>
5:21 pm - Saturday July 20, 9061

እግር መሳም፤ የጭራቅ አሕመድ እግር መዘርጠጫ ዘዴ

እግር መሳም፤ የጭራቅ አሕመድ እግር መዘርጠጫ ዘዴ

    ጭራቅ አሕመድ ያንቶኒ ብሊንከንን (Antony Blinken) እግር ስሜ ባማራ ሕዝብ ላይ የምፈጽመውን ጭፍጨፋ አሜሪቃ በገሃድና ሙሉ በሙሉ እንድትደግፈኝ አደርጋለሁ ብሎ መዛቱን የሚገልጽ ዜና በቅርቡ ተዜንኗል።  ላስተዋይ ሰው ግን የጭራቅ አሕመድ እግር መሳም የቅርብ ዜና ሳይሆን ያምስት ዓመት የመሠሪነት ዝና ነው።  ለኖቤል ሽልማት የበቃውም በዚሁ እግርን የመሳም የመሠሪነት ዝናው ነው፣ የኢሳያስ አፈወርቂን እግር ስሞ።  እግር የሚስመው ደግሞ እግር ተሳሚውን በማስደምም አደንዝዞ እግሩን ዘርጥጦ ለመፈጥፈጥ ሲልና ሲል ብቻ ነው።    

ጭራቅ አሕመድ ዶክተር አምባቸውንና ጀነራል አሳምነውን ጨምሮ አያሌ ጉምቱ አማሮችን እየዘረጠጠ የፈጠፈጣቸው እግራቸውን እየሳመ በማስደመም ካደነዘዛቸው በኋላ ነው።  የጭራቅ አሕመድ እግርን ዘርጥጦ ለመጣል እግርን መሳም፣ ይሁዳ ክርስቶስን አጋልጦ ከሰጠበት የይሁዳ መሳም (Juda’s kiss) ከሚባለው ክስተት ጋር በተወሰነ ደረጃ የሚመሳሰል ሲሆን፣ በሚከተለው ምሳሌ ሊብራራ ይችላል።  

ማናቸውንም አጋጣሚ ካገኘ ሊገድልህ ቁርጥ ውሳኔ የወሰነ፣ ካልገደልከው የሚገድልህ የመረረ የሞት ሽረት ጠላት አለህ እንበል።  ይህ የሞት ሽረት ጠላትህ ደግሞ ባንድ ወቅት እጅህ ላይ ወደቀና ልትገድለው ተነሳህ እንበል።  ልትገድለው ስትነሳ ግን እግርህ ሥር ወድቆ እግርህን በምላሱ እየላሰ፣ በእንባው እያራሰ ራሱን አለቅጥ በማዋረድ እንዳትገድለው ይለማመጥህ ጀመር እንበል።  ይህ የሞት ሽረት ጠላትህ በዚህ ደረጃ ራሱን በራሱ ሲያዋረድ ስታይ በድርጊቱ አለቅጥ በመደመም አለቅጥ ትፀየፈውና ፊትህን ከሱ ስታዞር እንደሚገድልህ በርግጠኝነት እያውክ ፊትህን ከሱ ታዞራለህ።  እሱም ፊትህ ስታዞርለት ማጅራትህን ብሎ ይገድልሃል።  ጭራቅ አሕመድ አያሌ ጉምቱወችን የገደለውና ያመከነው በዚህ መንገድ ነው።  ባጭሩ ለመናገር ጭራቅ አሕመድ ማለት ስታፈጥበት የሚጥመለመል ስትዞርለት የሚናደፍ ዐሲል ዕባብ ማለት ነው።  

