>
5:16 pm - Monday May 24, 5610

ዘመነ ካሴ የበለጠ ሞላን ፈለግ ቢከተል  እስክንድር ነጋ መውሰድ ያለበት ጥንቃቄ

ዘመነ ካሴ የበለጠ ሞላን ፈለግ ቢከተል  እስክንድር ነጋ መውሰድ ያለበት ጥንቃቄ

 

ያልጠረጠረ ተመነጠረ፣ ያልመከተ ተፈነከተ

መስፍን አረጋ

ሙሉ ጥንካሬው አውሬነቱ ብቻ የሆነው፣ ጨለማን ተላብሶ ተከላካይ አልባ ሰላማዊ ሰወችን ከማረድና ከማወራርድ በስተቀር በታሪኩ አንድም ጊዜ እንኳን ፊት ለፊት ተዋግቶም ሆነ ድል አድርጎ የማያውቀው፣ የጦቢያን የመንግስት መዋቅር ሙሉ በሙሉ ባይቆጣጠርና የምዕራባውያን ሙሉ ድጋፍ ባይኖረው ኖሮ የሸዋ ፋኖ ብቻ ደምጥማጡን ሊያጠፋው የሚችለው ሙትቻው ኦነግ፣ ኢትዮጵያን በኦሮሙማ መልክ እሰራታለሁ እያለ ሲፎክርና ሲደነፋ፣ ኢትዮጵያን በደምና ባጥንቱ የገነባትንና ከውስጥና ከውጭ ጠላቶች ጠብቆ ያቆያትን፣ በጀግነነቱ ወደር የሌለውን፣ በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረውን፣ ጎጠኝነትን የሚጸየፈውን፣ የሕዝብ ቁጥሩ የኦሮሞ ስም ስለተለጠፈበት ብቻ ኦሮሞ ነው የሚባለውን የሞጋሴና የጉዲፈቼ ድምር በብዙ ሚሊዮኖች የሚበልጠውን፣ ትልቁን የአማራን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉት ደግሞ፣ ኢትዮጵያ በሚገባት ደረጃ አማራ፣ አማራ የምትሸት አማራዊ ትሆናለች ከማለት ይልቅ ያማራን ሕዝብ ከኦሮሙማ በማሳነስ መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ ሲሉ ከማየት የበለጠ አሳፋሪ ነገር የለም።      

_____________________________________

ፋኖ ዘመነ ካሴ ባማራ ሕልውና ትግል ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው ማለት ያዋጁን በጆሮ ነው።  የዘወትር ጸሎታችን ደግሞ ጭራቅ አሕመድ ካራት ኪሎ ጆሮውን ተይዞ ወጥቶ በስቅላት ለዘላለም ተሸኝቶ ፣  ቀንደኛወቹ ወያኔወችና ኦነጎች ከያሉበት ተለቃቅመው ፍርድቤት ቀርበው የሚገባቸውን ቅጣት አግኝተው፣ ወያኔና ኦነግ የሚባሉት ድርጅቶች እንደ ድርጅት መቸም ላይመለሱ ሙተው ተቀብረው፣ ያማራ ሕልውና መቸም አደጋ ላይ እንዳይወደቅ ሁኖ በማያደግም ደረጃ ሙሉ በሙሉ እስከሚረጋገጥ ድረስ፣ ከሁሉም ፋኖወች ጋር ባንተ ትብስ፣ አንቺ ትብሽ መንፈስ እየተባበረ የሕልውና ትግሉን እንዲገፋበት ነው።  

