>

አቢይን ያላችሁ - እስኪ እንያችሁ! (ዳግማዊ ጉዱ ካሣ)

አቢይን ያላችሁ – እስኪ እንያችሁ!

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ (ma74085@gmail.com)


ጥቂት የማይባሉ ሥነ ቃላትንና ምሣሌያዊ አባባሎችን አውቃለሁ፡፡ እነዚህን መሰል ውብ የነገር ማሳመሪያዎችን አዘውትረው ከሚጠቀሙ ሰዎች መካከልም አንዱ ነኝ ብዬ አስባለሁ፡፡ የአቢይን ኦነግ/ኦህዲድ የኦሮሙማ መንግሥትን ለመግለጽ ከሚረዱ ሥነ ቃላዊ ትውፊቶች ውስጥ ታዲያን የሚከተለውን ቀድሞ ወደ አእምሮየ የሚመጣ የለም፡፡ እርግጥ ነው ብዙዎች እንዳሉ አውቃለሁ፤ ለአብነት ያህል “ባለጌን ካሳደገ ያነቀ ጠደቀ”፣ “ወይ አታምር ወይ አታፍር” ፤ “ቀን የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል” ፤ “የዕብድ ቀን አይመሽም”፤ “መሸጥ የለመደ እናቱን ያስማማል”፤ እና የመሳሰሉት እዚህ ላይ ቢጠቀሱ አቢይንና ሥርዓቱን ለመግለጽ ከበቂ በላይ ናቸው፡፡

በነገር የማይግባቡ ባልና ሚስት ነበሩ አሉ፡፡ ሚስት ጥሎባት ነገረ ሥራዋ ሁሉ ከባሏ በተቃራኒ ነው፡፡ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም አንድ ወቅት “ወርቅ ቢያነጥፉለት ፋንድያ ነው የሚለው ጥቂት ባልሆነበት ሁኔታ …” ሲል በምንም ነገር የማይረኩ ዜጎችን እንደገለጸው ያቺም ሚስት ባሏ የፈለገውን ያህል ቆንጆ ነገር ሊያደርግላት ቢፈልግም እሷ ግን ግራ ተጓዥ በመሆኗ ምንም ነገሩ አይጥማትም፡፡ በዚያም ምክንያት ከእርሱ በተቃራኒ ለመቆም አንድም የሚያግዳት የሞራልም እንበለው የሃይማኖት አጥር አልነበረም፡፡ ስለሆነም እንሂድ ሲላት እንተኛ፣ እንብላ ሲላት እንጠጣ፣ ወደላይ ሲላት ወደታች … የምትል ቅንጭላት አዟሪ ነበረች፡፡

አንድ ቀን አንድ እንግዳ ወደቤታቸው ይመጣል፡፡ እራት ተበልቶ ሲያበቃ የመኝታ ሰዓት ሲደርስ ባል ሆዬ “እኔና እንግዳው መደቡ ላይ እንተኛለን፡፡ አንቺ ልጆችሽን ይዘሽ አልጋው ላይ ተኚ” ሲላት “ኧረ ባክህ! ለምን ብዬ! አንተና ልጆችህ አልጋው ላይ፣ እኔና እንግዶ መደቡ ላይ ነው እምንተኛው፤ እንዲህ ስትል አታፍርም?” ብላው እርፍ፡፡ አያድርስ አትሉም? ይሄ ነገር እንኳን በቤቴ አልሆነ፡፡ ሆ!!  

“ኖሮ ኖሮ ወደመሬት፣ ዞሮ ዞሮ ወደቤት” ያለ ነውና ይህች ሚስት ጎርፍ ይወስዳትና ትሞታለች፡፡ ያኔ ባልዬው ጎረቤቶቹን ሁሉ ጠርቶ አስከሬኑን ፍለጋ ወደወንዙ ይሄዳሉ፡፡ ወንዙ አጠገብ ሲደርሱ ታዲያ በሴትዮዋ የተገላቢጦሽ ተፈጥሮ አንጀቱ ሲያር ዓመታትን ያስቆጠረው ባል ቆም ብሎ “አንደዜ ስሙኝማ ወንድምና እህቶቼ! የባለቤቴን ሬሣ የምታፋልጉኝ ከወንዙ ወደታች ሣይሆን ከወንዙ ወደላይ ነው፡፡ ምክንያቱም ክብርት ባልተቤቴ ነገረ ሥራዋ ሁሉ የተገላቢጦሽ ስለሆነ ለወራጅ ወንዙም ቢሆን ወደላይ እንጂ ወደታች አትሄድለትም፤ ጎርፉን እምቢ ብላ ሽቅብ እንዲወስዳት ታስገድደዋለችና በታች በኩል ብንፈፈልጋት ስለማናገኛት ትርፉ ድካም ብቻ ነው የሚሆንብን፡፡” በማለት አስከሬን ፍለጋቸውን ካለወጉ ወደላይ እንዲሆን አስገደዳቸው፡፡

