>
5:13 pm - Sunday April 19, 5857

በአማራ ህዝብ ስም የተደራጁት አብንን እና ብአዴን በስልሳ ሽህ አማራ ጅምላ ፍጅት ተስማምተዋል...!!!  ሸንቁጥ አያሌው

በአማራ ህዝብ ስም የተደራጁት አብንን እና ብአዴን በስልሳ ሽህ አማራ ጅምላ ፍጅት ተስማምተዋል…!!!

 ሸንቁጥ አያሌው

-ስልሳ ሽህ አማራዎች በወለጋ ተከበዉ የጅምላ ፍጅት እየተደረገባቸዉን ነዉና አለም ይድረስላቸዉ ሲል ባልደራስ ለተባበሩት መንግስታት አቤት ብሏል::ይሄ የባልደራስ ስራ  በወርቃማ የታሪክ መዝገብ ላይ የሚሰፍር ነዉ::በአማራ ህዝብ ስም የተደራጁት ግን በአማራ ህዝብ እልቂት ተስማምተዋል::
-በአማራ ህዝብ ስም ፖለቲካ የሚነግዱት አብን እና ብአዴን በአማራ ህዝብ እልቂት ተስማምተዉ ዝም ብለዋል::
-ብአዴን ይሄ ሁሉ አማራ ሲፈጅ አንድም ጊዜ ትንፋሽ ሳያሰማ ብልጽግና ዉስጥ የአሰራር መዛነፍ አለ የሚል ክስ ላቀረቡ አንድ አባሉ እጅግ ብዙ እና ሰፊ ዝባዝንኬ መግለጫ አዉጥቶ ተንኮል ነዉ ሲል የብልጽግናን መበስበስ ያጋላጡትን ጀግና ወንጅሏቸዋል::
-አብን የተባለዉ የብአዴን ቅጣይም የአማራን ህዝብ ፍጅት ጉዳይ ለተባበሩት መንግስታት እና ለአለም ማህበረሰብ ከማሳወቅ ይልቅ ስለ ምክክር መድረኩ መቀበጣጠር ይዟል::
Filed in: Amharic