>

የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት የአዲስ አበባን ህዝብ በስብዓዊ ጋሻነት ይይዛል!!! ምጽዐተ ኦሮሙማ!

ፋኖ አዲስ አበባ ከመግባቱ በፊት፣ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ፊንፊኔ ይገባል!!! እንደ ቂጣ የሚገላበጡ መናጆ ፖለቲከኞች!!!  

ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)

የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት የአዲስ አበባን ህዝብ በስብዓዊ ጋሻነት ይይዛል!!! ምጽዐተ ኦሮሙማ!

የዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ የኢትዮጵያን የመከላከያ፣ ደህንነትና የዲፕሎማሲዊ ሥራ በበተባበሩት አረብ ኢምሬትስ መንግሥት ቁጥጥር ስር መውደቁ እሙን ሆኖል፡፡ ኢምሬትስ  የምሥራቅ አፍሪካን ስትራቴጅካል አመራር በመስጠት፣ የቀይባህርን አጀንዳ በመቅረጽና በማራገብ፤ የሶማሌላንድ የወደብና የባህር በር ስምምነት በማቀነባበር ከፍተኛ የፖለቲካ ሴራ የሚሸረበው በአሜሪካን ግጭት ጠማቂነትና የሥነህዝብ ቅነሳ መር ፕሮጀክት በተለይ  የአፍሪካ ህዝብን በጦርነት ቅነሳ አረንጎዴ መብራት ሰጭነት፣ በሼክ መሃመድ ቢን ዛአይድ አል ናህያን አመራር፣ ገንዘብ ሰጭነትና  ኮነሬል አብይ አህመድ አስፈጻሚነት የሚከናወን ሚስጢራዊ ግንኙነት የተቆቆመ ቅጥረኛ ካንፓኒ የአፍሪካን አህጉር በመበጥበጥ ላይ ይገኛል፡፡ የኮነሬል አብይ አህመድ መንግሥትን በገንዘብ ፣ በመሣሪያና በደህንነት ጉዳይ አማካሪና በሃገራችን እጣ ፈንታ ፈላጭ ቆራጭ የፖለቲካ ሴራ በመንደፍ ኤምሬትስ ከፍተኛ ድርሻ አላት፡፡ 