 እንግዲህ የወደላይ አቅጣጫ ፍለጋቸው ይስመር አይስመር በሌላ ጊዜ የምንመለስበት ጉዳይ ሆኖ የኦነግ/ኦህዲድ የአቢይ መንግሥት ግን ከዚህች ሴትም በባሰ ከሕዝብ ፍላጎትና ከሀገር ዕድገት በተቃራኒ እየተጓዘ ባለፉት አራት ዓመታት ምን እንዳከናወነና በሀገርና በሕዝብ ላይም ምን ያህል ግዙፍ ግፍና በደል እንዳደረሰ በተለይ ኢትዮጵያውያን ነን ብለን የምናምን ወገኖች ሁሉ በሚገባ እንረዳዋለን፡፡ የአቢይ ወገኖች ግን አንዴውኑ ሁለመናቸው በርሱ ሃሽሻዊ ፍቅር ታውሯልና እርሱ እውነት ዕርሙ የሆነ አንደበቱን በከፈተና አሁን ተናግሮ አሁኑኑ የሚቃረነውን ዝባዝንኬ ባስተጋባ ቁጥር ከ“ማንጨብጨብ” በዘለለ የዚህ ብላቴና ሰይጣናዊ ተፈጥሮ ሊገባቸው አልቻለም፡፡ አለመለከፍ ነው፡፡ ለወትሮው “ሴት የላከው ጅብ አይፈራም” ነበር የሚባለው፡፡ አቢይ የላከው ደግሞ ሞትን ብቻም አይደለም ታሪክንም፣ ይሉኝታንም፣ ሀፍረትንም … ምንንም ምንንም አይፈራም፡፡ የሚገርም የታሪክ ሥላቅ ነው፤ የሚያስደነግጥ የትልልቆች ማነስና ከክብር ማማ ባልተጠበቀ ፍጥነት ወርዶ መፈጥፈጥንም እያየን ነው፡፡ የነዚህ አሽቃባጮች የነገ ዕጣ ፋንታ ምን እንደሚሆን ማወቅ ከባድ አይደለም፡፡ ያም ቀን ይደርሳል፡፡

በግርድፍ ግምት ከኢትዮጵያ ሕዝብ 90 በመቶ የሚሆነው ፍላጎቱ እጅግ ተመሳሳይ ነው፡፡ ይህንን እውነት በሕዝቡ ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎችና የዕለት ከዕለት መስተጋብሮች መገንዘብ ይቻላል፡፡ በደስታና በሀዘኑ፣ በፅዋ ማኅበሩና በዕድሩ፣ በዕቁቡና በወንፈሉ (በደቦ ሥራው) ይህ በገዢዎቹ እንዲለያይ ብዙ ሤራና ሻጥር የተሠራበት ሕዝብ እስካሁን አልተለያየም፤ ለገዢዎቹ ፍላጎትም አልተንበረከከም፡፡ አማራ ኦሮሞን፣ ኦሮሞ ትግሬን፣ ትግሬ አማራንና ኦሮሞን … ማግባቱንና እርስ በርስ መዋለዱን፣ በአበልጅና በአበነፍስ መተሳሰሩን አልተወም፡፡ የኢትዮጵያ ትንሣኤ አይቀሬነቱን ከሚያረጋግጡ ማኅበራዊ ኹነቶች አንዱ እንግዲህ ይህ የሕዝብ ለመንግሥት መሪዎቹ የተጫረሱ ዐዋጅ አይበገሬ ሆኖ መገኘት መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ መሪ የላትም፡፡ መሪው ተበላሽቷል፡፡

የአቢይ መንግሥት ምን ይመስላል ብለን እንጠይቅና ትንሽ እንነጋገር፡፡ የአቢይ መንግሥት በሕዝብ የደም ደለል የቆመ፣ ካለሰው ጭዳ ፀንቶ መቆም የማይችል፣ ሁከትና ብጥብጥ ካልነገሠ በሰላምና መረጋጋት ሀገርን ማስተዳደር የሚቻል መስሎ የማይታየው የአጋንንት ስብስብ ነው፡፡ ለዚህ ነባራዊ ሁኔታ ከሃይማኖት አንጻር ቀጥሎ ያለውን ሃቅ መጠቆም ይቻላል፡፡

