>

እኛ ኢትዮጵያዊያን አጎዋንን መተካት እንችላለን ??? (ፊልጶስ)

እኛ ኢትዮጵያዊያን አጎዋንን መተካት እንችላለን ???

 

ፊልጶስ


”ጥሩ ሰው ለመሆን ጥሩ ጓደኛ ይኑርህ፤

የተሳካለህ ሰው ለምሆን ግን ጠላት ይኑርህ።” የሚለው አባባል ከግለሰብ ጀምሮ እስከ አገር ድረስ  ለሁሉም ባይሆን ላወቀበት ይሰራል።

ብዙ ጠላት ያላቸው አገሮች፣ ራሳቸውን ለመከላከልና ብሎም አጠፋውን ለመመለስ ፤ ”ለጠላቶቻችን እጅ አንሰጥም!” በማለት ራሳቸውን ነጻከማውጣት አልፎ   የተደበቀ ኃይላቸውን እና እውቀታቸውን  ለመጠቀም በቅተውበታል።  እስራኤል እንደ አገር ለመመስረት ያበቃት የጠላትመብዛት  በአንድነት እንዲቆሙና ብሎም አሜሪካንና አውሮፓን ከጎናቸው አሰልፈው ዛሬ ዓለምን ለመዘውር በቁ፤ ከዚህ ላይ ጥራት እንጅ የቁጥርብዛት ወሳኝነት እንደሌለው መገንዘብ ያሻል።  ኢራን  ከ1979 ጀምሮ በአሜሪካና በአውሮፓ የተጣለባትን  ማንኛውንም ማዕቀብ ተቋቁማ አሁንካለችበት ደረጃ ደርሳለች።

ጥያቄው ዛሬ እኛስ……  አሜሪካና  አውሮፓ   በአገራችን ላይ ያላቸው ዓላማ   ከምጣኔ ሃብት ማዕቀብ ባለፈ ” እጃችሁን ጠምዝዘን  በ’ኛ ትዛዝትኖራላችሁ ወይም  ወያኔን እና ኦነግን ተጠቅመን እናፈርሳችኋላን።”  የሚል ነው። ለዚህ ደግሞ በድብቅ ሳይሆን በግልጽ  ‘ርምጃ  መውሰድከጀመሩ ውለው አድረዋል።

”ፕሬዝዳንት ባይደን ኢትዮጵያን ከአጎዋ ተጠቃሚነት የሚያግደውን ውሳኔ ፈረሙ” የሚለውን ዜና ሳንብና ስሰማ  በግሌ እንደ አገር፤እንደመንግሥት  እና እንደ ህዝብ ማንነታችን የሚፈተንበት ግዜ መድረሱን ገሃድ አድርጎታል።

ይህ አጎዋ የተባለው አሰራር ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ  ተመጽዋች  አገራት የተለያዩ ምርቶችን ወደ አሜሪካ ገበያ ከቀረጥና ከታሪፍ ነጻ በሆነሁኔታ በማስገባት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ስምምነት ነው ይባላል። ግን በዚህ የንግድ ስምምነት

ማን የበለጠ ተጠቃሚ እንደሚሆን ለባለሞያዎች ለተወውና በተለይም አሜሪካኖች በዚህ እንደማያቆሙ በወያኔና በኦነግ በኩል ያልቻሉትንኢትዮጵያን የማፈረስ ዓላማ ፣ በሌላ መንገድ ማንኛውንም ኃይላቸውን እንደሚጠቀሙ እሙን ነው። ይህ  ያለተገልጸለት ካለ መጸሃፍ እንደሚለው ፤

”ማየትስ ታያላችሁ ግን አታስታውሉም፤ መስማትስ ትሰማላችሁ ግን አታዳምጡም ”  የተባለው ለእኛ ነው።

ዘገባዎች እንደሚሉት ” ኢትዮጵያ የአጎዋ ተጠቃሚ ከሆነችበት ጊዜ ጀምሮ በየዓመቱ እስከ ከ150 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው የቆዳ፣ ጨርቃጨርቅና የአልባሳት ምርቶችን ወደ አሜሪካ ስትልክ ቆይታለች።” ይላል።

ታዲያ መንግሥት በርግጥም ከኦነጋዊ እመለካከቱ ራሱን አጽድቶ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት ቆሞ፤  በህዝብ ላይ እምነት ካሳደረና ፤ በውጩዓለምም የሚኖረውንም ዜጋ ” ሲበርደው እቅፍፉኝ ፤ ሲሞቀው ዘወር በሉ” ማለት ካቆመ፤  በአሜሪካ ከታገደችበት ከአጎዋን የምታግኘውን ገቢበራሷ በዜጎቿ ትብብር  መተካት ይቻላል።

