>

በእነ እስክንድር ችሎት ፖሊስ አጣሁት ያለውን ምስክር በ44 ሠዓት ውስጥ  ይዞ  እንዲያቀርብ ታዘዘ....!!! (አሌክስ ሸገር)

በእነ እስክንድር ችሎት ፖሊስ አጣሁት ያለውን ምስክር በ44 ሠዓት ውስጥ  ይዞ  እንዲያቀርብ ታዘዘ….!!!
አሌክስ ሸገር

*…. እስክንድር ላይ ተገዝቶ በሃሠት ለመመስከር የሞከረው ነብሠ በላው እና አደገኛው ወንጀለኛ ይባስ  እጁን ታስሮ በፖሊሶች ታጅቦ ጭራሽ  እዛው ግቢ ውስጥ  ተከሶ ችሎት ሊቀርብ ሲገባ በአይኔ በብረቱ አየሁትና የእስክንድር አምላክ ምን አይነት ፈጣን ፈራጅ እንደሆነ አይቼ ተደነኩ!
ዛሬ ጠዋት ፍርድ ቤት ተገኝቼ እንደተለመደው  አላግባብ በግፍ የታሠሩትን የነ እስክንድርን ችሎት ተከታትዬአለው አቃቤ መንግስት ከዚህ ሁሉ ረጅም ቀጠሮ በኃላም ዛሬም እንደልማዱ ምስክሮቹን ማቅረብ አልቻለም እንዲያውም በቀደም በስንት መከራ ፍ/ቤት ቀርቦ የነበረውን  ጌትነት የተባለውን የሃሠት ምስክር ትቼዋለው አይመስክር ይቅርብኝ ብሉአል ፖሊስም በበኩሉ ከዚህ በፊት ይዘህ አቅርብ የተባለውን ምስክር በአድራሻቸው ላገኛቸው አልቻልኩም ያለ ሲሆን ፍርድ ቤቱም በበ44 ሠዓት ውስጥ  ተይዞ አርብ እንዲቀርብ በጥብቅ አዞ ወተናል።
ሌላው ደግሞ ከችሎት ስንወጣ እስክንድር ላይ ተገዝቶ በሃሠት ለመመስከር የሞከረው ነብሠ በላው እና አደገኛው ወንጀለኛ ይባስ  እጁን ታስሮ በፖሊሶች ታጅቦ ጭራሽ  እዛው ግቢ ውስጥ  ተከሶ ችሎት ሊቀርብ ሲገባ በአይኔ በብረቱ አየሁትና የእስክንድር አምላክ ምን አይነት ፈጣን ፈራጅ እንደሆነ አይቼ ተደነኩ!
ፈጣሪ ዘረኞችን እና የዘር ፖለቲካ አራማጆችን
በሙሉ ይገስፅልን! ህገ ሴጣኑን ይንቀልልን ይሄ ሁሉ የወገናችን ደም ፈሶ ይሄ ሁሉ ሀገር ወድሞም እንኳን በዚህም ይብቃችሁ ይበለን!!
#
ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ
#አዲስ አበባ
Filed in: Amharic