እንደአጠቃላይ እውነት የአሁኖቹ በርካታ የዓለም ሀገራት መንግሥታት ዋና አለቃቸው ሊቀ ሣጥናኤል ነው፡፡ ይህን ለማረጋገጥ ተግባሮቻቸውን መመልከት ጥሩ አስረጂ ነው፡፡ የሊቀ ሣጥናኤል መገለጫዎች ሙሉ በሙሉ በነዚህ መንግሥታት ዘንድ ይንጸባረቃሉ፡፡ መንግሥታቱ የሰይጣንን መገለጫዎች ካላሳዩ ቃል ኪዳናቸውን እንዳፈረሱ ተቆጥሮ መከራና ፍዳ በነሱ ላይ ይደርሳል፡፡ ከሰይጣን ጋር በነፍሱ ተወራርዶ የገባ ሁለት ወዶ አይሆንምና ሰይጣን የሚያዘውን ሁሉ ሳያንገራግር መፈጸም አለበት፡፡ አጅሬ ቀልድ አያውቅም፡፡ ስለሆነም ቀጥ ብለው መታዘዝ አለባቸው፡፡ ግብሩን ማሟላት፣ የሴቴኒክ ባይብልን መርኆዎችና ትዕዛዛት ማክበር፣ ርህራሄንና ምሕረትን መጠየፍ ወዘተ. ከአንድ የሰይጣን ደቀ መዝሙር የሚጠበቅ አነስተኛው መሥፈርት  ነው፡፡ የኛም መንግሥት የዚያው ዓለም አቀፍ የአጋንንት አገዛዝ አካል በመሆኑ የተለዬ ርህራሄም ሆነ ሀገርና ሕዝብ ወዳድነት ሊያሳይ አይችልም፡፡ ብዙዎቻችን ላይገባን ይችላል እንጂ እነአቢይና ሽመልስ ወለም ዘለም ሳይሉ በቀጥታ እየታዘዙት ያሉት  ከጨለማው መንግሥት ከአባታቸው ከዲያቢሎስ ነው፡፡ እነሱም ብቻ ሳይሆኑ የነሱ ፈጣሪዎች የሆኑት ሕወሓቶችም የዚያው የአጋንንቱ ዓለም አካል በመሆናቸው እነሱም ታዛዥነታቸው ለሰይጣን ነው፡፡ ብዙዎቻችን ባይገባን ወይም እንዲገባን ባንፈልግ እንጂ ብዙዎቹ ዝነኛና ሀብታም የዓለማችን ዜጎች ከበርካታ የፖለቲካ አመራሮች ጋር የዚያው የሉሲፈር መንግሥት አራማጆችና አባላት ናቸው፡፡ “ነጻ ምሣ የለም” ይላሉ ፈረንጆች፡፡ ብዙ ሀብትና ትላልቅ ሥልጣን በተለይ በዚህ አስቸጋሪ ዘመን እንዲሁ ከሜዳ አይገኝም፤ ነፍስህን ገብረህ እንጂ፡፡ የዛሬ ነጫጭባ ድሃ ነገ ሜርሴዲስና ኮብራ ይዞ ካገኘኸው ጠርጥር፡፡ የአዲስ አበባ ፎቆችና ሕንጻዎች ግርጌ ተቆፍሮ ቢታይ ስንትና ስንት የሕጻናትና ቅንድባቸው የገጠመ ምስኪን ዜጎች ዐፅም ይገኛል፡፡ ዝርዝሩ ብዙና ጥልቅ ስለሆነ አሁን ወደዚያ መግባት አያስፈልግም፡፡ ምናለፋህ ጊዜው የሰይጣን ነው ብዬሃለሁ፤ የሚፈልገውን ትሆንለታለህ – የምትፈልገውን ብልጭልጭ ነገር ይሰጥሃል፡፡ በሁለትና ሦስት ዲግሪዎችህ ከ30 ዓመታት በላይ በሁለትና ሦስት የሥራ ቦታዎች ፈግተህ ብስክሌት የሌለህ ሰውዬ እሱ በአንድ አዳር የሚከብርበት የተለዬ ምሥጢር ሊኖር አይችልም፡፡ የዓለምን የሀብት ክፍፍል እናውቃታለን፡፡ በትክክለኛ ድካማችሁ ያለፈላችሁን ሰዎች ግና ይህ አስተያየቴ አይመለከትም፡፡ ለማንኛውም የኢትዮጵያ ሕዝብና ኢትዮጵያ ራሷ በሁለት የሚለያዩ የሚመስሉ በተጨባጭ ግን አንድ በሆኑ የጨለማው ዓለም ምድራዊ አጋፋሪዎች – በወያኔና በኦነግ/ኦህዲድ – የፊጥኝ ታስረው አሣራቸውን እያዩ መሆናቸውን አንርሣ፡፡ 

የሊቀ ሣጥናኤል ዋና ዋና የሚባሉ መገለጫዎች ምን ምን ናቸው?

