>

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከመስቀል አደባባይ ፤ወይብላ ማርያም እና ባንዲራ  ጋር ተያይዞ ለተነሱት ጥያቄዎች የሰጡት ማብራርያ....፦ (አወድ ሞሀመድ)

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከመስቀል አደባባይ ፤ወይብላ ማርያም እና ባንዲራ  ጋር ተያይዞ ለተነሱት ጥያቄዎች የሰጡት ማብራርያ….
አወድ ሞሀመድ

👉በመጀመርያ በመስቀል አደባባይ የፕሮቴስታንት አማኞች የጠየቁት የገቢ አሰባሰብ ፕሮግራም ፍቃድ ሰጥተናል፡፡
👉ፕሮግራሙ ሊካሄድ አንድ ቀን ሲቀረው አንድ ከፕሮግራሙ ጋር ግንኙነት በሌለው ሰው እንወርሳለን የሚል ሃሳብ ተንፀባረቀ፡፡
👉ይህም በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ቁጣ የፈጠረ በመሆኑ ግንኙነት ስናደርግ ይህን ያለው ከፕሮግራሙ ጋር ግንኙነት የሌለው ሰው መሆኑን ነግረናቸው ፤ነገር ግን በዚህም ወገን ያለው አባባልና እሱን መሰረት አድርጎ የተፈጠረውን ስሜት ሁለቱም ሃይ ሊባሉ ይገባል አልናቸው፡፡
👉ነገር ግን ጉዳዩ ጠንከር እያለ ሲሄድ በፕሮግራሙ እለት ተገኝተን ይሄ አደባባይ የሁላችንም ነው በማለት  ማንም ወራሽ እና ተወራሽ እንደሌለ የሚጠቁም መልእክት አስተላለፍን
👉ይህ አባባል በዛ መድረክ ሲነገር የመጀመርያ አልነበረም፤ ሌሎችም ተናግረዋል፡፡ እኔ ራሴ ደጋግሜ በተለያዩ ፕሮግራሞች ተናግርያለሁ፡፡
👉ስለዚህ ጉዳዩን አሁን እንዲባባስ ያደረገው የተጫጫኑ ስሜቶች በመኖራቸው ምክንያት ነው፡፡
👉ስለዚህ ጥያቄው ሲገፋ ያልነው በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ እንፍታ ነው ያልነው፡፡ በመረጃና በማስረጃ መፍታት የሚቻልባቸው ብዙ አማራጮች አሉ፡፡
👉ከአደባባይ ጋር በተያያዘ የውጪ ብቻ ሳይሆን የራሷ የራሷ የኢትዮጵያ ልምድም ጭምር አለ፡፡
👉ግንኙነት ለማድረግ ከመጀመርያው አንስቶ ብዙ ጥረት ተደርጓል ፤ከመጀመርያው የፓትርያርኩ መታመም አንስቶ በተለያዩ ምክንያቶች ተራዝሟል፡፡
👉እኔ በግሌ ፓትርያርኩ ጋር በመሄድም ጉዳየን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ እንፍታ ብዬ አነጋግርያለሁ፡፡ ልዩነት አልነበራቸውም፡፡ ይህንን ሃሳባችሁን በደብዳቤ አስገቡልን አሉን ይህንንም አድርገናል፡፡
👉ከዚህ ቀደም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ እኛ ወደነሱ እሄዳለን ፤እነርሱም ወደእኛ እየመጡ በርካታ ጉዳዮችን ፈትተናል፡፡
👉ዛሬ እንኳን ግንኙነት ቀጠሮ አለ ስለተባለ የተወሰነው እዚህ ሆነን ጉባኤውን እናስኪድ ሌሎቻችን ደግሞ እዛ እንሂድ ብለን ተከፋፍለን ነው የሄዱት፡፡
👉እኛ  ከሃይማኖት ጋር ፉክክር የምናደርግ መሪዎች አይደለንም!!
👉ወይብላ ማርያም ጋር የተከሰተው ክስተት አሳዛኝና መሆን ያልነበረበት ጉዳይ ነበር፡፡
👉በምንም መንገድ ታቦት ውጪ ማደር አልነበረበትም፡፡
👉ጉዳዩ አሁን በህግ ተይዟል፡፡ እውነታውን አውቀን በህግ ተጠያቂ እስካላደረግን ድረስ ይቅርታ ብቻውን በቂ አይደለም፡፡
👉ከባንዲራ ጋር ተያይዞ የሚነሱ የተለያዩ ሃሳቦች አሉ፡፡ ይህ ጉዳይ የብሄራዊ ምክክር አጀንዳችን ይሆናል፡፡ በዚህ ምክንያት ጥልም ግጭትም በፍፁም አንፈልግም፡፡ ሰውም እንዲሞት አንፈልግም!! ጉዳዮችን ሁሉ ከፖለቲካ ዝንባሌ ጋር ማያያዝም ተገቢ አይደለም፡፡👇
Filed in: Amharic