>

"አፄ ሚኒሊክ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የፈፀሟቸው አምስት ለማመን የሚከብዱ ዘግናኝ ታሪካዊ ወንጀሎች !!!!!" (ታዴ የማመይ ልጅ)

አፄ ሚኒሊክ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የፈፀሟቸው አምስት ለማመን የሚከብዱ ዘግናኝ ታሪካዊ ወንጀሎች !!!!!
ታዴ የማመይ ልጅ

ስለ አፄ  ምኒሊክ ብዙ ግዜ ጥሩ ጥሩ ነገሮችን ፅፊያለሁ። ነገር ግን ታሪክን ታሪክ የሚያሰኘው ጥሩውንም መጥፎውንም ስናውቅ ነውና አፄ ሚኒሊክ ከሰሩት ጥሩ ነገር ባሻገር የሰሩትን አምስት ታሪካዊ ጥፋቶች ደግሞ እንደሚከተለው በአጭሩ አስቀምጣለሁ ።
1ኛ . በዘር ተከፋፍሎ እርስ በእርስ በፍቅር እየተዋጋና በሰላም እየተገዳደለ ሲኖር የነበረውን ጨዋ ህዝብ በግድ አንድ ሁን ብለው መንግስት መስርተው ያለ ፍላጎቱ በሰላምና በፍቅር እንዲኖር አደረጉት ።
 2ኛ . ቴሌቪዥን የሰይጣን ስራ ስለሆነ እምቢ አላይም ያለውን ስልጡን ብሔር ጦር አዝምተው አዝምተው በፍቅር ከማረኩት ብኋላ ቤተ መንግስት አስገብተው እጅግ ዘግናኝ በሆነ መልኩ ሲኒማ  እንዲያይ አደረጉት !! አቤት የሚኒሊክ ጭካኔ  😭
3ኛ . ከአዲስ  አበባ ድሬዳዋ ድረስ በእግሩ ዘና እያለ ሀገር እያየ ለሶስት ወር ሲጓስ የነበረውን ህዝብ ባቡር የሚባል ነገር አስመጥተው ከአዲስ አበባ ድሬዳዋ  በአንድ ቀን እንዲገባ አድርገውት በእግሩ ወክ እያደረገ እንዳይሄድ ከለከሉት ።
4ኛ . ጣሊያን ኢትዮጵያን ወርሮ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በእኩልነትና በፍቅር እየረገጠ
  ሊገዛ ሲመጣ ሚኒሊክ ግን አይሆንም ብሎ ተዋግቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ በግድ ነፃነት ሰጠ ።
5 ኛ . እህል በድንጋይ እየፈጨ የጣፈጠ ምግብ ሲበላ የኖረውን ብሔር ምንም ሳያስፈቅዱት ወፍጮ የሚባል ማሽን  አስመጥተው ህዝቡ ወፍጮ ቤት ገብቶ እንዲያስፈጭ አደርገውት የዱቄት ብናኝ  የህዝቡ አይን ውስጥ እንድገባ አደረጉ !!!!
ይሄን ሁሉ ጭካኔ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የፈፀሙት ንጉስ ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ ከአንድ መቶ ሰባ አምስት አመታት በፊት የተወለዱ። የንግስተ ሳባ ልጅ ዳግማዊ ሚኒሊክ!
 💚💛❤
Filed in: Amharic