ይኽውም፤

1/ መንግሥት፣ የፋብሪካና የአምራች ባለቤቶች ግልጽ የሆነ በባለሞያዎች የተጠና መረሃ-ግብር መንደፍ፤ መረሃ -ግብሩ ከአጎዋን የታጣውን ገቢበአገር ወስጥና በሌላው ዓለም እንዴት   ምርታቸውን መገባየት የሚችሉበትን መንገድ ማጥናት።

2/ የፋብሪካ አምራች ባለቤቶች ምርታቸውን ለዓለም ገብያ የሚያቀርቡበትና የሚሸጡበት   ከዘመኑ ጋር አብሮ የሚሄድ የኦንሊን (online)  ድህረ-ገጽማዘጋጀት።

3/ መንግሥት ከውጭ የሚያስገበውን  የጨርቃ-ጨርቅና የቆዳ ምርት በአገር ውስጥ እንዲመረትና እንዲሸጥ ማደርግ::

4/ የኢትዮጵያ ህዝብም በተቻለ መጠን የአገር ምርትን እየገዛ እንዲጠቀምና  ከውጭ ከሚመጡ አልባሳትና የቆዳ ምርት ውጤቶች ራሱንመከላከል።

5/ በተለይም በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያያኖች ለራሳቸው፣  ለአገር ቤት ቤተስቦቻቸውና እንዲሁም በስጦታ መልክ   የአገር ውስጥ ምርትንመግዛትና በኦንላየን (online) ግብይቱ ላይ ቀዳሚ አስተዋአጾ ማድረግ፤ በተጨማሪም የኢትዮጵያን ምርት በተላላቅ “ኦንላየን “ ድህረ-ገጾች ላይእንዲገኙና እንዲሸጡ  የተቀናጀ ስራ መስራት።

ለዚህ ምሳሌ የሚሆኑን ህዝቦች ህንዶች ናቸው፤ ህንዶች ክአሜሪካም ሆነ ከአውሮፓ ወደ አገራቸው ሲሄድ ቁራጭ ልብስና ቁሳቁስ ገዝተውአይሄዱም።የሚሄዱት ጥሬ  ዶላራቸውንና ኢሯቸውን ይዘው ነው። እነሱ የሚያደርጉት በአገራቸው በህንድ የሚመረተውን ለእንድ ዓመትና ለሁለትዓመት የሚበቃቸውን ሸምተው፣ በወዳጆቻቸውም በስጦታ መልክ ገዝተው ወደ አሜሪካና አውሮፓ ይመለሳሉ። ባሉበት አገርም ሆነውለቤተሰቦቻቸው ሆነ ያስፈልጋል የሚሉትን በዚያ በእገራቸው  (online) የሸምታሉ።ታዲያ እኛም ይህን መሰሉን ነገር ብናደርግ ለአገራችን ኢኮኖሚየምናደርገው አስተዋአጾ ከአጎዋን የምናጠውን ገቢ ከመተካት በላይ የአገርቢቱን ምርት ያበረታተል።

ከላይ ያነሰዋቸው ሃሳቦች  ያጋራኝና ይህችን መጣጥፍ እንድጽፍ ያደረገኝ የባሮቲዮብ አዘጋጅ ባልደረባ ሲሆን በዚህ አጋጣሚ የሃሳቡ ባለቤት እሱመሆኑን መግለጽ እወዳለሁ። በተጨማሪም ማሳሰብ የምፈልገው  በአገራዊ ምጣኔ ሃብት ዘርፍ የተሰማራችሁ የአገር ውስጥም ሆናችሁ በውጭአገር የምትኖሩር ባለሞያዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ማስገንዘቢያ ብትሰጡበት ፣ እንዲሆም የሚመለከታችሁ  ክፍሎች ይህን  እንደ መጀምሪያሃሳብ ወስዳችሁ የተሻለና ገንቢ ስራ እንዲሰራ ብትተባበሩ  በአጎዋን  የምናጠውን መተከታ ብቻ ሳይሆን ራሳችን ለራሳችን መሆን እንደምንችልዓለምን እናስተምርበታለን፤ እኛም እንማርበታለን።

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!!

 

 

Filed in: Amharic