለት ሳምንት ወሎ ግንባር ቆይቻለሁ፥አንድ ቢጫ ጀሪካን ከጋራጅ ተውሼ በግማሽ ሰአት ውስጥ ከምስጋና ጋር መመለሴን አስታውሳለሁ።ሰባራ መርፌ እንኳን አልነካንም።ለምንወደው ስልጡን ህዝብ መከታ ልንሆን ዘምተናል፥ጠላቱንም አይኑ እያዬ ተበቅለንለታል፥ከፍ ያለ ኩራትም ይሰማናል።ታዲያ ጸረ ኢትዮጲያ፥ጸረ አማራና ጸረ ጎጃም ሃይሎች ባንድ ላይ ምን ያስጮሃቸዋል ከተባለ መልሱ ሌላ ነው።
ወሎ አማራ መሬት ላይ በተአምር ማር ብናዘንብ እንኳን እነዚህ ሃይሎች አሲድ አዘነቡ እንደሚሉን ቀድመን እናውቅ ስለነበር ጫጫታቸው አላስገረመንም።ይልቁንስ ጠላት ሲጮህ ስራችን በሚገባ እየከወንን መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል፥ጮክ ብሎ ይነግረናል።በተረፈ  ሰባራ ቅል  እንኳን በጉያው ደብቆ መርጡለማርያም የደረሰ  አንድ እንኳን አባል ቢገኝ እጣው መራራ ነው የሚሆነው።
ትግላችን ይቀጥላል!!ከፋፋይነትና ሴረኛነት ጉሮሮው ይታነቃል ።እና መሰሪ ሃይሎች ሆይ ህዝቡን ተውት አይደናገር፥እኛ እንደሁ እንኳን በውሻ ጩኸት በአንበሳ ግሳትም አንደነብር።
ድል ለአማራ ህዝብ!!!
ድል ለኢትዮጲያ ህዝብ!!!
/አዲስ ትውልድ፥አዲስ አስተሳሰብ፥አዲስ ተስፋ/
 
Filed in: Amharic