 ባለመታደል ግን ፋኖ ዘመነ ካሴ ካማራ ሕልውና በላይ የራሱን ስልጣን እንደሚያስቀድም  ጉልህ ፍንጮችን እያሳየ ነው።  ለዚህ ምሳሌ ደግሞ እሱ ዘመነ ካሴ ከነመፈጠሩ ከማይታውቅበት ጊዜ ጀምሮ መላውን ያማራን ሕዝብ ጨምሮ ለመላው ጦቢያውያን ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ከፍተኛ ትግል እየታገለ ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለውን  (ማንም ሰው ሊያንቋሽሸው ወይም ሊያንኳስሰው የማይችለውን) እስክንድር ነጋን ለማንቋሸሽና ለማንኳሰስ ሲሞክር መታየቱን መጥቅስ ብቻ ይበቃል።  ይህ ደግሞ ሌላ ምንም ሳይሆን ኋላ የመጣ ዓይን ዓወጣ ነው።  

ፋኖ ዘመነ ካሴ ፋኖ እስክንድርን መተቸት ካስፈለገው ውስጥ ለውስጥ መተቸት ሲችል፣ ያማራን ገመና ውጭ አውጥቶ፣ አደባባይ አስጥቶ ለወያኔና ለኦነግ በማጋለጥ፣ እስክንድርን ጨምሮ የሁሉም ፋኖወች የበላይ እኔ ስለሆንኩ ሁሉም ጉዳይ ማለፍ ያለበት በኔ በኩል ነው የሚል ዓይነት ትቢት አዘል መልዕክት በዩቱቦ (YouTube) አስተላልፏል።  የዘመነ ካሴ አሁናዊ ሁኔታ የሚጠቁመው፣ እስክንድር ጦሩን ይዞ ወደ አዲሳባ ቢመጣ፣ እስክንድር ስልጣን ላይ ከሚወጣ ሁሉንም ነገር ልጣ ብሎ፣ ከጭራቅ አሕመድ ጋር አብሮ እስክንድርን ከኋላ ሳይወጋው እንደማይቀር ነው።   

ስለዚህም ፋኖ ዘመነ ካሴ እሱ ራሱ ፍንጨ እያሳየን እንዳለው የበለጠ ሞላን ፈለግ በመከተል ካማራ ሕልውና በላይ የራሱን ስልጣን አስቀድሞ ፣ በለጠ ሞላ ከጭራቅ አሕመድ ጋር ተመሳጥሮ አብንን እንዳቀለጠው  ዘመን ካሴም ከጭራቅ አሕመድ ጋር ተደራድሮ ፋኖን እንዳይከሰክሰው  ከወዲሁ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ የግድ ነው፣ ያልጠረጠረ ተመነጠረ፣ የጠረጠረ ቤቱን አጠረ  ነውና።  ያማራ ሕዝብ ደግሞ፣ ደጋግሞ እየተካደ፣ ባመናቸው ፈረሶች በደንደስ እየተጣለ መከራውን ስለበላና ፈጠቁ ስለፈጀ፣ ትንሽ ጭስ ሲያይ እሳት ብሎ ቢጮህ አይፈረደበትም፣ እባብ ያየ በልጥ በረየ ነውና።        

በመጀመርያ ደረጃ ፋኖ ዘመነ ካሴ ለእስር የበቃው ፣ መቸም መታመን የሌለበትን እምነት ቢሱን ጭራቅ አሕመድን አምኖ  ከጭራቅ አሕመድ ጋር ለመሸማገል ቀርቦ ጭራቅ አሕመድ ስለካደው ብቻ ነው።  አንዴ ለመሸማገል የሞከረ ደግሞ ሁለቴም፣ ሶስቴም ለመድገምና ለመደጋገም አይመለስም ፣ ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስስ አይለቅምና።  የዘመነ ካሴ አዳናቂወች “መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ” ሲሉ ደግሞ ኢትዮጵያ በሚገባት ደረጃ አማራ፣ አማራ ትሸታለች ወይም አማራዊ ትሆናለች እያሉ ሳይሆን፣ ያማራ ክልል የሚባለውን ወያኔ ሠራሽ የኢትዮጵያ ክፍል ከተቆጣጠርን በኋላ በቀረው የኢትዮጵያ ክፍል ላይ ከጭራቅ አሕመድ ጋር እንደራደራለን እያሉ ነው።  ባማራ ሕዝብ ላይ ይህን ሁሉ የመከራ ዝናብ ካዘነበው ከጭራቅ አሕመድ ጋር መደራደር ቀርቶ ለመደራደር የሚያስብ ደግሞ ከራሱ ከጭራቅ አሕመድ በላይ ያማራ ሕዝብ ጠላት ነው ።  

