>

ከትግራይ መንግሥት [የተሰጠ] ጊዜያዊ መግለጫ  - (ትርጉም  በአቻምየለህ ታምሩ)

ከትግራይ መንግሥት [የተሰጠ] ጊዜያዊ መግለጫ 
 
*…. “የቦታ ማስተካከያ አደረግሁ እንጂ በጦርነት ተሸንፌ ከአፋርና ከአማራ ክልሎች አልወጣሁም” የሚለው ፋሽስት ወያኔ “የቦታ ማስተካከያ ማድረጌን እንደድክመት ቆጥረው ድጋሜ ትግራይን ለመውረር የሚያስቡ ኃይሎችን አለም ያስቁምልኝ” ሲል የተማጸነበትን የትግርኛ መግለጫ ትግርኛ ለማትችሉ ሙሉ መግለጫውን ቃለ በቃል ወደ አማርኛ ተርጉመነዋል። 
 
የትኛውንም ቋንቋ መቻል ሰዎች ተደብቀው የሚያወሩትን ለመረዳት ያስችላል 🙂 
የመግለጫው ሙሉ የአማርኛ ትርጉም እነሆ!
ትርጉም  በአቻምየለህ ታምሩ

ከትግራይ መንግሥት [የተሰጠ] ጊዜያዊ መግለጫ 
የትግራይ ሕዝብ እና መንግሥት ሕገ መንግሥታዊ ስርዓት ይከበር ስላሉ ብቻ ለአመታት ወደር የሌለው ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ስነልቦናዊ ጫና እየደረሰባቸው እንደመጣና አሁንም ተጠናክሮ እየቀጠለ እንዳለ የሚታወቅ ነው። ከዚህ በመቀጠልም ፋሽስቱ ጉጅሌ ዐቢይ አሕመድ ትግራይን ለማምበርከክ የሚያስችሉት የተለያዩ ዝግጅቶች አድርጎ የአማራ ክልል አመራር እና ሌሎች ግብረ አበሮቹ ከጎኑ አሰልፎ ከትግራይ ሕዝብ እና መንግሥት ላይ ወታደራዊ ወረራ እና ዘመቻ ዘር ማጥፋት ከታወጀ እነሆ ከአንድ አመት በላይ ሆኖታል።
ከዚህ ከአንድ አመት በላይ ያስቆጠረ ሕዝባዊ ጦርነት የትግራይ ሕዝብ ራስን በራስ የመወሰን መብቱ ለማስከበር ብሎ መራራ ትግል እያካሔደ ክቡር መስዋእት እየከፈለ መጥቷል፤ አሁንም አቅሙን ይበልጥ አጠናክሮ ሕዝባዊ ትግሉ አጠናክሮ እየቀጠለ ነው።ይህ ፋሽስታዊ ጉጅሌ ከግብረ አበሮቹ ሆኖ የትግራይ ሕዝብን በአራቱም አቅጣጫ ዘግቶ ምግብ መድሃኒት ነዳጅ እና ሌሎች መሰረታዊ ሸቀጦች ወደ ትግራይ እንዳይገቡ የትግራይ ሕዝብ የስልክ፤ የመብራት፤ የባንክ የትምህርት አገልግሎት እና ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎቶችን እንዳያገኝ የተቻለውን ሁሉ እያደረገ ትግራይና ሕዝቧን በመራራ መከራ ውስጥ እንዲኖር ቢፈርድበትም በፅኑ አንድነታችን እና ትግላችን በጠላቶቻችን ላይ ወርቃዊ ድሎች እያፈስን የሚበዛው የትግራይ አከባቢ ከጠላታችን እጅ ነፃ ካደረግነው ወራቶችን አስቆጥረናል።
እነዚህ ደመኛዎች ጠላቶች የትግራይ ሕዝብ ኅልውና ከባድ አደጋ የመሆን አቅም ለማዳከም ተገደው ወደ ሰላማዊ ንግግር እንዲመጡም ከኋላቸው እየተከተልን ከአማራ እና ዓፋር ክልሎች ከጠላታችን ላይ አንፀባራቂ ድሎች አስመዝግበናል።  በዚህ በፅናት መንገድ ላይ ተአምራዊ የትግራይ ሠራዊት ጀግንነት ከላቀ ቦታ እንደደረሰ ወዳጅና ጠላት በግልፅ የተረዳበት ታሪካዊ ምዕራፍ ታይቷል።
ከትግራይ ወጥተን ወደ ዓፋርና አማራ ክልል የገሰገስንበት ዋነኛ ምክንያት የጠላታችን አቅም ለማዳከም እንጂ የሆነ ቦታ በቋሚነት የመያዝ እና ግዛት የማስፋፋት ዓላማ እንደሌለን የትግራይ ሕዝብም ግዛት እንድናስፋፋ እንዳልላከን የታወቀ ነው። ስለሆነም በተለያዩ ጊዜያት ይዘናቸው የነበርነው የዓፋርና አማራ አከባቢዎች እየለቀቅን እና አላማችን ለማሳካት ያስችሉናል ያልናቸውን  ቦታዎች እየያዝን መጥተናል።