ዶክተር ፀጋዬ አራርሳ፡- በኩሽ ሚዲያ ኔትወርክ ‹‹ በደመ ነፍስ ያለው የብልጽግና ስርዓት›› በሚል ርዕስ በአዘጋጁ ሀብታሙ ተስፋዬና በዶክተር ፀጋዬ አራርሳ የተደረገ ውይይት በማድመጥ የተቀነባበረውን የፖለቲካ ሴራ መረዳት ይቻለናል፡፡ ዶክተር ፀጋዬ የኮነሬል አብይ አህመድ መንግሥትና የዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ መኃል ያለን ሚስጢራዊ ግንኙነት ዶክተሩ አብራርተዋል፡፡ ዶክተር ፀጋዬ አራርሳ አንደበት ‹‹ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) በሚቀጥለው ሁለት ሳምንት አዲስ አበባ ይገባል፡፡ ኦነሠ አዲስ አበባን ከመቶ ኪሎ ሜትር ራድየስ ርቀት ላይ ኮነሬል አብይ ህልውናውን ማስጠበቅ አልቻለም፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከፍንፊኔ ሠላሳና አርባ ኪሎሜትር  ርቀት ላይ ይገኛሉ፡፡ የአራት ኪሎው የአብይ ቤተ-መንግሥት በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የመድፍ ላንቃዎች ቁጥጥር ሥር ይገኛል፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በቅርብም አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡ ›› ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ህዝብ በስባዓዊ ጋሻነት (Human Shields) ተይዞል በአንድ በኩል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና የአዲስ አበባ አስተዳደር የሸገር ከተማ  ህዝብን ሳያማክር መመሥረት፡፡ የሸገር ከተማ ኩታ ገጠም መሬት 1600 (አንድ ሽህ ስድስት መቶ) ስኩየር ኪሎሜትር  ስፍት ሲኖራት በውስጦም ስድስት ክፍለ ከተሞች ሰበታ፣ ቡራዩ፣ ለገጣፎ፣ለገዳዲ፣ ሱሉልታ፣ ገላን፣ እና መናገሻ ይካተታሉ፡፡ ከእላይ በስዕሉ እንደሚታየው የሸገር ከተማ አዲስ አበባን እንደ ስበሰዓዊ ጋሻነት ዙሪያዎን ከበዋታል፣ ኦህዴድ ብልጽግና አንዴ ውኃ እቆርጣለሁ፣ አንዴ ከርስና ፈርስ፣ አንዴ በሰበሩብን ቦታ ሠበርናቸው ወዘተ እያሉ የአዲስ አባባን ህዝብ ያስፈራራሉ፡፡  በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ህዝብ  ኦሮሞ መጣልህ እያሉ አንዴ ኮነሬል አብይ ከሱሉልታ፣ከለገዳዲ የኦሮሞ ፈረሰኞች መንግሥታችን ተነካ ብለው ሊያስነኩት ሲሉ ይለናል፣ አንዴ አዳነች አቤቤ ቤቶች ስታፈርስና ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ ስታፈናቅል፣ አንዴ ሽመልስ አብዲሳ የሸገር ከተማ ኬኛ፣ የጫካ ፕሮጀክት ቤተ-መንግሥት ኬኛ እያለ ህዝቡን በስባዓዊ ጋሻነት አግተውታል፡፡  የአዲስ አበባ ህዝብ በስባዓዊ ጋሻነት በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) ከተያዘ እጣ ፈንታው ምን ይሆናል፡፡ ኮነሬል አብይ አህመድ አዲስ አበባ በፋኖ የአማራ ሠራዊት ከምትያዝ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብትያዝ የኦሮሞ መንግሥት ይቀጥላል የሚል ጽኑ እምነት እንዳለው ይታወቃል፡፡ የፋኖ የአማራ ሠራዊት ወደ አዲስ አበባ የሚያደርገው ግሰጋሴና  የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ወደ ፊንፌኔ ከተማ ግስጋሴ የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥትን ለመጣል ከሆነ በጋራ ፖለቲካ ፍኖተ-ካርታ አዘጋጅቶ መወያየት ከወዲሁ አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡ በሁለቱ ቡድን ጦርነቱን ማስቀረት የሚቻለውና በኮነሬል አብይ መንግሥት ላይ የጋራ ግንባር ፈጥሮ መዋጋት የአብይን መንግሥት ይቀጨዋል፡፡  ፋኖ የአማራ ሠራዊት የትግል የድጋፍ ጥሪ ማስተላለፍ ለሱማሌ፣ አፋር፣ ጋምቤላ፣ ደብብ ክልል፣ ሲዳማ፣ ቤኒሻንጉል፣ ትግራይ፣ ሃረሪ፣ ወዘተ ከወዲሁ ግንኑነቱን ማጥበቅ ይጠበቅበታል እንላለን፡፡