ለምሳሌ ያህል ጭራቅ አሕምድ የተዋሕዶን ዐብዮት አክሽፎ ተዋሕዶን ከሞት አፋፍ እንድትደርስ ያበቃት በዚሁ የመለማመጥና የመናደፍ ዘዴው ነው።  ተዋሕዶ ሐይማኖት በሕልውናዋ ላይ የመጣባትን ጭራቅ አሕመድን ለመቆራርጥ፣ አማኞቿን በነቂስ አነሳስታ፣ ሰይፏን ካፎቱ አውጥታ በጭራቁ ላይ አቃጣችበት፡፡  ጭራቅ አሕመድ ደግሞ በተዋሕዶ ሰይፍ ሊቆራርጥ መሆኑን አውቆ፣ በፍርሃት እየራደ ተዋሕዶ አባቶች እግር ሥር ወድቆ ጫማቸውን በምላሱ እየላስ በእንባው ያርስ ጀመር።  የተዋሕዶ አባቶች ደግሞ ያገር መሪ ቀርቶ ተራ ግለሰብ ያደረገዋል ተብሎ በማይታሰበው በጭራቁ ያልተለመደ ድርጊት ከመገረም አልፈው በመደመም ከወደቀበት ሊያነሱት ጎንበስ ብለው እጃቸውን ዘረጉለት።  ጭራቁ ግን የተወሕዶ አባቶች እሱን ለማንሳት የዘረጉለትን እጅ ስቦ መሬት ላይ በግንባራቸው ፈጠፈጣቸው።  እነሱ ከግራቸው ሊያነሱት ሲሞከሩ እሱ እግሩ ሥር ጣላቸው።  እግሩ ሥር ከጣላቸው በኋላ ደግሞ እግራቸው ሥር እንዲወድቅ በማድረጋቸው የያዘባቸውን ከፍተኛ ቂም በከፍተኛ ደረጃ ተወጣባቸው፣ አለቅጥ አዋረዳችው።  

አቶ ዳንኤል ክብረት እየሱስን ባይኔ በብረቱ አየሁት ያለው፣ ጭራቅ አሕምድ የተዋሕዶ አባቶችን እግር በምላሱ እየላስ በእንባው ሲያብስ አይቶ ነው።  አቶ ዳንኤል ያላወቀው ይልቁንም ደግሞ አውቆ እንዳላወቀ የሆነው ግን የጭራቅ አሕመድ ዓላማና የእየሱስ ዓላማ ሐራምባና ቆቦ (ፍፁም ተቃራኒ) መሆናቸውን ነው፣ ዱባና ቅል እየቅል እንዲሉ።  እየሱስ የሐዋርያወቹ እግር ያጠበው ትሕትናን ሊያስተምራቸው ነበር።  ጭራቅ አሕመድ ተዋሕዶ አባቶች እግር ሥር የወደቀው ግን፣ ሊያነሱት እጃቸውን ሲዘረጉለት፣ የዘረጉለትን እጆች ስቦ በግንባራቸው ለመፈጥፈጥ ነው።  

ስለዚህም ጭራቅ አሕመድ እየሱስ ሳይሆን የእየሱስ ፍፁም ተቃራኒ ዳቢሎስ ነው።  በመሆኑም አቶ ዳንኤል ክብረት ባይኑ በብረቱ ያየው እየሱስን ሳይሆን ዳቢሎስን ነው።  የሚያገለግለውም እየሱስን ሳይሆን ዳቢሎስን ነው።  በመሆኑም አቶ ዳንኢል ክብረት ደቀየሱስ ሳይሆን ከቤተክሲያን ቅጽር መባርር ያለበት፣ ጊዜው ሲደርስ ደግሞ የዳቢሎስ አገልጋይ በመሆን ለፍጸመው ወንጀል ከጌታው ከዳቢሎሱ ከጭራቅ አሕመድ ጋር ባንደነት ተጣምሮ፣ በፍንጅ (handcuff) ታስሮእጅ እግሩ ተጠፍሮ፣ መሬት ላይ ተዘርሮ፣ በዲንጋ ተወግሮ ፍጹም ሞት መሞት ያለበት ደቀዳቢሎስ ነው።  