ዛሬም በተመሳሳይ ሁኔታ የተግራይ ሠራዊት ተይዘው የነበሩ አንዳንድ የዓፋርና አማራ አከባቢዎች ለቀን የሚገባ ማስተካከያ በማድረግ የትግራይ ሕዝብ ትግል በድል ለማጠናቀቅ የሚያስችለንን ስትራቴጂ ነድፈን የበለጠ አቅጣጫ እና ቦታ በማውጣት ለመተግበር ተወስኗል። ሠራዊታችን በሙሉ አቅሙ እያለ በራሳችን ፍላጎትና ተነሳሽነት ለበለጠ ድል እምናደርገው ማስተካል እንጂ ከጠላት እንቅስቃሴ ትርጉም ያለው መተሳሰር እንደሌለው የትግራይ መንግሥት ለሕዝቡ ማረጋገጥ ይወዳል።
አሁንም ትኩረታቸችን የትግራይ ሕዝብ ኅልውና ለማረጋገጥ ሲሆን የትግራይ ሠራዊት ከሚገኝባቸው አከባቢዎች ያሉት ያገር ሽማግሌዎች እና የእድሜ ባለፀጎችም እየተካሄደ ያለው ደማዊ ጦርነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እያነሱ ነው።  የኢትዮጵያ ሕዝብ ምኞትና ፍላጎትም በመሰረቱ ይህ ነው። ይህ እንዳለ ሆኖ የትግራይ ሠራዊት ወደመሀል በገባ ቁጥር ጠላት በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሐን ዜጎችን  በኃይል እያፈነ ወደ ጦርነት እንዲገቡ በማድረግ ለመናገርም በጣም የሚከብድ እልቂት እየፈፀመ ሊቀጥል በስፋት እየሰራበት መሆኑ የሚታወቅ ነው። ስለሆነም የኢትዮጵያ ሕዝብ ከልጆቹ እልቂት ተገላግሎ በሰላም እንዲኖር ሁሉም ሊያደርገው የሚችል ትግል እና ጫና እንዲያደርግ ጥሪ እናቀርባለን።
ይህ እንዳለ ሆኖ እኛ ወደመሀል አገር በገፋን ቁጥር ጣልቃ ገብነት የውጭ ኃይሎችም በተመሳሳይ ሁኔታዎች እየተለቀና እየሰፋ ሄዷል። ይህ ጦርነት ከአንድ አገር ውስጥ የሚደረግ የእርስበርስ ጦርነት ብቻ ሳይሆን የተለያየ ጥቅም ያላቸው አገሮች በተለያየ ሁኔታ የተሳተፉበት የትግራይ ሕዝብ ግን ካለማንም እርዳታ ብቻውን ያን ሁሉ ችግር የተሸከመበት ሁኔታ ነው ያለው። በአምባገነኑ ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራው የኤርትራ መንግሥትም የትግራይን ሕዝብን ለማድረቅ አምና የጀመረ ዘመቻ ዳግም ለመቀጠል ተጨማሪ መንቀሳቀስ እና እንቅስቃሴ እያደረገ እንዳለ የሚታወቅ ነው።
በሌላ አቅጣጫ ደግሞ ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ የተለያዩ ጥያቄዎች እየመጡ ነው።  የትግራይ ሕዝብ እና መንግሥትም ለሰላም የሚያግዝ ጠንካራ አቋም ሊወስድ ስለሚገባ የትግራይ ሠራዊት ከዚህ በፊት ከነበረባቸው አከባቢዎች ለመውጣት እንደ አንድ መሰረታዊ ምክንያት ተወስዷል።
የትግራይ ሕዝብ ጠላቶች ከገፀ ምድር ለማጥፋት ቆርጠው የተነሱ መሆናቸውን እያወቅን ከላያቸው ላይ አንፀባራቂ ድሎች ማፈስ የጀመርንበት በየካቲት ወር 2013 ዓ.ም. እኛ ለሰላም ቅርቦች እንደሆንን በማያወላውል ሁኔታዎች ግልፅ አድርገን መቆየታችን የሚታወቅ ነው።  ከዚህ በኋላም ቢሆን አቋማችን በተደጋጋሚ እየገለፅን ለዓለሙ ማኅበረሰብ እያሳወቅን መጥተናል።  የትግራይ ሠራዊት በነበረባቸው አከባቢዎች የሚወጣበት ያለበት አንዱ ምክንያት ለሰላም ስራዎች ሰፊ እድል ለመስጠት ነው።  ስለሆነም የዓለም ማኅበረሰብ በተመሳሳይ አቋም ሊይዝ እና ለተፈፃሚነቱ በትኩረት እንዲሰራ ጥሪ እናቀርባለን።
