>

"በትግራይ ሰማይ የኢትዮጵያ አየር እንዳይበር ይታደግልኝ ...!!!" (የደብረፂዎን የተማጽኖ ደብዳቤ)

“በትግራይ ሰማይ የኢትዮጵያ አየር እንዳይበር ይታደግልኝ …!!!”
የደብረፂዎን የተማጽኖ ደብዳቤ

 

*…. ከዛሬው ደብዳቤው በሳቅ የገደለኝ “ከአማራና አፋር በገዛ ፈቃዳችን ስለወጣን ይህን አለም እንዲያውቅልን ቢሆን ጥሩ ነው” የሚለው ክፍል ነው
አህመድ ሱሌይማን
 
ደብረፂዎን ዛሬ ለ UN ዋና ስራ አስኪያጅ ጉትሬስ ሁለት ነገር በፍጥነት ቢደረግልኝ የሚል የልመና ደብዳቤ ፅፏል። የትግሬ መሪዎች እነዚህን ጥያቄዎች እንደሚጠይቁና ሊደረግላቸው የሚችልበት ዕድል ሊኖር እንደሚችል የኢትዮጵያ መንግሥት ከትግራይ የወጣ ሰሞን 1991 ኢራቅን ጠቅሼ በሁኔታው ፅፌ ነበር።
 በዋናነት አንስቼ የነበረው የ NO FLY ZONE (NFZ) ጉዳይን ነበር። 91 ላይ አሜሪካ፣ እንግሊዝና ፈረንሳይ ከ NATO ጋር በቅንጅት በሰሜኑ የኢራቅ ክፍል (ኩርድ) የኢራቅ መንግሥት ምንም አይሮፕላን የሲቪሊያንንም ጨምሮ እንዳያበር፣ የሚበር ካለም እንደሚመቱ አስጠንቅቀው በገዛ ሀገሯ የበረራ ዕቀባውን ሊያደርጉባት ችለዋል። ይሄ ሳዳም ሁሴን ጠላቶቹን በአየር እንዳይመታ ለማገድ በሚል ሰበብ የተላለፈ ነበር።
ይሄ የበረራ ዕቀባ ለ 13 አመት እንደ ፈረንጆች እስከ 2003 ቆይቶ የነበረ ሲሆን፣ በኋላም አስፍተውት በደቡቡም የኢራቅ ክፍል (ሺዓ) ተግብረውታል። በዚህም የኢራቅ መንግሥትን ቶርች በብረት አስረው በራሱ አየር ክልል ለዚህ ሁሉ አመታቶች እንዳይበር በማድረግና ጠላቶቹ በአይሮፕላን እንመታለን የሚል ስጋት ሳይኖርባቸው እንዲታጠቁ እንዲደራጁና እንዲጠነክሩ አድርገዋቸዋል። ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው በ 2003 እንደፈረንጆች እንደገና ወረራ አድርገው ኢራቅ የተበተነችው።
የትግሬው መሪ ዛሬ የጠየቀው ይሄንኑ ይደረግልኝ ብሎ ነው። በትግራይ ሰማይ የኢትዮጵያ አየር እንዳይበር ይታደግልኝ የሚል ነው። ይሁን ቢባል እነ አሜሪካ እንዴት ህጉን ተፈፃሚ ሊያደርጉ ይችላሉ ለሚል፣ ጅቡቲ ባላት ተወንጫፊ ሚሳዬሎች አማካኝነት በትግራይ ሰማይ የሚበርን የኢትዮጵያ አይሮፕላን መትታ በመጣል ህጉን ተፈፃሚ ታደርጋለች።
***
ከዛሬው ደብዳቤው በሳቅ የገደለኝ ከአማራና አፋር በገዛ ፈቃዳችን ስለወጣን ይህን አለም እንዲያውቅልን ቢሆን ጥሩ ነው የሚለው ክፍል ነው
Filed in: Amharic