በነገራችን ላይ አቢይና ሽመልስ በሃይማኖታቸው ፕሮቴስታንት እንደሆኑ ይነገራል፡፡ በተለምዶ “ጴንጤ” የምንለው ይህ የክርስትና እምነት አንዱ ቅርንጫፍ ልክ እንደማንኛውም ቤተ እምነት ሁሉ በሰይጣን የመጠለፍ ዕድል እንዳለው መረዳት አስፈላጊ ነው፡፡ እሱ የማይገባበት የእምነት ተቋም የለም፡፡ ከእስክንድርያ ኦርቶዶክስ እስከ ሮማ ካቶሊክ፣ ከፓትርያርክ እስከ ተራ ዲያቆን በፍቅሩ ጨምድዶ የማይዘው ተቋምና ግለሰብ የለም፡፡ ስለሆነም ከኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ውስጥ ሰይጣንን የሚያገለግሉ የመኖራቸውን ያህል ከጴንጤም ሰይጣንን የሚያገለግሉ እጅግ በርካታ ቸርቾችና ፓስተሮች መኖራቸውን መካድ የለብንም፡፡ ፈራጁ እግዚአብሔር ቢሆንም አቢይ ከነተከታይ ግሪሣው የሚከተለው የእምነት መስመርና ዘማሪ ዶክተር ደረጀ ከበደና ፓስተር ቢኒያም የሚከተሉት የሃይማኖት መስመር አንድ ነው ብባል መቀበል ይከብደኛል፡፡ የነአቢይ ሃይማኖት የሽፋን ነው፤ የማያውቁትን ኢየሱስን በስም እያነሱ ቢጨፍሩ ኢየሱስ ሞኝ አይደለምና ሥራቸውን እንጂ አፋቸውን አያይም፡፡ የእግዚአብሔርን ፍጡር ባልተወለደ አንጀት የሚያርድ የኢየሱስ ተከታይ ሊሆን ፈጽሞውን አይችልም፡፡ ነኝ ቢል እንኳን በማላገጡ ብቻ ፍርድ ይጠብቀዋል፡፡ ክርስቶስ ዘርና ቀለም ሳይለይ ለዓለም ሕዝብ እንደበግ ታረደ፤ አቢይ ደግሞ “አማራና ኦሮሞ፣ ትግሬና አፋር” እያለ በአንዱ ሞት በሌላው ገዳይነት እየተደሰተ እናያለን፡፡ በቀደምለት 200 አማሮች ሲገደሉ አንድም አዘኔታ ሳይኖረው ለአንድ ሞሮኳዊ ሕጻን ሀዘኑን ሲቸር ከማሳቅ አልፎ ጤንነቱን መጠራጠር እንደርሳለን – ለዚያ ልጅ ማዘኑ ትክክል ነው፤ ግን እውነት መሆኑ ያጠራጥራል፡፡ “ለቤት ቀጋ ለውጭ አልጋ” ከዚህ በላይ የለም፡፡ አቢይ ዘመድ ካለው ከዚህም ሳይብስበት ይመርመርና ይታከም፡፡ ታሟል!!

ከፍ ሲል ለማብራራት እንደተሞከረው የሰይጣን መገለጫዎችን በተግባር የሚያሳይ የማንኛውም ሃይማኖት አገልጋይና ተከታይ ምዕመን ሁሉ ክፍሉ የሰይጣን እንጂ የቅዱስ መንፈስ ሊሆን አይችልም፡፡ የሰይጣን ከዳሚዎች በቀላሉ ይታወቃሉ፡፡ ሲጀመር የሰውን ልጅ አንድነትና የእግዚአብሔር (የአላህ) ፍጡር መሆን ይክዳሉ፡፡ ስለሚክዱም ነው በዘር ሐረግ መነሾ በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ካልፈጁ ዕረፍት የሚባል ነገር የማይመኙት፡፡ በፈጣሪ የሚያምን በዘር ልክፍት አይጠመድም፡፡ በፈጣሪ የሚያምን ለሰው ነፍስ ይቅርና ለደቃቃዋ ትንኝ ሕይወትም ይጨነቃል፡፡ በፈጣሪ የሚያምን ወንድማማች ማኅበረሰቦችን በሤራና በተንኮል አያጨራርስም፡፡ በፈጣሪ የሚያምን በሰዎች ዘንድ በተለይም እመራዋለሁ በሚል የአንድ ሀገር ሕዝብ ዘንድ የግርድ እና አመሳሶ ልዩነት በመፍጠር በአንዱ መጨፍጨፍ በደስታ አይረካም፤ በሌላው ማደግና መበልጸግ አይኮፈስም፡፡ በፈጣሪ የሚያምን ለአንዱ መርዝ ለሌላው መድሓኒት አይልክም፡፡ እናም መለስና አቢይ የሰይጣን የባሕርይ ልጆች እንጂ በምንም ዓይነት መንገድ የእግዚእብሔር ልጆች ሊሆኑ አይቸሉም፡፡ የመጨረሻ ዕጣቸውም ዘላለማዊ ጥርስ ማፋጨት ነው፡፡