አቶ ልደቱ አያሌው፡- ለሠላሳ አመታት የመናጆ ፖለቲካን (Pacemaker) በማራመድ የሚታወቁት አቶ ልደቱ አያሌው  ከምፅዐተ ኢትዮጵያ የ2019ዓ/ም ምርጫ ያድነናል!!! ሠላማዊ የፖለቲካ ትግል ኢትዮጵያን ይታደጋል፣ ኢትዮጵያዊ ህብረ ብሔራዊ ትግል ምፅዐተ-ኢትዮጵያን ይታደጋል!!! በሚል ዛሬም የሠላማዊ ትግል ምልክትና አርዓያ የሆነው እስክንድር ነጋ እድሜውን የጨረሰው አንባገነኖች እስር ቤት ነበር፣ ዛሬ በፋኖ የሽምቅ ትግል የኮነሬል አብይ ፋሽስታዊ አገዛዝ እድሜ ለማሳጠር ዱር ቤቴ ካለ ሠነበተ፡፡ ዛሬ አቶ ልደቱ የሠላማዊ ትግልን ለማንኛው ክልል ሊሰብክ ይሻዋል? ኮነሬል አብይ የአማራን ልዩ የፖሊስ ኃይል ለማስፈታት አቅዶ፣ አማራን  ሱሪውን አስወልቃለሁ ያለ ጸረ-ህዝብና ፀረ-ዴሞክራሲ መንግስትን በሠላማዊ መንገድ ማውረድ ይቻላል፡  ለምርጫ እንሰናዳ ይሉናል፡፡ ገና ሦስት አመት ጠብቀን፣ ኮነሬሉም ገና ሥስት አመት ይቀረኛል ነው እኮ ያሉት፣ በህዝብ የተመረጠን መንግሥት ለማውረድ ቢሞከር ከደርግ ቀይ ሽብር መቶ እጥፍ በአንድ ቀን የሰው እልቂት እፈፅማለሁ ያለ ፋሽስት ጋር ስለ ሠላማዊ ትግል ማውራት ምፅአተ ወሬ ነው፡፡ የአቶ ልደቱ አያሌው መጣጥፍ ‹‹ከሞት በኃላ ህይወት›› አለና ለሰማያዊ ዓለማችሁ አስቡ ምድራዊ ዓለማችሁ አያሳስባችሁ ነው የሚሉን፡፡ ኮነሬል አብይ አህመድ ፋሽስታዊ አገዛዝ እስከ 2019ዓ/ም ምርጫ በሰላማዊ ውድድር እንዲወርድ ማድረግ እንችላለን እስከዚያ ብንታገስ የሚል ጥቅል እንድምታ አለው፡፡ በሠላማዊ መንገድ የታገሉ አንድ ሽህ አንድ የአገሬ የፖለቲካ ሰዎች ለእስር የተዳረጉበት ዴሞክራሲ ባልታጠነ ፋሽስታዊ ሥርዓት ቀንበር ስር ሆነው ነው፣ ሥርዓቱን አጥተውት ግን አይደለም፡፡ አቶ ልደቱ ታዲያ አንዴ እን በአፍ ወለምታ እን በሠላማዊ ትግል ተሳትፈው ለታፈኑ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!! እንዴት አላሉም፡፡

