ስንታየሁ ለማ በደቡብ ኢትዮጵያ ለባልደራስ የድጋፍ ፊርማ ሲያሰባስብ ታሰረ!
ስንታየሁ በካራማራ ታስሮ ከተፈታ 3 ሳምንታት ያልሞለው የቀድሞ ዳኛ ነው!
በአካባቢው የድጋፍ ፊርማውን በማሰባሰብ ላይ የነበረው የፓርቲው አባልና የቀድሞ ዳኛው አቶ ስንታየሁ ለማ ዛሬ ቅዳሜ ሚያዝያ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. በጋሞ ዞን፤ ምዕራብ አባያ በፖሊስ ታስሯል። የማስፈረሚያ ቅፆችንም ተነጥቋል።
ስንታየሁ ወደ ቦታው ያቀናው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፓርቲው የፃፈውን የድጋፍ ደብዳቤ በመያዝ ነው። ደብዳቤውን ቢያነብላቸውም ፖሊሶች ከሕግ ውጭ አስረውታል።
ስንታየሁ ለማ የካራ ማራ የድል በዓልን በአዲስ አበባ እንዳያከብሩ ተከልክለውና በአባ ሳሙኤል ወህኒ ቤት ከ40 ቀን በላይ ታስረው በቅርቡ ከተፈቱት የባልደራስ ከባላት መካከል አንዱ ነው።
የስርዓቱ አቀንቃኞች በተቃዋሚዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ሰሞኑን ከጠየቁ በኋላ የባልደራስ አባላት እየታሰሩ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል ቢኒያም ታደሰ፣ ሰናይት ታደገና ሱራፍኤል ታደገ ይገኙበታል። በተጨማሪም ጋዜጠኛ ሲሳይ ጎበዜና በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚኖሩ በርካታ የዐማራ ክልል ተወላጆችም ታስረዋል።