ጣፋጭ ፍሬ ከዛፉ ላይ ያስታውቃል፡፡

ስለአቢይና ቡድኑ በተለይ አሁን ብዙ ነገር ይታወቃል፡፡ ድብቅ የነበሩ ነገሮች ሁሉ ገሃድ ወጥተዋል፡፡ ከአሁን በኋላ “ሤራ፣ ሸፍጥ ምናምን” የሚባሉ ነገሮች መጠቀስም ያለባቸው አይመስለኝም – የአደባባይ ምሥጢርን ሤራ ማለት አግባብ አይደለምና፡፡ በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው፣ በማኅበራዊውና በወታደራዊው መስክ ምን ምን የመሰሉ ማጭበርበሮችን እንደሚፈጽሙ ግልጽ ሆኗል፡፡ ግልጽ ሊሆን የማይችለው አውቀው ለተደበቁ ውታፍ ነቃዮች ነው፡፡ የአቢይ አሸርጋጆች የሚከተሉትን ጥሬ ሃቆች አያውቁም አንልም፡፡

  • እውነተኛዋ የኢትዮጵያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ በብዙ አካባቢዎች ብትውለበለብ በወያኔ ጊዜ ብዙም እክል አይገጥማትም ነበር፡፡  አሁን ግን ሕይወት እስከማስጠፋት ደርሳለች፡፡ እነዚህ ገልቱዎች በሥልጠና ካምፖቻቸው ውስጥ ምን ተብለው እንደሚሰበኩ አላውቅም የትም ይሁን የትም ይህችን ሰንደቅ ዓላማ ሲያዩ ደማቸው ይንተከተካል – ሕወሓታውያን ጭምር፡፡ የያዘውን ሰው ወይንም በልብሱ ላይ ያስጠለፈን ዜጋ አዋርደውና አንገላትተው ያስወልቁታል፤ ከመኪናም ላይ ሲያዩ ይልጣሉ፡፡ የሌላ ሀገር ሰንደቅ ዓላማ ብታውለበልብ ከፈለግህም ብትለብስ ጉዳያቸው አይደለም፡፡ ጠባቸው ከኢትዮጵያ ጋር ነውና ይህችን ምስኪን ሰንደቅ ዓላማ በአሁኑ ወቅት እያሳደዱ ማቃጠላቸውንና ማዋረዳቸውን በስፋት ተያይዘውታል፡፡ የዚህ ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ዋና ምንጭ ደግሞ ቤተ መንግሥት ነው፡፡ ከቤተ መንግሥት ባይታዘዙ ኖሮ በዚህን ያህል ድፍረት ባልተንቀሳቀሱ ነበር፡፡ የአቢይ አምላኪዎች የማይገባቸው ትልቁ ሀገራዊ ቁም ነገር የትም አካባቢ የሚፈጸም ግድያና ዘረፋ እንዲሁም የንብረት ቃጠሎና ውድመት ካለሽመልስ አብዲሣና ካለአቢይ አህመድ ዕውቅናና ምናልባትም ቀጥተኛ ትዕዛዝ ውጪ የማይፈጸም መሆኑን ነው፡፡ ሽብርና ግድያ የነዚህ ሰዎች ሥልጣን ማስቀጠያና የኦሮምያ ኢምፓየር ምሥረታ ማስፈጸሚያ ሥልት ናቸው፡፡ አልታወቀላቸውም እንጂ ሰዎቹ ለይቶላቸው አብደዋል እኮ፡፡ 
  • ባንዲራን በሚመለከት  የሚገርመው ሌላው እውነታ ደግሞ የሰይጣን ኮከብ ያለበቱ የወያኔ ሥሪት ሰንደቅ ዓላማ ማንም የማይወደው መሆኑ ነው – ከሁለት ያጣ ጎመን ሆኗል፡፡ አቢይም ሽመልስም ደብረፅዮንም … ሁሉም አይወዱትም፡፡ ምክንያቱ እንደሚመስለኝ አንደኛ ኢትዮጵያን ስለሚወክል ኢትዮጵያን ከመጥላት በሚመነጭና ሁለተኛም እነዚያ የፈረደባቸው ሦስት ቀለማት ስላሉበት መሆን አለበት፡፡ በየመሥሪያ ቤቱ ስንታዘብ ይህ ባንዲራ በሥርዓት አይሰቀልም፤ አይወርድም፡፡ በዚያ ላይ ነትቦና ተቀዳዶ ነው የሚታዬው፡፡ ባለቤት የለውም – ልክ እንደሀገሪቷ፡፡ ዛሬ ዛሬ የሚከበረው የየክልሉ ሰንደቅ ዓላማ ነው – ከአማራ ክልል ውጪ በተለይ፡፡
