>
5:08 pm - Monday February 22, 2512

• የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና ሸኔ በምዕራብ ሸዋ በአማሮች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ነዋሪዎች ገለፁ!

• የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና ሸኔ በምዕራብ ሸዋ በአማሮች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ነዋሪዎች ገለፁ!

 • ጥቃት የደርስባቸው በፋኖነት ተፈርጀው ነው፣ ህፃናትን ጨምሮ በየጫካው ተጠልለዋል!

/

የኦሮሚያ መስተዳድር ልዩ  ኃይል እና  ኦነግ-ሸኔ በምዕራብ ሸዋ፣ ዳኖ ወረዳ ቀርቀሮ ጅባት በተባለ አካባቢ የሚኖሩ አማሮችን ከትናንት ሰኞ ሚያዚያ 24 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ጥቃት እያደረሱ መሆኑን ከግድያው የተረፉ አማሮች ተናገሩ።

አማሮችኝ በማንነታቸው ተለይተው የሚጨፈጨፉት በፋኖነት በመፈረጅ እንደሆነም ከሥፍራው የሚገኙ ምንጮች አረጋግጠዋል።

 

በምዕራብ ሸዋ፣ ዳኖ የሚገኙ የአማራ ተወላጆች  የሚደርሰባቸውን ጥቃት በተደጋጋሚ ለመስተዳድሩ፣ ለፌዴራሉ መንግሥት እና ለጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት በደብዳቤ እና በአካል በተላኩ ወኪሎቻቸው አብራርተዋል። ይሁን እንጂ፣ ከጭፍጨፋ የሚታደጋቸው አካል አላገኙም።

ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር  በኩል ከሚወጡ መግለጫዎች ጋር ተያይዞ የዘር ጥቃት እንዳንዣበበባቸው ሲናገሩ ቆይተዋል።

ሆኖም ሰሚ አጥተው እየተጠቁ ይገኛሉ። አሁን ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ተገድለዋል፤ ከፊሎች ቆስለው ወደ ለሕክምና ወደ ጉራጌ፣ ወልቂጤ ከተማ ተወስደዋል።

ከትናንቱ ጥቃት የተረፉ በርካታ አማሮች በየጫካው ተጠልለው ‘ድረሱልን’ እያሉ ነው። በተለይ ሴቶች፣ ሕፃናት፣ አዛውንቶች በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛሉ።

Filed in: Amharic