>

"አማራ ኢትዮጵያን በራሱ አምሳል ሰርቷታል!" ይሉት ተረት አገር ለማፍረስ  የተወጠነው ሴራ አካል ነው...!!! (አበበ በለው)

“አማራ ኢትዮጵያን በራሱ አምሳል ሰርቷታል!” ይሉት ተረት አገር ለማፍረስ  የተወጠነው ሴራ አካል ነው…!!!

አበበ በለው

*.... ሁሉም እንደሚያውቀው መረጃወችም እንደሚያሳዩት ኢትዮጵያን አማራ እራሱን ጥሎ ተቀበላት እንጅ ፡አማራ ኢትዮጵያን አማራ አላደረጋትም፡፡ በአምሳሉም አልፈጠራትም፡፡እንዲያውም አማራነቱን ጥሎ ኢትዮጵያን ተላበሳት እንጅ፡ ኢትዮጵያን አማራ አማራ አላደረጋትም
ለአለፉት 40 ዓመታት አማራ እኛን ጎድቶናል አማራ ኢትዮጵያን በራሱ አምሳል ሰርቷታል ፡ስለዚህ ኢትዮጵያን እንደገና አፍርሸ እኔን አስመስየ እሰራታለሁ ፡ብለው የተነሱት የትግራይ እና የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ ነን የሚሉ ፖለቲከኞች፡ይህን ሀሳባቸውን ለማሳካት የቻሉትን ሁሉ አድረገዋል።
ይህን አማራ ኢትዮጵያን እራሱን አስመስሎ ሰርቷል የሚለውን ውንጀላቸውን ፡ እያስተማሩ፡የቻሉትን ያህል ከብሄራቸው ተወላጆች ውስጥ ቀላል የማይባል  አባል እና ታጋይ አግኝተውበታል፡፡
ይህ ውንጀላቸው ለስልጣንም አብቅቷቸዋል ፡፡
ያሰቡትን መፈፀም እና ያለ ከልካይ አላማቸውን ማሳካትንም ተያይዘውታል፡፡
የዚህ ሃሳብ አራማጆች የወጠኑትን ኢትዮጵያን በራሳቸው አምሳል የመስራት ህልም እውን ማድረግ የሚያስችል የአስተዳደር ስርዓት፡ በክልልም በብሄርም ቀርፀው፡ አማራን ጠልተው አስጠልተው ማጥፋቱን እያፋጠኑት ነው ፡፡
ይሁን እንጅ ዛሬም ኢትዮጵያ እንደተመኙት በፍጥነት እነሱን መምሰል ባለመቻሏ ፡ያለው አማራጭ ፡ኢትዮጵያን እራሱን አስመስሎ ሰርቷታል ብለው የፈረጁትን አማራን ገድሎ ከምድረገፅ ማጥፋትን በጋህድ አየሰሩት ነው፡፡
ሁሉም እንደሚያውቀው መረጃወችም እንደሚያሳዩት ኢትዮጵያን አማራ እራሱን ጥሎ ተቀበላት እንጅ ፡አማራ ኢትዮጵያን አማራ አላደረጋትም፡፡
በአምሳሉም አልፈጠራትም፡፡እንዲያውም አማራነቱን ጥሎ ኢትዮጵያን ተላበሳት እንጅ፡ ኢትዮጵያን አማራ አማራ አላደረጋትም።
እንደከሳሾቹ አባባል አማራ ኢትዮጵያን በአምሳሉ ቢሰራት ኖሮ ፡የሌሎችን ቀምቶ ቢሆን ኖሮ ፡ዛሬ ኢትዮጵያዋያን ሁሉ የአማራ ብሄር ብቻ በሆኑ ነበር፡
በኢትዮጵያ ከመቶ በላይ ብሄር እና ቋንቋወችም ባልኖሩ ነበር፡፡
የሆነው ግን ግልፅ ነው ፡አማራ ህብረ ብሄራዊቷን ኢትዮጵያ እየሞተም እሷን ሆኖ ዜግነት እና ሀገር ብሎ ሲኖር፡ ሌሎች ግን ብሄርም ሀገርም ይዘው ኖረዋል፡፡
የግፍ ግፍ የሆነው ደግሞ፡
በየተራ ኢትዮጵያን በአምሳላቸው መስራት የፈለጉት ፅንፈኞች፡አማራን ከኢትዮጵያዊነት ማስለቀቅ ስለአልቻሉ እና ፡የሚሰሯት ኢትዮጵያ እነሱን ብቻ መምሰል ስላልቻለች፡ ሌላውን ጨርሰው እነሱን ሊያስመስሏት እየሞከሩ ነው።
የሚፈልጓት ኢትዮጵያ እነሱን ብቻ እንድትመስል ፡የማይፈልጓትን ኢትዮጵያ ሆኖ የኖረውን  አማራ እያሳደዱት ነው።
 ሌላው ቀርቶ ፖለቲካውንም  ስልጣኑንም ሳይጠይቃቸው፡አማራ መሆኑ ብቻ እንዲያስገድለው አወጀውበታል፡፡
ከአማራ የተወለደ  የእነሱ ቋንቋ ተናጋሪ ቢገኝም ከአማራ ልጅ  አያሳየን በለው እዛው ተወልዶ እነሱን የሚሆነውንም ዘሩን ቆጥረው አንየው አሉ።
ሰሞኑን  ከኦሮምያ የተሰደዱ እናት፡ ልጃቸው ኢትዮጵያን መከላከያ ተቀጥሮ እየጠበቀ፡ እናቱን ግን ኢትዮጵያን ብለው እሱን ወልደው ካሳደጉበት  እንዳይኖሩ፡ ልጆቻቸውን ገለው፡ አማራ ሆነው እንኳን ፡ስሙን ወደማያውቁት ደብረ ብርሃን ተሰደዱ፡፡
እንግዲህ ኢትዮጵያን የሚያውቅ እና ኢትዮጵያዊ የሆነ ካለ feb 17/2022 በዋሽንግተን ዲሲ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተናል #nomore አማራ እና አፋር መግደል ብለናል ተገኙ እና ድምፃችሁን አሰሙላቸው።
ቪዲዮውን እዩ እና ፍረዱ
Filed in: Amharic