  • ባለፈው ሰሞን በተጀመረው ጦርነት ወያኔን እስከመቀሌ ተከትሎ እጅ ማሰጠት ሲቻል አማራን ለማጥቃትና ሕወሓትን ይበልጥ ለማጠናከር ሲባል ጦርነቱ እንዲቆም መደረጉ – ሊያውም በአማራ ክልል ውስጥ – ለሸር እንጂ ለበጎ አልነበረም፡፡ እንደተባለው ወያኔዎች ከተጠናከሩ በኋላ፣ ፊልድ ማርሻልነትን ጨምሮ በሀገራችን የሌለ ስንትና ስንት ሹመት በከዚህ መልስ ለምድረ ቦቅቧቃ ፈርጣጭ የኦሮሙማ የጦር መኮንን ከታደለ በኋላ፣… ወያኔዎች አቢይ በሚያደርግላቸው ሁለንተናዊ ድጋፍ ታግዘው አፋርን በከፊልና ከአማራም የተወሰኑ ቦታዎችን እንደገና መያዛቸው እየተነገረ ነው፡፡ አማራንና አፋርንም አቢይ መደራደሪያ እያደረጋቸው ነው፡፡ 
  • የኢትዮጵያን መሬት አቢይና አዳነች አበቤ ጠፍጥፈው የሠሩት ይመስል ይህ የኦሮሙማ መንግሥት በተለይ የአዲስ አበባን መሬት ለፈለገው ሁሉ እየጎመደ በመስጠት ላይ ነው፡፡ የኦሮሙማ ጀሌ ከሆንክ አስፋልት መንገድም ይሰጥሃል – ምሣሌ ካስፈለገ ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ (የዱሮው ዓሣ ቤት) ግማሽ አስፋልት ድረስ በግምብ ታጥሮ እየተገነባ ያለ ሕንጻ አለ፡፡ በሌሎች አካባቢዎችም ያለአንዳች ስስት በሽዎች የሚቆጠር ካሬ ሜትር ለኦሮሙማ ባለሀብቶችና የኦሮምያ መንግሥት ድርጅቶች እንደልብ እየታደለ ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ የገረመኝ ግን ለአቶ ግሩም ጫላ የተሰጠው የ5 ሽህ ካሬ ሜትር ቦታ ነው፡፡ አራት በአምስት በሆነች አነስተኛ ክፍል ውስጥ ቢቢሲንና ሲኤን ኤንን የመሰለ የዜና አውታር መገንባትና የሚዲያ ዝግጅትን ማስተላለፍ ሲቻል ለዚህ ሰው የተሰጠው መሬት ግን ለእርሻ አይሉት ለፋብሪካ እጅግ የሚያስደነግጥ ነው፡፡ በዚያ ቦታ ላይ የሚገነባው የባለ63 ወለል ፎቅ ዋና ተግባሩ የሚዲያ ሥራ መባሉ ነው አሰጣጡን ትልቅ ጥያቄ ውስጥ እንድንከተው የሚያደርገን፡፡ ሀገር ተዘርፋ ልታልቅ ነው፡፡ የሚገርሙ ኦሮሙማዎች ናቸው፡፡
  • ሌላው ባንክ ሁሉ በስፖርታዊ ቋንቋ ቤንች ተደርጎ ኦሮምያ ኅብረት ሥራ ባንክ ነው በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱን ገንዘብ እንደፈለገው እያሽቃነጠበት የሚገኘው፡፡ ንግድ ባንክም ብሔራዊ ባንክም በዚህ ባንክ ሥልጣናቸው ተሸሮ ጦጣ ሆነዋል፤ ለነገሩ የሁሉም መሪዎች ኦነጎቹ ማለቴ ኦሮሙማዎቹ በመሆናቸው ለነዚህ የመንግሥት ባንኮች የሚቆረቆር የለም፡፡ በየሚዲያው እንደሚስተዋለው ከሆነ ግን ለመናፈሻ ጉብኝት ሳይቀር ትኬት የሚቆረጠው ከኦሮምያ ኅብረት ባንክ ነው፡፡ ኦ! ኦ! ኦ! ኦሮምያ እጅግ ታድላለች!! ልጅ መውለድ እንዲህ ነው፡፡ በዘረፋና በቅሚያ ቀብራራ ሀብታም ያደርጋል፡፡ በግድያና በእሥር ዴሞክራሲን የሚያጠፋ ልጅ መውለድ ያኮራል፡፡ ታራ ነገራን (ዮሐንስን) አስሮ የሚያሰቃይ፣ አቦይ ስብሃትን (በርባንን) የሚፈታ መንግሥት መደነቅ አለበት፡፡  በርቺ ኦሮምያዬ!!