አቶ ጁሃር መሃመድ፡- ከደረጀ  ኃይሌ ጋር ‹‹በነገራችን ላይ›› ፣በጃዋር ቃለመጠይቅ የተነሱት አንኮር ጉዳዩች› ክፍል አንድ በተመለከተ የኮነሬል አብይ መንግስት በዴሞክራሲያዊ ሥርዓትና በፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ መኃል ላይ ያለ አኖክራሲ ሥርዓተ አገዛዝ ነው፡፡ Barbara F Walter ትላለች በመጽሃፎ  “How civil wars start and how to stop?  የአኖክራሲን ስትተነትን  Anocracy፡  “the key concept is that of “anocracy”, a transition stage of government between autocracy and democracy.” Barbara F Walter  “How civil wars start and how to stop? “ አቶ ጁሃር መሃመድ የባርባራን ጽንሰ-ሃሳብ እንደራሳቸው ግኝት አድርገው በማቅረብ የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት ዴሞክራሲያዊም አይደል፣ እንዲሁም አንባገነናዊም መንግሥት አይደለም ብለው ሊያሳምኑን ይሞክራሉ፡፡ የኮነሬል አብይ ፋሽታዊ አገዛዝ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶችን በጦርነት ያስጨረሰና ሃያ ስምንት ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የመሠረተ-ልማት ውድመት ያስከተለ ሥርዓትን አኖክራሲ ብሎ ማለሳለስ የአድርባይነት አመለካከት ነው፡፡ አቶ ጁሃር በኦሮሚያ በትግራይና በአማራ ክልሎች የተለኮሰውን የማያባራ ጦርነት ጠማቂ ኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት መሆኑን አይረዱም ማለት ዘበት ነው፡፡ የኮነሬል አብይ መንግሥት ‹የዴሞክራሲ ሥርዓት› ያሳፍናል ብሎ መመኘት ከእባብ እንቁላል፣ እርግብ እንዲፈለፈል መጠበቅ ነው፡፡ በኮነሬል አብይ መንግሥት ‹ዴሞክራሲ›  በሌለበት ሥርዓት ‹ሠላማዊ ትግል› ማድረግ ይቻላል የሚለው ምኞት የአቶ ልደቱ አያሌው፣‹‹የመናጆ ፖለቲካ›› ፔስሜከርስ የሮጭ አሮሮጭ ሆኖ በምርጫ መሳተፍ የመናጆ ፖለቲካ ነው እንላለን፡፡ ይህን የመናጆ ፖለቲካ አቶ ጁሃር መሃመድ ማራመዳቸው አየስገርምም፡፡ ለዴሞክራሲ ለማምጣት እንታገላለን የሚሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች ህብረተሰቡ ምሁሩ የሚያቀርበውን ገንቢ ሂስ ከማቅረብ ይልቅ የራሳቸውን አስተሳሰብ ብቻ በመጫንና ሁሌ እንደ ገደል ማሚቶ የሚያስተጋባ እንጉርጉሮ ማሰማት የዴሞክራሲ ባህል አይደለም እንላለን፡፡ በኢትዮጵያ መጀመሪያ የጋዜጠኝነት ሙያና ሥነምግባርን  መንግሥት አረከሰውና አጠፋው፣  ቀጥሎም  አንባገነንነትን በዴሞክራሲ ጽንሰ-ሃሳብ ጠቀለለው፣ እንደ ሽንኩርት ብትልጠው ብትልጠው ዴሞክራሲ በነቢብ ብቻ፣ በዓብይ ምላስ ላይ ብቻ፤   አንባገነንነት በገቢር  የማያባራ ጦርነት በተግባር የህዝብ የእለት እንጀራ ሆነ፡፡ የኮነሬል መንግሥቱ ኃይለማርያም፣ የመለስ ዜናዊ፣ የኃይለማርያም ደሣለኝ፣ የኮነሬል አብይ አህመድ ፋሽስታዊ ስርዓት በዴሞክራሲ ስም፣ በምርጫ ስም፣ ሲምሉና ሲገዘቱ ዘመናት አለፈ፡፡ አቶ ልደቱ፣ ጁሃር፣ ወዘተዎች ኢትዮጵያ ውስጥ  ስለየትኛው ዴሞክራሲ እንደሚያወሩ አይታወቅም፡፡ ዛሬ የሚሰማ ትውልድ ተፈጠረ፣ ዛሬ ሦስት ገጽ የማያነብ ትውልድ ተፈጠረ፣ ዛሬ የማይጽፍ ትውልድ የኮምፒውተር ኢንተርኔት የሚተይብ ዘመናይ ትውልድ ተፈጠረ፣ ከጥቂት አመታት በኃላ  በእጁ በእስኪሪቢቶ መፅፍ የማይችል ትውልድ እንደሚሆን ምንም አያጠያይቅም!!! በኢትዮጵያ ዬኔታ ዳግም የፊደል ሠራዊት፣የቄስ ትምህርት ቤት የፊደል ገበታ የሚዘረጉበት  ጊዜ ይመጣል፡፡ በአዲሱ ቴክኖሎጂ ምን ተማርንበት ቀሰምንበት፡፡  የምሁራን ምርምርና ጥናት ይጠይቃል፡፡               

የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!!

Filed in: Amharic