ባማራ ሕዝብ ባሕላዊና ታሪካዊ ትውፊት በየለቱ የሚስቁትና የሚሳለቁት፣ የፋኖ ደጋፊ መስለው በመቀረብ ፋኖን ከፋፍሎ የማዳክም አጀንዳ የተሰጣቸው እነ ኦቦ ዮናስ ብሩን የመስሉ ቀንደኛወቹ ኦሮሙሜወች ዘመነ ካሴን አለቅጥ በመካብ ሰማይ ሲያደርሱት ሲመለከት ደግሞ፣ ያማራ ሕዝብ ለምን ብሎ ሊጠይቅ ይገባል።  ካማራ ሕዝብ ዓይነተኛ ባሕሪወች ውስጥ አንዱ ደግሞ አይሆንምን ትቶ ይሆናልን የሚይዝ ገንጋኝ  (ጠርጣራ) መሆኑ ነው።      

ስለዚህም ላማራ ሕልውና ወሳኝ የሆነው የውቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ ፣ ዘመነ ካሴ ፍንጭ እያሳየን እንዳለው የበለጠ ሞላን ፈለግ እከተላለሁ ብሎ ቢነሳ፣ በለጠ ሞላ በአብን ላይ ያደረሰውን ያህል ጉዳት፣ እንደውም እጅግ በጣም የበለጥ ጉዳት ዘመነ ካሴ በፋኖ ላይ እንዳያደርስ ከወዲሁ ምን ጥንቃቄ ይወሰድ የሚለው ነው።  የዚህ ወሳኝና አንገብጋቢ ጥያቄ መልስ ደግሞ አጭርና ቅልብጭ ያለ ሲሆን፣ እሱም እስክንድር ነጋን /ጠበቅ/ አድርጎ መያዝ ነው።    

ባሁኑ ሰዓት ከትግሬና ከኦሮሞ ጎጠኞች በስተቀር ጦቢያውያንን ሙሉ በሙሉ ባንድነት በማሰባሰብ የሚችል መሪ አንድ ብቻ ሲሆን፣ እሱም አብዛኛው የጦቢያ ሕዝብ በሙሉ ልብ የሚያምነው፣ የእውነተኛነትየርተኧኛነት (ቀጥተኛነት)፣ የፍትኸኛነትየጽናትና ያይበገሬነት ተምሳሌት የሆነው ፋኖ እስክንድር ነጋ ነው።  የእስክንድርን ታማኝነት፣ ሰብዓዊነትና ጨዋነት እጅጉን የሚያጎላው ደግሞ ከኦሮሙማው መሪ ከጭራቅ አሕመድ ቀጣፊነት፣ አጭበርባሪነት፣ ቀላማጅነት፣ ባለጌነት፣ ነውረኛነት፣ ጋጠወጥነት፣ መሠሪነት፣ አውሬነትና አረመኔነት (ባጠቃላይ ደግሞ አጸያፊ ሰብእና) አንጻር ሲታይ ነው።  ስለዚህም በእስክንድር ነጋ የሚመራ ያማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል አማራ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያንን በቀላሉ በዙርያው በማሰበሰብ የትግሉን ሜዳ አማራ ክልልን ብቻ ሳይሆን መላዋን ጦቢያን የሚያጠቃልል ሰፊ ሜዳ አድርጎበመላዋ ጦቢያ ላይ በሰፊው የተሰራጩትን እልፍ አእላፍ አማሮች በስፋት አሳትፎ ፣ የጭራቅ አሕመድን ኦነጋዊ መንግስት መግቢያ መውጫ በማሳጣት ውድቀቱን በከፍተኛ ፍጥነት እንደሚያቃርበው ሳይታለም የተፈታ ነው። 

