>
5:13 pm - Wednesday April 18, 7962

በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ አመት መሉ ተቀምጦ የማይሰለቸው ተ.መ.ድ ነገም ስብሰባ ይቀመጣል (ሱሌማን አብደላ)

በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ አመት መሉ ተቀምጦ የማይሰለቸው ተ.መ.ድ ነገም ስብሰባ ይቀመጣል
ሱሌማን አብደላ

ይሄ ድርጅት ግርም ነው የሚለው። አለም ነቅቶ ሙድ እየያዘባቸው እንኳን ከነቃችሁ ይቅር አይልም። ዘላለም ለአሜሪካ እንደሰራ መጨረሻው በአፍሪካዊያን እና በኤሽያ አገሮች መቀበር ነው። አፍሪካ በተመድ የራሷ መቀመጫ ያስፈልጋታል። ኤሺያም እንደዛው። ማን ቀረ ?.ያው እነ G7 ሆኑ። የመጨረሻ እድሉ ራሱን ማትነን ነው። በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ አመት መሉ ተቀምጦ የማይሰለቸው ጉተሬስ የሚባል የአሜሪካ አስፈፃሚ ነገም የአውሮፓ ህብረትን ጥሪ ተቀብሎ ስብሰባ ይቀመጣል። ከሁሉም ከሁሉም ግን ይሄ ተቋም እንደዚህ ሰውየ አሳፋሪ ሰው መርቶት አያቅም። ትንሽ እንኳን የራሱ የሚለው አቋም የለም።
ሁለተኛው መልዕክት ተለቋል። ሊንኩን ከፍታችሁ በ Retweet እና Quote tweet አብራችሁ ዝመቱ።https://t.co/VLLrI1gwt7
“አውሮፓ ሕብረትና ግብፅ….!!!”
አውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ላይ የመጨረሻ ያለውን ዘመቻ ጀምሯል። ተመድን አስገድዶ ስብሰባ ጠርቶታል። በዚህ ስብሰባ ላይ አፍሪካዊያን አገሮች የሉም። ጥያቄው የቀረበው ግን ከግብፅ ነው። ግብፅ የአረብ ሊግን ተጠቅማ ጥያቄውን የአውሮፓ ህብረት ወዳጆቿ አቅርባለች።
ይህ ሚስጥራዊ ውይይት ከመፈፀሙ በፊት ወያኔ ለሁሉም አገሮች የአዱኑኝ ደብዳቤ ፅፏል። መፃፉን አልጀዚራ ዘግቦት ሁላችሁትም አንብባችሁታል። ይህ ስብሰባ የተጠራው የፊልትማን ጉዞ ውጤት እንደሌለው ከታወቀ ቡሀላ ነው።
በቱርክና ኤምሬትስ ላይ ሊሰራ የነበረው ቁማር ውጤ የለለው ሆኗል። ጀፍሪ ፊልተማን ጉዞ ሊጀምርነው ተብሎ ከተነገረ ቡኋላ መዳረሻ የለለው ጉዞ ውስጥ መግባቱን On day on ዘግቧል። የአውሮፓ ህብረት ለተመድ አባል አገራት የሰበአዊ ስብሰባ እንዲጠራ የተረገውም ይሄንን ሴራ ለማስፈጸም ነው። ይስማማሉ አይስማሙም ጊዜ የሚፈታው ጥያቄ ነው።
ዋናው ጉዳይ ግን ግብፅ ናት። ግብፅ የምትይዘው የምትጨብጠው አጥታለች። አለም ያልተረዳት ጭንቀት ውስጥ ገብታለች። ይወድቃል የተባለው የአብይ አሕመድ መንግስት አሎደቀም። ትፈርሳለች የተባለችው ኢትዮጵያን አንድነቷን እያጠናከረች መቀጠል ይዛለች። ሁሉም ነገራቸው የተበላሸባቸው የምዕራባውያን እና የግብፅ ህልም አዲስ ትግል ጀምረዋል። ግብፅ ቻይና መንግስትና የኢትዮጵያ መንግስት ያላቸው ግንኙነት ያሰጋኛል ስትል ባደባባይ ተናግራለች።
ይሄም ብቻ ሳይሆን የግብፅ መንግስት ቻይና ባለው የግብፅ አምባሳደር ለቻይና መንግስት ደብዳቤ አስገብቷል። ከቻይና በመቀጠል ለሩሲያና ለህንድ ለደቡብ አፍሪካ መንግስት ደብዳቤ ገብቷል። ደብዳቤው ሚስጥራዊ ቢሆን ከሚዲያ ግን አራቀም። on day on መረጃውን አገኙሁት ብሎ በፊትለፊት ገፁ ለብዶታል። እንደ on day on ዘገባ ከሆነ የግብፁ መንግስት ለሮማው የካቶሊክ ጻጻስ ሳይቀር ደብዳቤ ልኳል። ይህ በግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የተላከ ደብዳቤ ነው። ሌሎች ሚዲያዎች ግን ህወሓት በዲያስፖራው በኩል ነው ለጻጻሱ አዱኑኝ ስልት የተማፀነችው ሲሉ ቢዘግቡም ነገሩ ግን እንደዛ አይደለም። የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የፃችውን ደብዳቤ በመልዕክተኛ ነው ለሮማው ጳጳስ ህወሓት የሚድንበትን መንገድ ፈልጉ የሚል ደብዳቤ የላከችው።
የነዚህ ሰዎች ነገር ይገርማል። ጦርነቱ እያለቀ ሲመጣ ወያኔ ከሞተ ሁሉም ነገር ተቀየረ በተለይ የምስራቅ አፍሪካና የአሜሪካ የአውሮፓ ግንኙነት እንዳጨለመ ቆጥረው በኛ ላይ ያለ የለለ ሀይላቸውን ለመጠቀም እየጣሩ ነው።
Filed in: Amharic