በዚህ አጋጣሚ ደግሞ በትግራይ ሕዝብ እየደረሰ ያለውን የዘር ማጥፋት፣ በሰብአዊነት ላይ እየደረሰ ያለው ወንጀል የጦር ወንጀል እንዲቆም እና ሁኔታዎች በሰላማዊ መንገድ ፍፃሜ እንዲያገኙ የላቀ እንቅስቃሴ እያደረጉ ላሉት አገሮች፣  ተቋማት እና ግለሰቦች የላቀ ምስጋና እና አክብሮት እንዳለን እየገለፅን እያካሄዱ ያለው ኃላፊነት የተሞላው ጥረት ወደ ተግባር እስኪቀየር አሁንም ጫናዎችን አጠናክረው እንዲቀጥሉ በተለይም ዳግማዊ ጄኖሳየይድ እንዲፈፀም የአለም ማኅበረሰብ ዝም ብሎ ማየት እንደለለበት ጥሪ እናቀርባለን።  በተጨማሪም  እጃቸውን አስገብተው ያሉት አገሮች ከዚህ የጀኖሳይድ ጦርነት እጃቸውን እንዲያነሱ እየገለፅን ካልሆነ በሞራል በሕግ እና በታሪክ ተጠያቂ መሆናቸው እናሳውቃለን።
የትግራይ ሕዝብ ልጆችህ ካሁን በፊት ከሚኖሩበት አከባቢዎች ለምን እየወጡ እንዳሉ በሚገባ ተረድተህ ዛሬም እንደትላንቱ ከመስመርህ ፀንተህ ትግልህን እንድታጠናክር የትግራይ መንግሥት ጥሪውን ያቀርባል።  እድሜው ለትግል የደረሰ ትግራዋይ ሁሉ ወደ ትግል እንዲቀላቀል ሁሉ ትግራዋይ ሊረባረብ ይገባል።  ይህንን ሕዝባዊ ጦርነት የሚያስፈልገውን ሁሉ ከሟሟላትም በቀጣይነት ሊሰራበት የሚገባ ኅልውናችን ሙሉ በሙሉ እስኪረጋገጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
በተለያዩ የአለም ክፍሎች ያላችሁ የትግራይ ዲያስፖራ በዚህ ሕዝባዊ ጦርነት እያሳያችሁት ለመጣችሁት ፅናትና አንድነት የትግራይ ሕዝብና መንግስት ትልቅ ክብር እንዳለው ከልብ ልንገልፅላችሁ እንወዳለን።  በሕዝባችሁ ላይ እየደረሰበት የመጣውን ወደር የሌላቸው ወንጀሎች አለም እንዲያውቃቸው ለማድረግ ገንዘባችሁን፣  እውቀታችሁን፣ ጉልበታችሁና ጊዜያችሁን ሰጥታችሁ  የተሟላ ትግል በማካሄዳችሁ የትግራይ ልጆች ደጋግመው እያስታወሱት የሚኖር ደማቅ ታሪክ ሰርታችኋል፤  እየሰራችሁም ነውና ክብር ለናንተ ይሁን። የትግራይ ሕዝብ ራሱ በራሱ የመወሰን መብቱ ሙሉ በሙሉ እስኪረጋገጥ የጀመራችሁትን ትግል አጠናክራችሁ  እንድትቀጥሉ ደግመን ጥሪ እናቀርባለን።
በስተመጨረሻም መጀመርያ እና መድረሻ ይህ የሕዝባዊ ጦርነት የትግራይ ሕዝብ መብትና ጥቅም ማረጋገጥ እንደሆነ በተደጋጋሚ የተገለጠ እውነታ ነው።  በመሆኑም ጠላት ይህንን አሁን ያደረግነውን የቦታ ማስተካከሎች እንደ ድክመት ቆጥሮ በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚያደርገውን የዘር ማጥፋት እንቅስቃሴ እስካላቆመ ድረስ የትግራይ ሠራዊት በሚመቸው ቦታ እና ሁኔታ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኑ ደግመን ለማረጋገጥ እንወዳለን።  አሁንም  እስከነ ሙሉ አቅም እና ችሎታችን ነን።  ሙሉ ሕዝባችን ለዘላቂ እና አስተማማኝ ኅልውናህ እንደ ከዚህ ቀደም ከዚህ ቀደሙም በበለጠ ለሁሉም አቀፍ ትግል ተዘጋጅ።  ካለምንም ጥርጥር በትግላችንና በፅናታችን ድላችን እውን ይሆናል።
ኅልውናችንና ደኅንነታችን በክንዳችን!
ትግራይ ታሸንፋለች!
የትግራይ መንግሥት
ታኅሣሥ 9 ቀን 2014 ዓ.ም.
መቀሌ
Filed in: Amharic