ፋኖ ዘመነ ካሴ ጭራቅ አሕመድን ለማስወገድ ከፍተኛ ሚና ሊጫወት ይችላል።  መላውን የጦቢያን ሕዝብ ቀርቶ መላውን ያማራን ሕዝብ በዙርያው ለማሰባሰብ ግን አይችልም ባይባልም እንኳን በጣም ያዳግተዋል፣ የእስክንድርን ያህል አይቀልለትም።  ሌሎቹም ፋኖወች (ምሬ ወዳጆ፣ መሳፍንት ተስፉ ወዘተ. ) እንደዚሁ።

ፋኖወች ምሬ ወዳጆ፣ መሳፍንት ተስፉና የመሳሰሉት ጎበዝ ወታደሮች ቢሆኑም፣ የፖለቲካ ብስለታችውና የእይታ አድማሳቸው ግን እጅግም የሰፋ አይደለም ፣ በዚህ ረገድ ብዙም ልምድ የላቸውምና።  ጭራቅ አሕመድ ደግሞ የተፈጠረው ለማታለል ብቻ የሆነ ተፈጥሯዊ አታላይ ከመሆኑም በላይ በማታለል በተካኑ፣ አማራን አምርረው በሚጠሉ አታላይ ምዕራባውያን አማካሪወች የሚመከር ነው።  ስለዚህም ፋኖወች ምሬ ወዳጆ፣ መሳፍንት ተስፉና የመሳሰሉት  የጭራቅ አሕመድን ሸር እና ደባ የመገንዘብ ችሎታቸው እጅግም ነው።  በዚህ ረገድ ደግሞ ዘመነ ካሴ ከነ ምሬ ወዳጆ የተሻለ ቢሆንም እምብዛም የላቀ አይደልም፣ ከጅ እይሻል ዶማ እንዲሉ።  ለዚህ ምሳሌ ደግሞ ዘመነ ካሴ ያሜሪቃ ባንዲራ የተለጠፈበትን ጥብቆ (T-shirt) ለብሶ ዩቱቦ (YouTube) ላይ በመቅረብ ያሜሪቃን ድጋፍ ለማግኘት መሞከሩን መጥቀስ ብቻ ይበቃል።  

ምዕራባውያን በተለይም ደግሞ እንግሊዝና አሜሪቃ አማራን የሚጠሉት አማራ በመሆኑን እንጅ፣ ያማራ ሕዝብ ምንም ቢያደርግ ከጎኑ እንደማይቆሙ ዘመነ ካሴ አሁንም ድረስ አልተረዳም።  ጥቂት የትግሬ ሴቶች ተደፈሩ  ከሚል በመረጃ ካልተረጋገጥ አሉባልታ (unconformed report) ተነስተው፣ ትግሬወች አዲሳባ ላይ በትግሬነታቸው ታሰሩ ብለው ኡኡታውን ሲያቀልጡት የነበሩት፣ የተባብሩት መንግስታትን የጸጥታ ምክር ቤት በትግሬወች ጉዳይ አምስት ጊዜ ስብሰባ ያስቀመጡት ምዕራባውያን ፣ ባማራ ሕዝብ ላይ በቪዲዮ የተደገፈ ከፍተኛ ጭፍጨፋ ሲፈጸም፣ አማሮች ባማራነታቸው ብቻ ከያሉበት እየተለቀሙ በገፍ ታስረው በግፍ ሲሰቃዩ (tortured) ሰምተው እንዳልሰሙ፣ አይተው እንዳላዩ የሆኑት ያማራን ሕዝብ መጨፍጨፍ በቀጥታና በተዛዋሪ የሚደግፉ በመሆናቸው መሆኑን ፋኖ ዘመነ ካሴ በቅጡ የተረዳ አይመስልም።  

