>

የእዝን እና የደም ካሳ ....!!!! (ዘመድኩን በቀለ)

የእዝን እና የደም ካሳ ….!!!!

ዘመድኩን በቀለ

ኦነግ ሽሜ “… ክቡር ፍሬዘዳንት ይሄ መቶ ሚልዮኑ የወለጋው ነው። እሱም ቢሆን ገና አላለቀም። የሸዋውም ገና አልደረሰልንም። ሂሳብ ሠርተን አልጨረስንም። እንደጨረስን ክፍያውን እንፈጽማለን
ክውብር ፍሬዘዳንት፦ እናመሰግናለን። ግን አላነሰም ሽሜ። ለ2,563 … የታረዱ ዐማሮች፣ ለ1መቶ 45 ሺ… የተዘረፉ ከብቶች፣ ለ68 የተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያናት፣ ለ46 የተቃጠሉ መስጊዶች፣ ለ84 የተቃጠሉ ወፍጮዎች፣ ለ18 የተቃጠሉና ለተዘረፉ የዐማራ መኪኖች 100 ሚልዮን ብር አያንስም ጌታዬ? እ… ?
ኦነግ ሽሜ፦ ወጪ በዛብና ይሌ። ወደፊት እያየን እንጨምራለን። በቅርቡ ዐማራ በብዛት በሚኖርባቸው የኦሮሚያ አካባቢዎች ላይ ያቀድነው ፕሮጀክት ከተሳካ እንጨምራለን። ለጊዜው ግን ይህቺን ያዟት። ትጠቅማለች ብለን ሳይሆን እንዲያው ያው ለአፍ ማስያዢያ፣ ለእንባ ማበሻ፣ ለአንዳንድ ወጪዎች ይሆናችኋል ብለን ነው።
ክውብር ፍሬዘዳንት፦ መልካም ገና ሌላም አስባችኋል ማለት ነው?
ኦነግ ሽሜ፦ አዎ “ጌታ” ቢረዳን “ዋቃ ጉራቻ” ቢያግዘን እንደ ዐቢይና ደመቀ ፈቃድ በተለይ ዐማራ በሚበዛበት በአሩሲ ዞን፣ አሩሲ ስሬ፣ ሁሩታ፣ ጮሌ፣ ጀጁ በከፊል፣ በዚያኛው በኩል ደግሞ መርቲ እና አቦምሳ አካባቢ ትንሽ ፕሮጀክት ቢጤ አስበናል። ሠራተኞችም አስገብተናል። እናም እሱ ከተሳካ እንጨምራለን። ለጊዜው ግን ይህቺን ያዟት። አይዞኝ መበርታት ነው። ፅናቱን ይስጣችሁ።
ክውበር ፍሬዘዳንት፦ አሜን ሽሜ። አሜን። የአዲስ አበባስ መቼ ነው? ወደ ጎጃምስ ብቅ አትሉም ወይ? ጠይቅልን ስላለኝ ነው ህዝቡ።
ኦነግ ሽሜ፦ የአዲስ አበባው ቀኑ አልተወሰነም። አሁን መጀመሪያ ስሟን መቀየር አለብን። ፊንፊኔ ብለን ማወጅ አለብን። ከዚያም ብዙ ነገር ይቀራል። ግን ያው በመሃል ሌላ ክስተት ካልተፈጠረ በቀር አንዘነጋትም። ይከብዳል ግን እንደምንም ለመፈጸም እንሞክራለን። የጎጃሙን ግን ጀምረነዋል። ከጎጃም በፊት ሰላሌ፣ ዓባይ በረሃ ውስጥ ያሉት መጽዳት አለባቸው። እሱን በተሳካ ሁኔታ እየከወን ነው። በእውነቱ ከእናንተ በኩል እስከአሁን ለሥራችን እንቅፋት የሆነም የለም። ለዚህም ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። እናም እያየን አቅም በፈቀደ መጠን ጎጃምንም የፕሮጀክቱ ተቋዳሽ እንዳርጋታለን ብለን እናስባለን።
ኪሊሊሊሊሊው… ጥርርርርር…  የሽሜ ስልክ ጠራ። ሃሎ። አከም ጂርታ። ገለተ ዋቀዮ፣…  ኤ ባርዳሪን ጂራ… ቁማርቲቻ ተበቻቲን ጂራ… ኤ… ሆማ ኢንያዲን… ነምቲቺ ጎዋ ወዪቲ… ከኔፍ። ሚሎዮና ዺባ ቶኮ ከኔፍ። ሆማ ኢንጀኔ። ገመዴቱማ ነራ ፉዸቴ። ዋተካ ኢንዱበኔ። ቶሌ። ነጋቲ። ብሎ ሽሜ ስልኩን ዘጋው። ዐቢቹ ደውሎ እኮ ነው። በሉ ልሂድ ሌላ ጨዋታ አለብኝ። ልዘጋጅ።
“…ሻሎም !  ሰላም !
Filed in: Amharic