>

በዚህ ውሀ ቅዳ ውሀ መልስ፣አትራፊው ማን ይሆን...? (ዲ ዳግማዊ)

በዚህ ውሀ ቅዳ ውሀ መልስ፣አትራፊው ማን ይሆን…??

ዲ ዳግማዊ

በመጀመሪያው ቀን የአማራ ክልል ለኦሮሚያ ክልል 50 ሚሊየን ረዳ… በሁለተኛው ቀን የኦሮሚያ ክልል ለአፍር ክልል 60 ሚሊየን ብር ሰጠ… በሶስተኛው ቀን የአፋር ክልል ለሶማሌ ክልል 35 ሚሊየን ሰጠ… በአራተኛው ቀን የሶማሌ ክልል ለቤንሻንጉል 40 ሚሊየን ሰጠ… በአምስተኛው ቀን ቤንሻንጉል ለደቡብ ክልል 5 ሚሊየን ሰጠ… በስድስተኛው ቀን ደቡብ ክልል ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 25 ሚሊየን ሰጠ… በሰባተኛው ቀን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መልሶ ለኦሮሚያ ክልል 150 ሚሊየን ሰጠ… በስምንተኛው ቀን የኦሮሚያ ክልል ተመልሶ ዛሬ ለአማራ ክልል 100 ሚሊየን ሰጠ። በመጨረሻ ሂሳቡ ቢሰላ አትራፊው ማን ይሁን…….?
ፈጣሪ በቸርነቱ ይጠብቀን እንጂ ውሀ ቅዳ ውሀ መልስ ነው ነገሩ።
Filed in: Amharic