ባጠቃላይ ደግሞ ጦቢያን በተመለከት የምዕራባውያን (በተለይም ደግሞ የንግሊዝና ያሜሪቃ) ዋና ዓላማ ቢቻል ያማራን ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ማጥፋት፣ ባይቻል ደግሞ ቁጥሩን በጭፍጨፋ፣ በርሐብና በበሽታ በማመናመን ፣ ብዛቱ ከኦሮሞና ከትግሬ ሕዝብ ብዛት እጅጉን ያነሰ፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የሚጫወተው ሚና ኢምንት የሆነ  አናሳ ብሔረሰብ (minority) ማድርግ መሆኑ ለዘመነ ካሴ አልታየውም።  ዘመኔ ካሴ ይህ ሁሉ የማይታየው በመሆኑ ደግሞ አሜሪቃኖች ዘመነ ካሴን በተለያዩ መንገዶች በማሳመን ጉያቸው ውስጥ አስገብተው፣ ያሜርቃ ጉዳይ አስፈጻሚ የማድረጋቸው እድል ከፍተኛ ነው።  

ስለዚህም፣ ያማራ ሕዝብ ሆይ ፈረንጆቹ እንደሚሉት ሁሉንም እንቆላሎችህን አንድ ቅርጫት ውስጥ በማስገባት (put all your eggs in one basket) ዘመነ ካሴ ላይ ሙሉ በሙሉ ተማምነህ ባለቤቷን ተማምና ላቷን ውጭ እንዳሳደረቸው የዋህ በግ ሁነህ፣ በኦሮሙማ ጅብ ቁርጥምጥም ተደረገህ እንዳትበላ ከወዲሁ ተጠንቀቅ።  እንደ ወርቅ በእሳት ተፈትኖ የወጣውን፣ ከእምነቱና ካቋሙ ዝንፍ እንደማይል በተግባር ያሳየውን፣ በስልጣን፣ በጥቅም ወይም በሌላ በማናቸውም መደለያ ሊደለል የማይችለውን፣ የምዕራባውያን ጉዳይ አስፈጻሚ ይሆናል ተብሎ የማይጥረጠረውን የቁርጥ ቀን ልጅህን አርበኛውን እስክንድር ነጋን እንዳይንህ ብሌን እየተንከባከብክ አጥበቅህ ያዝ። 

የጭራቅ አሕመድን ጭራቃዊ መንግስት ከሁሉም ፋኖወች በላይ ይበልጥ የሚያሰጋው መነሻችን አማራ መድረሻችን ኢትዮጵያ ብሎ የተነሳው ፋኖ እስክንድር ነጋ ነው።  እነ ዮናስ ብሩን የመሰሉ የጭራቅ አሕመድ ጭራቃዊ መንግስት ቀንደኛ ደጋፊወች የቀሩትን ሁሉንም ፋኖወች እያሞገሱ በፋኖ በእስክንድር ነጋ ላይ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ የከፈቱትም፣ ሌሎቹን ፋኖወች ወደዋቸው ሳይሆን ዋና ስጋታቸው ፋኖ እስክንድር ነጋ መሆኑን በደንብ ስለሚያውቁ ነው።  የእስክንድርን ስም ለማጥፋት እየሞክሩ ያሉት ደግሞ እስክንድር ጦር የለውም የሚባለውን ወሬ በማናፈስ ነው።  የእስክንድርን ስም በዚህ ወሬ ማጥፋት የተፈለገው ደግሞ ስሙን በሌላ ወሬ ማጥፋት የማይቻል ስለሆነ ብቻ ነው፣ እስክንድርን ባላዋቂነት፣ በሆዳደርነት፣ በነጭ አሽከርነት፣ በጎጠኝነት፣ በጠባብነት፣ በዘረኝነት፣ በፊሪነት፣ በሐይማኖት አክራሪነት፣ ባግላይነት፣ በውሸታምነት፣ ባስመሳይነትና በመሳሰሉት መክሰስ አይቻልምና።  በተለይም ደግሞ ዘመነ ካሴ ፍንጭ እያሳየ እንዳለው፣ እስክንድርን በስልጣን ጥመኝነት መጠርጠር ስለማይቻል ነው።  