  • በሦስትና አራት ሚሊዮን ብር የተሠራ የመንግሥት ሕንጻ አሁን ቀለም ለመቀባትና አንዳንድ ነገሩን ለማደስ 2.2 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደረገ ተብሎ ሲነገርም አንዳችም ሀፍረት ፊታቸው ላይ አይነበብም፡፡ አክራሪ የዘረኝነት ልክፍት ሀፍረትና ይሉኝታን አያውቁም፡፡ በሃምሣ ሚሊዮን ብር የዛሬ አምስት ዓመት የተሠራ የአስፋልት መንገድ ዛሬ ባምስተኛ ዓመቱ በብር አንድ እና ሁለት ቢሊዮን ጥገና ተደረገለት ሲባል መስማት የዕንቆቅልሾች ሁሉ ቁንጮ መሆኑ አይቀርም፡፡ አምናና ታችአምና ከኮሌጅ ተመረቀ የተባለ የፌዴራሉን የሥራ ቋንቋ “ሀሁ”ንና ኤቢሲዲን ለይቶ የማያውቅ ቄሮ ዛሬ ላይ ሥራ በያዘ ባመቱ ቪ8 እና ሪቮሉሽን የተባሉ ስማቸውን እንኳን አስተካክሎ የማይጠራቸው ዘመናዊ መኪኖችን ሲነዳ ማየት ከኢትዮጵያ ውጪ የሚታሰብ አይደለም፡፡ ኦሮሞነት የሁሉም ነገር አድራጊ ፈጣሪ ሆኖ ሌላው ቀርቶ ኦሮምኛን አለመናገር የሚያስገድል ደረጃ መደረሱ እየተነገረ ነው፤ በፊት በፊት ከሥራ ያስባርርና ሥራን በማሳጣት ብቻ የተወሰነ ነበር እንጂ እስከዚህ የከፋ አልበረም፡፡ አሁን ግን ነገሮች እጅግ እየጠጠሩ ነው፡፡ ህገ መንግሥት ተብዬውንም እንደፈለጉ የሚጥሱት እነሱው ናቸው፡፡ ወልጋዳውን የወያኔ ህገ መንግሥት እንኳን አያከብሩትም፡፡ ምን ገዷቸው! ማንስ ጠይቋቸው!
  • አዲስ አበባ በአንድ አዳር ወደኦሮሞነት እየተለወጠች መገኘቷ የአደባባይ ምሥጢር ከመሆኑ በተጓዳኝ ነባር ሠፈሮችና ታሪካዊ ቅርሶች እየፈረሱ ከተማዋ መናፈሻ በመናፈሻ እየሆነች ነው፡፡ በመሠረቱ መናፈሻ መገንባት በራሱ ደስ ያሰኛል እንጂ አያስከፋም፡፡ ግን ዓላማው ሲጤን አዲስ አበባን የማጥፋቱና ወደሌላ የባለቤትነት መብት ለመለወጥ ግልጽ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ለመረዳት ፊደል መቁጠርን እንኳን አይጠይቅም፡፡ ፒያሳ፣ አራት ኪሎ፣ ፍል ውኃ፣ ሠንጋ ተራ፣ ልደታ፣ ቡፌ ደላጋር (ባቡር ጣቢያ)፣ አራተኛ፣ ካዛንቺስ፣ እሪ በከንቱ፣ ዶሮ ማነቂያ፣ ቤተ መንግሥት አካባቢ፣ ወዘተ. ቀደምት ነዋሪዎቻቸው ተባርረውና ወደከተማዋ ዳርቻ ተጥለው እነዚህ ቦታዎች የአዳዲሶቹ ባለጊዜዎችና የወያኔዎች መኖሪያና የሥራ ቦታ ወይንም አንዳንዶቹ መናፈሻ እየሆኑ ነው፡፡ አሁን አሁን ደግሞ መናፈሻ በመገንባት ሥራ የተለከፈው ጠ/ሚኒስትር ተብዬ ሕዝቡን ከመኖሪያው እያፈናቀለ አዲስ አበባን ሙሉ በሙሉ የመናፈሻ ሥፍራ ሊያደርጋት ምንም አልቀረውም፡፡ ዜጎች የሚልሱትንና የሚቀምሱትን አጥተው በርሀብ አለንጋ እየተገረፉ፣ በየደቂቃው ሽቅብ በሚወነጨፍ የኑሮ ውድነትም መፈጠራቸውን እየረገሙ፣ በኮቪድ ወረርሽኝ ሕዝብ እየተጨነቀ፣ ቤት ለመሥራትም ሆነ ተከራይቶ ለመኖር