>
5:18 pm - Saturday June 15, 8667

*... አዲ አርቃይ፣ ማይ ጠምሪ፣ ኮረም፣ ጨርጨር እና አላማጣ የአማራ እንጂ የትግራይ  አይደሉም ..!!!" (አቻምየለህ ታምሩ)

*… አዲ አርቃይ፣ ማይ ጠምሪ፣ ኮረም፣ ጨርጨር እና አላማጣ የአማራ እንጂ የትግራይ  አይደሉም ..!!!”
አቻምየለህ ታምሩ

 

*….. ብአዴን የሚባለው ጉድኮ እንኳን አዲ አርቃይ፣ ማይ ጠምሪ፣ ኮረም፣ ጨርጨር እና አላማጣ መላው ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎና ሸዋ በፋሽስት ወያኔ ቁጥጥር ስር ቢወድቅ እንኳን መቀመጫውን በነ አዳነች አበቤ ችሮታ ወዳገኘው የአዲስ አበባው ጽሕፈት ቤቱ አዛውሮ  እንቅስቃሴያቸው በጽሕፈት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለተወሰነው ምንደኞቹ የዞን አስተዳዳሪ እያለ መሾሙን የማይተው እርመ በል ነውረኛ ድርጅት ነው

አዲ አርቃይ፣ ማይ ጠምሪ፣ ኮረም፣ ጨርጨር እና አላማጣ በታሪክ ብቻ ሳይሆን በፋሽስት ወያኔ ሕገ አራዊት መሠረት እንኳን ይካለሉ ቢባል የአማራ ክልል እንጂ የትግራይ ክልል ክፍሎች አይደሉም።

 ባለፈው ባቀረብሁት አንድ ጽሑፍ ከ1983 ዓ.ም. በፊት ከ65% በላይ የአላማጣ ወረዳ ሕዝብ አማራ የነበረ ሲሆን  ወደ 25% የሚጠጋው ደግሞ ራይኛ ተናጋሪ እንደነበር ፋሽስት ወያኔ ራሱ እንደገና ያሳተመውን የ1977ቱን የሕዝብና የቤት ቆጠራ ማስረጃ ዋቢ በማድረግ አሳይቻለሁ። አዲ አርቃይና ማይ ጠምሪን በሚመለከት መጽሐፍ የጻፍንበት ስለሆነ በፋሽስት ወያኔ በግፍ ከመወረራቸው በፊት የነበራቸው ታሪክ አሻሚ አይደለም። አዲ አርቃይ፣ ማይ ጠምሪ፣ ኮረም፣ ጨርጨር እና አላማጣ አሁንም በፋሽስት ወያኔ ቁጥጥር ስር ናቸው። እነዚህ አካባቢዎች በፋሽስት ወያኔ  ቁጥጥር ስር ባሉበት ሁኔታ ሁሉም ቦታዎች ነጻ ወጥተው ተብሎ ዘመቻው በድል መጠናቀቁና ሠራዊቱ ባለበት ይቁም መባሉን አፈ ቀላጤው ለገሰ ቱሉ ነግሮናል። ይህ የተደረገው ብአዴን የሚባለው ዘግናኝ ፍጥረት ፈቅዶ ነው። ለነገሩ ይህ ዘግናኝ ፍጥረት ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ጎንደርና ዋግ በፋሽስት ወያኔ ቅኝ ግዛት ስር ወድቀው በነበረበት ወቅት ጎጃምን፣ ጎንደር ከተማ ዙሪያና ሰሜን ሸዋን ብቻ ሊገዛ አስተዳዳሪ እያለ ምንደኞቹን ይሾም የነበረ ጉድ ነው። ብአዴን የሚባለው ጉድኮ እንኳን አዲ አርቃይ፣ ማይ ጠምሪ፣ ኮረም፣ ጨርጨር እና አላማጣ መላው ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎና ሸዋ በፋሽስት ወያኔ ቁጥጥር ስር ቢወድቅ እንኳን መቀመጫውን በነ አዳነች አበቤ ችሮታ ወዳገኘው የአዲስ አበባው ጽሕፈት ቤቱ አዛውሮ  እንቅስቃሴያቸው በጽሕፈት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለተወሰነው ምንደኞቹ የዞን አስተዳዳሪ እያለ መሾሙን የማይተው እርመ በል ነውረኛ ድርጅት ነው። ከዚህ በላይ ምን መከራ ሊደርስበት እንደሚችል ባላውቅም አማራው ብአዴን የሚባለውን ዘግናኝ ፍጥረት ተሸክሞ እስከቀጠለ ድረስ አማራ ወደፊትም ገና ብዙ ውርደት ይጠብቀዋል።
Filed in: Amharic