>

ጠቅላይ ሚኒስትሩን የገጠመው አደገኛ ህመም! (ያለለት ወንዳዬ)

ጠቅላይ ሚኒስትሩን የገጠመው አደገኛ ህመም!

ያለለት ወንዳዬ


 

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ የናርሲሲስቲክ የባህርይ ችግር / Narcissistic personality disorder ተጠቂ መሆኑ ከሚያሳየው ባህሪና ከሚናገረው ንግግር ተነስቶ በቀላሉ ለመገንዘብ ይቻላል፡፡ ይህ ህመም አንድ ሰው ራሱን ከፍ አድርጎ እንዲያስብ የሚያደርግ  የጤና እክል ነው።
የናርሲሲስቲክ የባሕርይ ችግር በአብዛኛው በወንዶች ዘንድ በጣም የተለመደ ነው ። መንስኤው ባይታወቅም በጄኔቲክና በአካባቢያዊ ሁኔታዎች የተዋሃደ ሊሆን እንደሚችል የዘርፉ ምሁራን ይናገራሉ፡፡
በዚህ ህመም የተጠቁ ሰዎች ከሚያሳዩት የተለመዱ የሕመም ምልክቶች መካከል  ፦ ራስን ልዩና የሁሉ የበላይ ንጉስ አድርጎ የመቁጠር (ግርማዊነት) ፥ ደንታ ቢስነትና ስሜታዊነት፣ የሌሎችን ስሜት ችላ ማለት፣ ከመጠን በላይ አድናቆትን የመፈለግና ትችትን ወይም ነቀፌታን የመፍራት እንዲሁም መቋቋም ያለመቻል ባህሪይ ይታይባቸዋል፡፡ ፍፁም ራስወዳድና አስመሳዮች ናቸው፡፡ የሚያስጨንቃቸው የክብርና የውዳሴ ፍላጎታቸውን ማርካት ብቻ እንጂ ስለሌላው ደንታቢስ ናቸው፡፡ ” ከሁሉም የበለጥኩና የተሻልኩ ነኝ” ብለው ስለሚያስቡ ራሳቸውን ከሌሎች የመነጠል አባዜም የተጠናወታቸው ናቸው፡፡
ከአለም ታላላቅ  መሪዎች መካከል አዶልፍ ሂትለር ፥ ፍራንክሊን ሮዝቬልት ፣ ሙሐመድ ጋዳፊ ፣ ፖል ፖት ፥ ስታሊንን ጨምሮ አብዛኛዎቹ አንባገነናዊ መሪዎች የዚህ ህመም ተጠቂዎች እንደነበሩ ይገለፃል፡፡
የዚህ ህመም ተጠቂዎች ህመማቸውን ተረድቶ ወደ ህክምና ካልተወሰዱ በስተቀር የሚያደርጉት ፣ የሚናገሩትና የሚወስኑት ሁሉ ብቸኛው ትክክለኛ መንገድ እንደሆነ ስለሚያስቡ አጠናክረው ይገፉበታል እንጂ አይታረሙም ፥ ሌላው ሰው ቢንጫጫና ቢጮህ ለእነዚህ ታማሚዎች ደንታቸው አይደለም፡፡ የሚፈልጉትን ውዳሴና ክብር ከሚያገኙበት መድረክ ፊት እንቅፋት የሚሆንን ሁሉ ያስወግዱታል እንጂ አይራሩለትም፡፡
በሽታው በባለሙያ ምርመራ ተደርጎ ተከታታይና ለረዥም ጊዜ የሚከወን የህክምና ሂደትን ይፈልጋል፡፡ ሕክምናው የንግግር ሕክምናን ጨምሮ የቡድን ቴራፒ ፣ የቤተሰብ ህክምና ፥ የስነልቦና ባለሙያ ምክርን ያካተተ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ስልጣን ከመጣ ጊዜ አንስቶ የዚህ በሽታ ምልክቶች የሚስተዋልበት ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜም እየተባባሰ መጥቶ “እመራታለሁ” ያላትን ሀገር ወደፍርስራሽነት ሊቀይራት እየተንደረደረ ብሎም ህዝቡን ወደ አስከፊ የመከራ አዘቅት ውስጥ እንዲወርድ እያደረገ ይገኛል፡፡
ይህ ሠውዬ! ያለበትን አደገኛ የአዕምሮ ህመም በመረዳት  በጊዜ ከህዝብ ስልጣን ላይ ገለል ካልተደረገ ፥ እመኑኝ! ይቺን ሀገር እየተጨበጨበለት እንዲያፈርሳት እድል እየሰጠነው ነው!
Filed in: Amharic