የተዋሕዶ አባቶች የሠሩት ትልቅ ስህተት ደግሞ ዳቢሎሱ ጭራቅ አሕመድ ተዋሕዶን ለማጥፋት ሲነሳ ሲመለከቱ፣ ለመዕምናቸው ዘወትር የሚሰብኩትን የሰይፈኛውን የቅዱስ ሚካኤልን ወይም ደግሞ የፈረሰኛውን የቅዱስ ጎርጊስን ገድል ባለመፈጸም ነው።  እነዚህ የተዋሕዶ አባቶች ተዋሕዶን ከዳቢሎሱ ከጭራቅ አሕመድ በቀላሉ ማዳን ይችሉ የነበሩት፣ መዕምናዊ ኃይላቸውን ፈርቶ በመንቀጥቀጥ እግራቸው ሥር ሲወድቅ፣ በተዋሕዶ አባትነታቸው በታጠቁት የሥላሴ ሠይፍ አንገቱን ቀንጥሰው በመጣል በወደቀበት ማስቀረት ነበር።  እነሱ ግን አጉል ይቅርባይ በመሆን ዳቢሎሱን ከግራቸው ሥር ሊያነሱት ሲሞከሩ ዳቢሎሱ እግሩ ሥር ጥሏቸው፣ እነሱ ወድቀው ተዋሕዶን ይዘው ወደቁ።  ስለዚህም ጭራቅ አሕመድ በተዋሕዶና በመዕምኖቿ ላይ እያደረሰው ላለው አርማጌዶናዊ ጥፋት ዋናወቹ ተጠያቂወች ራሳቸው የተዋሕዶ አባቶች ናቸው።        

የተዋሕዶ አባቶች የሠሩትን ትልቅ ስህትተ ደግሞ ያማራ ፋኖ መድገም የለበትም። ጭራቅ አሕመድ ለድርድር የሚነሳው ሊሸነፍ መሆኑን ሲረዳ ብቻ ነው።  የሚደራደረው ደግሞ ሰጥቶ በመቀበል ለመስማማት ብሎ ሳይሆን፣ ሊያሽንፈው የተቃረበውን ኃይል በድርድር ሰበብ እየተለማመጠ ካዘናጋ በኋላ ድባቅ ለመምታት ሲል ብቻ ነው። ስለዚህም ማናቸውም ግለሰብም ሆነ ቡድን ከጭራቅ አሕመድ ጋር እደረደራለሁ ብሎ የተነሳ ቀን፣ ቀብሩን መማስ መጀመሩን ሊያውቅ ይገባል። 

በተለይም ደግሞ ፋኖ ሆይ ከጭራቅ አሕመድ ጋር ለመደራደር የተነሳህ ቀን፣ ቀብርህን መማስ መጀመርህን እወቀው።  ያማራ ሕልውና ትግል አመራሮች እውነትም የሚታገሉት ላማራ ሕልውና ከሆነ፣ የሚከተሉትን ሁለት ቅድመሁኔታወች (preconditions) ባላስቀመጠ በማናቸውም ድርድር ውስጥ አንገታቸው ቢቆረጥ መሳተፍ የለባቸውም።  የመጀመርያው የድርድር ቅድመሁኔታ የጭራቅ አሕመድ በላዔ አማራ መንግሥት ሙሉ በሙሉ መገርሰስና ሙሉ በሙሉ መፈራረስ ሲሆን፣ ሁለተኛው የድርድር ቅድመሁኔታ ደግሞ ጭራቅ አሕመድና ግብራበሮቹ (በተለይም ደግሞ ደመቀ መኮንንተመስግን ጡሩነህሰማ ጡሩነህአበባው ታደሰይልቃል ከፋለ እና የመሳሰሉት ብአዴናዊ ግብራበሮቹ) ባማራ ሕዝብ ላይ ለፈፀሙት ወንጀል አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተው ዘላለማዊ መቀጣጫ መሆን ነው።

     መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic