>

ከአድዋ ድል መልስ፣ ለጀግናው ንጉሥ የቀረበ ምወድስ...!!! (አሳፍ ሀይሉ)

ከአድዋ ድል መልስ፣ ለጀግናው ንጉሥ የቀረበ ምወድስ…!!!

አሳፍ ሀይሉ

«ባመጣው ወጨፎ በሠራው እርሳስ
ወቃው አመረተው ያን የባሕር ገብስ
እምዬ ምኒልክ የኢትዮጵያ ንጉሥ፡፡
«ጣሊያን ኮሶ ጭኖ ሸዋን ሊያጠጣው
ገና ሲበጠበጥ ዳኘውን ቀናው፡፡
«ቅዳሜ ተግዞ እሑድ ተበራየ
መስኮብም ገረመው ጣሊያንም ጉድ አየ፡፡
«ምኒልክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይኽን ጊዜ አበሻ፡፡
«ምኒልክ ማለፉን የምትጠይቁኝ
ፊትም አላለፈ ኋላም አይገኝ፡፡
«ዳኘው በዲሞቶር በለው በለው ሲል
የቃኘው መኮንን – ደጀኑን አፍርሶ – ጦር ሲያደላድል
አባተ በመድፉ አምሳውን ሲገድል
ባልቻ በመትረየስ ነጥሎ ሲጥል
እቴጌ ጣይቱ – ዳዊቷን ዘርግታ – ስምዐኒ ስትል
ለቆሰለው ጀግና ውሃ ስታድል
እንዲህ ተሠርቶ ነው የዓድዋው ድል፡፡»
Source:- ከዶ/ር ሥርግው ሀብለሥላሴ፣ «ዳግማዊ ምኒልክ የአዲሱ ሥልጣኔ መሥራች»፣ ገጽ 239ff፡፡ Image: Menelik II King of Kings of Ethiopia, around 1890s.

ምንይልክ – ወደር የሌለህ ጀግና… 💚💛❤!!!

Filed in: Amharic