>

አለም በአሸባሪነት የፈረጀው ቡድን መፍትሄ ሊሆነን አይችልም...!!! (የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ማህበር)

አለም በአሸባሪነት የፈረጀው ቡድን መፍትሄ ሊሆነን አይችልም…!!!

የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ማህበር

*…. ታላቁ ሃይማኖት እስልምና የኦነግ ዓላማ ማስፈፀሚያ እንዳይሆን ከፍተኛ ስጋት አለን…!!!

ከ2010 ጀምሮ ባለፉት 4 አመታት ለነባሩ እስልምና ጋሬጣ ሆነው የገጠሙን ፈተናዎች ድብዝዝ ብለው  ግራ የሚያጋቡ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ሁሉም ነገር ግልፅ ሆኗል። መንግስት ሀገር ሲቀና አብሮ የኖረውን ነባሩን እስልምና አሳልፎ ለመጤው ወሃቢዝም ይሰጣል ብለን ባለማመን ብዙ ህገወጥ ተግባራት ሲፈፀሙ ችለን አሳልፈናል። ችግር በተፈጠረ ቁጥር ታገሱ ችላችሁ እለፉ ሀገር ጦርነት ላይ ነች፣ አሁን ኮቪድ አሁን ምንትስ ነው እየተባለ መሻይኾቻችን ሲደለሉ የነበረው ወሃቢዝምን በዘር ፖለቲካ በማጠን መጅሊሱ ላይ ለማንገስ ምቹ ሁኔታ እየተጠበቀ እንደነበር አሁን ግልፅ ሆኗል።

ነባሩ ሙስሊም ማህበረሰብ መንግስትን አምኖ ሰላማዊነቱን ጠብቆ ህግ አክብሮ ሀገር ከንጭቅ ትለፍ ብሎ ችግሮችን በትእግስት ለማስኬድ በፍፁም ቅንነት የተጓዘ ቢሆንም ከብልፅግና መንግስት የተሰጠው ምላሽ ግን ክህደት ሆኗል። ነባሩ ሙስሊም ለ14 ክፍለ ዘመናት ብዙ መስዋእትነት  ከፍሎ የመሰረተውን ተቋም ለመጤ እና ከ30 ዓመት የዘለለ እድሜ ለሌለው ዓለም አቀፍ ሽብርተኞችን በማፍራት ለሚታወቀው ወሃቢዝም አሳልፎ ሰጥቷል። በዚህም ህዝባችን እጅጉን አዝኗል በከፍተኛ የቁጣ ስሜት ውስጥም ይገኛል።

የደረሰብን ክህደት እና ጭቆና እጅግ ከስሜት ቁጥጥር ውጭ የሚያደርግ ቢሆንም አሁን ላይ ህዝበ ሙስሊሙ ማድረግ ያለበት:— ባለበት መረጋጋት፣ በመንግስት የተወሰነው ውሳኔ ህገ ወጥ እና ህገ መንግስቱን በግልፅ የሚፃረር፣ መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ በግልፅ መግባቱን  ለኢትዮጵያና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳወቅ ቀዳሚው ሥራችን ነው።

ነባሩ ሙስሊም መሪ አለው።  የሚመራው በመሻኢኾቻችን እና ዑለሞቻችን ነው። መሪ የሌለን ህዝብ አይደለንም። ከመሻይኾቻችን  ጋር በጋራ በመሆን ቀጣይ መሆን ያለበት ምንድን ነው ሚለውን በተረጋጋ መንገድ ምክክር እያደረግን ዑለሞቻችን የሚወስኑትን እና የሚያስቀምጡትን አቅጣጫ ለህዝባችን የምንገልፅ በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙ በትእግስት እንዲጠብቅ እናሳስባለን።

በተጨማሪም አንዳንድ የማሕበራዊ ሚድያዎች ላይ ለፊታችን ጁመዓ ሀገር አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ በየመስጂዱ ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ  ከመሻኢኾቻችን ጋር ምንም አይነት ምክክር ያልተደረገበት በመሆኑ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ በመሪዎቻችን ዑለማዎች እና መሻኢኾች የተጠራ ሰልፍ አለመኖሩን መታወቅ አለበት።

ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ የተቃውሞ መርሃ ግብር ሲኖር በግልፅ የምናሳውቅ ይሆናል። መሪ እንደሌለው ህዝብ ጠላቶቻችን በሚያዘጋጁልን ወጥመድ ዘለን ዘው አንልም። ማንነቱ የማይታወቅና ኃላፊነት የማይወስድ አካል በሚጠራው በየትኛውም አይነት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ባለመሳተፍ እየተሴረብን ያሉ ሸሮችን መከላከል ይገባናል።

በዚህ ሰአት ተቃውሞ ሊጠሩ የሚችሉ አካላት 3 ናቸው።

1) በቅን እሳቤ የመሻይኾቻችን መታሰር የተቋማችን መደፈር አሳስቧቸውና አስጨንቋቸው የሚገኙ የመስመራችን ልጆች ሊሆኑ ይችላሉ ሆኖም ግን መሪ እንደሌለው ህዝብ ከዑለማ ጋር ምክክር ሳይደረግ ህዝባችንን ለአደጋ የሚያጋልጥ የተቃውሞ ጥሪ ከማስተላለፍ መቆጠብ ይገባናል።

