>

አፋኙን መንግስት እንጠይቃለሁ! ጎበዜ ሲሳይ የት ነው???? (መስከረም አበራ)

አፋኙን መንግስት እንጠይቃለሁ! ጎበዜ ሲሳይ የት ነው????

መስከረም አበራ
አማራ የተባላችሁ ዜጎችንም እጠይቃለሁ ይህ ጎበዜ ሲሳይ የሚባል ቅን ልጅ እንዲህ የሚሆነው ለምን ይመስላችኋል? ጎበዜ ወያኔ፣ኦህዴድ፣ኦነግ፣ የቀድሞው ኢሳት በሉት ግንቦት ሰባት ፊታውራሪዎች “Converge” የሚያደርጉበትን የአማራን ህዝብ በደል የማጥፋፋት ስራ ከመተባበር እምቢ ብሏል። ኢትዮጵያን እንደምወድ ለማረጋገጥ የተወለድኩበት  የአማራ ህዝብ በየአቅጣጫው በሽፍንፍን ሲጨፍጨፍ፣በትንሽ በትልቁ ደባ ሲሰራበት ዝም አልልም ባይ ነው!!!!
 ለራሱ ምንም ሆኖ መኖር ሲችል እናንተ እና እኔ ለወጣንበት ህዝብ እንደ ሰው ተከብሮ መኖር ሲል በባለጊዜዎች የወታደር ጫማ ተረግጦ የገባበት የጠፋውን የእውነት ሰው የት ነው የሄደው የማትሉት እንዴት ነው?????????  ወይስ እንደተለመደው  ከሞተ በኋላ በፎቶው ቲሸርት አሰርታችሁ ለብሳችሁ ፎቶግራፍ ልትነሱ ነው?????
ነገራችን ክብደት ያጣው እኮ የቆሙልንን ሰዎች እንደምንም ስለማንቆጥር  ፣ጀግኖቻችንን አስገድለን ከሞቱ በኋላ ሬሳ መሳሙ ላይ ስለምንረባረብ ነው!!!!!
ጦርነታችሁን የሚዋጋላችሁን ሰው ጉዳይ ቸል አትበሉ ነገ ውጊያችሁ  የሚዋጋ ታጋይ ታጣላችሁ
ምን አዚም ነው ????
ካልተረጋገጡ ምንጮች ይህ መረጃ ይሰማል:-

ዜጎች አሁንም በመንግስት ላይ ጥያቄ ማንሳታቸውን ቀጥለዋል። በተለይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከሕግ ውጪ የሚደረግ አፈናን በተመለከተ በኦሮሚያ ፖሊሶች ላይ ምሬታቸውን እያሰሙ ነው። በለገጣፎ ልዩ ካምፕ የከተመው የኦሮሚያ ፖሊስ ኮማንዶ አዲስ አበባ ዘልቆ ካለፍርድ ቤት ማዘዣ በሕገወጥ መንገድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን እያፈነ የሚወስደው ነገር አነጋጋሪ ሆኗል። በተለይ የአማራ ተወላጆች በየቀኑ እየታፈኑ መሆኑ ታውቋል። ………………. ጥያቄው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በሕይወት አለ ወይስ የለም ነው። ከልክ በላይ ደብድበውት ፊቱ አባብጦ በኦሮሚያ ፖሊሶች ታጅቦ የካቲት ሆስፒታል መቶ እንደነበር የሆስፒታሉ ሰዎች ተናግረዋል። ካሕወሓት የባሰ ጊዜ ላይ ደርሰናል።

Filed in: Amharic