የአማራ ህዝብ ለማይቀረው ትግል ቆርጦ መነሳት አለበት! እየሞቱ መኖር ይብቃን…!?!
ሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደ ትንሣኤ አባተ
አሁን ጥያቄው የመኖርና አለመኖር ነው። እንጅ የስልጣን ወይም የሀብት ክፍፍል ጥያቄ አይደለም። አብይ አህመድና ብአዴን የሚባል ጠላት እስካሉ ድረስ የአማራ ህዝብ መከራ ይቀጥላል:: የአማራ ህዝብ እየሞተ መኖሩን አቁሞ ለመጨረሻው ትግል ራስን ነፃ የማውጣት ትግል መታገልና መነሳት አለበት:: ያካልሆነ ሂትለር በአይሁድ ህዝብ ላይ የፈፀመው የዘር ፍጅትና ጭፍጨፋ በአብይ አህመድ ቡድን የመጨረሻው ይሆናል። በምድር ላይ የመኖር ዘመኑም ያከትማል። ሀገራችን ኢትዮጵያም በአይሁድ ህዝብ ላይ የተፈፀመውን ፍጅት በአማራ ህዝብ ላይ እየፈፀመችው ትገኛለች። ህዝቡ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ከሚል ከተደገመበት አዚም ወጥቶ ሴት ወንድ ሳይል ለህልውናው ለነፃነቱ መታገል አለበት። በመጀመርያ በምድር ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን የመኖር መብቱን ማረጋገጥና ነፃ መውጣት አለበት:: ነፃ ያልወጣ በሞት ጥላ ውስጥና በመሞት ሀገር ውስጥ የሚኖር ህዝብ ሀገር የለውም። አባቶቻችን የሞቱላት ኢትዮጵያ ዛሬ የለችም:: ለሰላሳ ዘመን አማራውን በልታለች:: አማራ የከፈለላትን ውለታ እንደመርገም ጨርቅ ቆጥራዋለች። የአማራ ህዝብ እንደጠላት ከተቆጠረ በመላ ሀገሪቱ ባይተዋር ከሆነ መሞት ከጀመረ ሰላሳ አመት ቢሞላውም; ቢሳደድ ቢገደልም ባለ ማለቁ አሁንም መከራውና ስቃይ በአብይ አህመድ የፍጅት አዋጅ ታውጆበታል:: እንደ በግ እየታረደ ይገኛል:: አማራ ከአብይ አህመድ አሰልች ቃልና ከተላላኪዎቹ አዚም ወጥቶ ከጠላት ብአዴን ኮፈን ውስጥ ተላቆ በዚህ ወቅት ሙስሊም ክርስቲያን ሳይል የውስጥ አንድነቱን አጠናክሮ ወደ ትግል መግባት ግድ ነው። ቄስ መነኩሴ ; ሸሕ የሚባል የለም:: ትግሉ የመኖርና ያለመኖር የነፃነት ትግል ነው። አማራ አንድ ሁኖ ካልቆመ ወደ ትግል ገብቶ የአብይ አህመድን መንግስት ካልሻረ የአማራ ህዝብ እርድ ባለበት ይቀጥላል:: በየትኛው ዓለም የነፃነት ታጋይ እንደ ፅድቅ እንጅ እንደ ኃጢያት አይቆጠርም በዚህ ወቅት መግለጫም ማውጣቱ ; ሰላማዊ ሰልፍ
መሰለፉን ጋብ አድርገን በየተኛውም መስመር ታግለን የአብይ አህመድን መንግስት ማስወገድ ያስፈልጋል ይህ ሊሆን ግድ ነው።
ወጣት ሴት ወንድ ሳይል ለነፃነት መታገል አለብን:: አብይ አህመድ ከግብፅ ፈርዖናውያን; ከባቢሎኑ ናቡከደነፆር; ከሮማ ቄሳሮች ; ከድዎቅርጥያኖ
እና ከጀርመኑ ሂትለር የከፋ የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን መጥፎና ክፉ ሀኪተኛ ነፍሰ በላ ወልደ ኃጉል ሰው ነው::
ከዚህ አዚማም ጠባብና ዘረኛ አገዛዝ ወጥተን ሁሉም ለነፃነት በያለበት ትግል አድርጎ ነፃ መውጣት ኢትዮጵያንም ነፃ ማውጣት ይጠበቅብናል:: ፍትህ በሌለበት በአብይ አህመድ የፍርድ አደባባይ ፍትህ መጠየቅ እራስን ማታለልና የሞት ዘመንን ማራዘም ነው እላለሁ።
የሞቱትን በግፍ የተጨፈጨፉትን ወገኖቻችንን ለሙስሊሞቹም ለክርስቲያኖቹም እረፍተነፍስ ይስጥልን።