2) ወሃቢ/ኢኽዋኖች ለሱፍያው ማህበረሰብ ተቆርቋሪ መስለው ተቃውሞ በመጥራት፣ አሁን ላይ ጥርሱን አግጥጦ ሊነክሰን ከተዘጋጀው  የታጠቀ ኃይል ጋር ህዝባችንን በማላተም ግጭት እንዲነሳ በማድረግ ትግላችንን ለማጠልሸትና መሪዎቻችንን ለማስወንጀል ነጥብ ለማስቆጠር የታለመበትም ሊሆን ይችላል።

3) የመንግስት ተላላኪዎች ሰላማዊ ትግላችንን ለማጨናገፍ፣ መሪዎቻችን በህግ ተጠያቂ ለማድረግና ለመወንጀል ነጥብ ለማስጣል ሆን ብለው ግጭት እንዲነሳ በማድግ ሴራ ሊሸርቡብን ስለሚችሉ እያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን የተጠና ጊዜና ቦታውን ያገናዘበ መሆን ግድ ይለናል።

ስለሆነም በመላው ዓለም ላይ ያላችሁ የመሻኢኽ እና የዑለሞቻችን ደጋፊዎች የሆናቹ የነባሩ ሙስሊም ተከታዮች በጠቅላላ በያለንበት ከዚህ በፊት እንደምታደርጉት በመረጋጋት በዱዓ እና ያሲን በመቅራት ለሀገራችንም ይሁን ለዲናችን ወደ አላህ በመዞር ከአላህ መፍትሄ እየጠየቅን በትዕግስት እንደ ቀድሞ መሻኢኾቻችን ታሪክ እንስራ።

እየደረስብን ያለውን መንግስታዊ ጫና፣ በግድ ወሃቢዝምን የማጥመቅ ዘመቻ፣ የተቋም ነጠቃ፣ ታሪካችንን የማፍረስ ሂደት፣ የመሻኢኽና የወጣቶቻችን ያለ ወንጀል መታሰር፣ መድሎና የተረኝነት ግፎች ለዓለም አቀፍ ሚድያዎች፣ ለኤንባሲዎች፣ ለዓለም አቀፍ ተቋማትና፣ ለዓለም መንግስታት በማሳወቅ ትግላችንን እናጠናክር። ትግል ተቃውሞና ሰላማዊ ሰልፍ ብቻ አይደለም። አሁን የሚድያ ጦርነት አንዱና ዋነኛው ነው። በተለያየ ቋንቋ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መንግስት በሃይማኖታችን በግልፅ ጣልቃ በመግባት ሿሚ ሻሪ እየሆነ ያለበትን ሁነት እናሳውቅ።

ፍትህ በመንግስት ደህንነቶች ማዋከብ እና ጭቆና ለሚደርስባቸው መሻኢኮች እና ዑለማዎች!

ታላቁ ሃይማኖት እስልምና የኦነግ ዓላማ ማስፈፀሚያ እንዳይሆን ከፍተኛ ስጋት አለን…!!!

*…. አንድነት ለካ ማታለል ማሞኘት  ነው ፤ መጅሊሱ ውስጥ የገቡት ለውሸት ለክህደት ነው

ተቀዳሚ ሙፍቲህ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ የተባሉት ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የኦነግ መሪን ከኋላ አጅበው ሲከተሉ ይታያሉ ።

“ኢትዮጵያ ተፅዕኖ ፈጣሪ እንዳትሆን እናደርጋታለን” በማለት እየሰራ ያለው እና ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ቅርርብ ያለው አህመዲን ጀበል ወደዚህ ሃላፊነት እሳቸው እንዲመጡ እንዳደረገ የሚታወቅ ነው ።ታላቁ ሃይማኖት እስልምና የኦነግ ዓላማ ማስፈፀሚያ እንዳይሆን ከፍተኛ ስጋት አለኝ ።

ከኦነግ ተከታይ ውጭ ያሉ ሙስሊሞች ነገሮች መልካቸውን መቀየራቸውን ባስተዋሉ ጊዜ ራሳቸውን ከኢትዮጵያ እስልምና ጉባኤ ሊያገሉ ይችላሉ ብዬ እሰጋለሁ ።

የአብይ አህመድ ኦህዴድ መንግስት ከነ አህምዲን ጀበል ጋር ሆኖ እኝህን ታላቅ አባት አንስቷቸዋል:: ስልካቸውን ተነጥቀው የቁም እስረኛ እንደተደረጉ እየተሰማ ነው::

እነ አብይ ጣልቃ ሳይገቡ ሙስሊሙ ማህበረሰ ራሳቸው ያላቸውን ልዩነት ፈተው የራሳቸውን እመራር እንዲሽሙ ማድረግ ነበር የሚገባው:: አሁን የታየው የዋሃቢ ሳላፊስቶች hostile takeover ግን የባሰ ችግር እንጂ የሚያመጣው ሰላም ያመጣል የሚል እምነት የለኝም::

ትግላችን ረጅም ሰላማዊነት መለያችን ነው!!!

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid021nJd77FADx6zoi4az29CP6b5Vt6zJ69ZW1Goh4uvmV8H56q8Z8XodankyDjxgejYl&id=100058666369421

Filed in: Amharic