አቅም በማጣት ምክንያት በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ወደበረንዳ አዳሪነት እየወጡ፣ … ያለችንን አነስተኛ ሀብት ለሕዝብ እምብዝም በማይጠቅምና ከዚያም ባለፈ ከየመኖሪያው እያፈነናቀሉ ለጅብ በሚያጋልጡ መናፈሻዎች ከተማን ማጥለቅለቅ የጤና አይደለም፡፡ መናፈሻ ዳቦ አይሆንም፤ መናፈሻ የመኖሪያ ቤት ችግርን አይቀርፍም፤ መናፈሻ ድህነትን አይቀንስም፤ መናፈሻ ከሀገሪቱ ዜጎች ሁለት መቶኛ የማይሆኑትን ሀብታሞች ለማስደሰት ካልሆነ በስተቀር 98 ከመቶ በላይ ለሚሆነው ድሃ ዜጋ የሚፈይደው ነገር የለም፡፡ የሚያመዝነው ጉዳቱ ነው፡፡ በዚያ ላይ የመኪና መንገዶችን እየዘጉና መተላለፊያ እያሳጡ ከተማዋን ማጣበብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከአሁኑ ወደባሰ የተመሰቃቀለ ችግር ውስጥ ሊከት እንደሚችል ደናቁርት ኦሮሙማዎች አልገባቸውም፡፡ እነሱ ዛሬን እንጂ ነገን የማየት ችሎታም ሆነ ፍላጎት የላቸውም፡፡ ከተማን በማሸብረቅና የቆሸሸ ገመናን በቀለም በመሸፋፈን የሚወገድ ችግር እንደማይኖር ያዳፈኑት የሚመስላቸው እሳተ ገሞራ ፈንድቶ ሲፈጃቸው ይረዱታል፡፡ “ከተራበ ለጠገበ አዝናለሁ” መባሉ በጣም ትክክል ነው፤ “ካልጠገቡ አይዘሉ፤ ካልዘለሉ አይሰበሩ” የሚለውም ጭምር፡፡ ኦሮሙማዎችን በጥጋብና በዕብሪት የሚበልጥ እንደማይኖር እረዳለሁ፡፡ 
  • “ሁሉን ቢያወሩት ሆድ ባዶ ይቀራል” ይባላል፡፡ ችግራችን ተወርቶ አያልቅም፡፡ ይህ አቢይ የሚባል የዲያቢሎስ ውላጅ ወደ ሥልጣን ከመጣ ወዲህ ያልሆንነው ነገር የለም፡፡ ሁሉ ነገር የጨበጣ ሆኗል፡፡ ውሎ መግባት በስለት ከሆነ ቆዬ፡፡  የዕለት ከዕለት ኑሮ ለብዙዎች የጣር ያህል ነው፡፡ ሞትን የሚመኘው ዜጋ እጅግ ብዙ ነው፡፡ ዐዋቂዎች ወደጓዳ ሲደበቁ ደናቁርት ወደአደባባይ ወጥተው አገር መሪ ከሆኑም ሰነበተ፡፡ የሚሾመው ሁሉ ሲታይ ከዕውቀት የጸዳና በሃይማኖትና በዘር የተመለመለ፣ በዕድሜም ያልገፋ ጮርቃ፣ በልምድና በተሞክሮም ያልበሰለ ለግል ብልጽግና ብቻ የሚሮጥ ኩታራና ውሪ ነው፡፡ አንድ ሰው እንዲሾም ከፈለገ ከሞራል፣ ከመልካም ሥነ ምግባር፣ ከባህል፣ ከእውነተኛ ሃይማኖት፣ ከሀገር ፍቅር ስሜት፣ ከራሮት (ርህራሄ)፣ ከሰብኣዊነትና ከመሳሰሉት ማኅበራዊና ሃይማኖታዊ ዕሤቶች ራሱን ማፅዳት ይኖርበታል፡፡ አንድ ዕጩ የሥልጣን ጥመኛ አቢይ እጁን ወደአፍንጫው ከመስደዱ ሶፍት ወይ መሃረብ ከኪሱ አውጥቶ አፍንጫውን ሊጠርግ ከተሸቀዳደመ ለሥልጣን ብቁ ነው፤ መረገማችን እስከዚህ ነው፡፡ አብዛኛው ተሹዋሚ በትውውቅና በዓላማ ትስስር እንደመሆኑ በዐይን ጥቅሻ ብቻ አድርግ የሚሉትን ምራቅ ሳይደርቅ የሚያከናውን ጭፍን ታዛዥ ነው፡፡ ከንፍሮ ጥሬ እንዲሉ ሆኖ በጣት ከሚቆጠሩ እጅግ ጥቂቶች በስተቀር ማሰብ የሚችል ወደፖለቲካው እንዲጠጋ አይፈቀድለትም …. ቢበቃኝስ፡፡  
Filed in: Amharic