የእስክንድርን ስም በማጥፋት ዘመቻ ላይ የተሰማሩት ደግሞ ወያኔወችና ኦነጎች ብቻ ሳይሆኑ፣ ባማራ ሕዝብ ደም የስልጣን ጥማቸውን ለማርካት ያሰፈሰፉ፣ ያማራ ሕዝብ መሠረታዊና ዘላለማዊ ጠላት ከሆነው ካሜሪቃ መንግስት አመራሮች ጋር በተለይም ደግሞ ከሚካኢል መዶሻ (Mike Hammer) ጋር በየጊዜው እየተገናኙ በየጊዜው የሚዶልቱ፣ አማራን ከኢትዮጵያውነት ዝቅ አድርጎ ከኦሮሙማ በታች የሚያደርግ “መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ” የሚል አዲስ መፈክር ያነገቡ፣ የስልጣን ጥማቸውን ለማርካት ምንም ከማድረግ የማይመለሱ፣ ያማራ ለምድ የለበሱ ፀራማራ ተኩላወች ናቸው።  

እስክንድር ጦር የለውም የሚባለውን ወሬ ካማራ ሕዝብ ጠላቶች እየተቀባበላችሁ እንደ ገደል ማሚቶ የምታስተጋቡ፣ ጦር ማለት ምን ማለት እንደሆነ የማታውቁ የዋሆች አማሮች ደግሞ እውነትም ላማራ ሕልውና የቆማቸሁ ከሆነ፣ እስክንድር ጦር የለውም ከማለት ይልቅ፣ የእስክንድር ያለው ጦር በብዛትና በጥራት ይበልጥ ያድግና ይመነደግ ዘንድ የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ።  እነ ዘመነ ካሴ፣ ምሬ ወዳጆ፣ መሳፍንት ተስፉና የቀሩት ሁሉም ፋኖወች ደግሞ ያማራን ሕዝብ ሕልውና ከስልጣንም ከሌላም በላይ አስቀድመው ፣ የሁሉም አገር ወዳድ ጦቢያውያን ሙሉ ድጋፍ ስላለው ያማራን ሕልውና ለማስጠበቅ ፍቱን በሆነው ፣ መነሻችን አማራ መድረሻችን ኢትዮጵያ ብሎ በተነሳው በፋኖ በእስክንድር ነጋ ዙርያ እንዲሰባሰቡ ለማሳመን የበኩላችሁን ድርሻ ተውጡ ። 

በመጨረሻም ምክር ቢጤ ለክቡር ውድ ወንድሜ ላርበኛ እስክንድር ነጋ ።  የስልጣን አራራ (ጥም) ሌላው ቀርቶ ከራስ አብራክ የወጣን የራስ ልጅን እንደሚያስገድል፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪከ በደንብ ለምታወቀው ላንተ ለእስክንድር ነጋ መንገር ማለት ቀባሪውን ማርዳት ነው።  ያማራ ሕዝብ መሠረታዊ ጠላት በሆነው ባሜሪቃ መንግስት የሚደገፉት፣ አማራን እንወክላለን የሚሉት የስልጣን ጥመኞች እያደረጉ ያሉት ደግሞ አንተን እስክንደር ነጋን በሰላሳ ጠገራ ሽጠው ለወያኔና ለኦነግ አሳልፈው ለመስጠት ወይም ደግሞ እነሱ ራሳቸው ለማስገደል መሆኑን ከቀን ወደ ቀን ይበልጥና ይበልጥ ግልጽ እየሆነ መጥቷል።  

ስለዚህም አርበኛ እስክንድር ነጋ ሆይ፣ እንደ እርግብ የዋህ ብትሆንም እንደ እባብ ብልጥ ሁነህ፣ በዙርያህ እየተፈጸመ ያለውን ደባ አይትህና አስተውለህ፣ እኛም አወቀናል ጉድጓድ ምሰናል ብለህ፣ ደባውን ለማክሸፍ መውሰድ ያለብህን ጥንቃቄወች ሁሉ ባጣዳፊ ውሰድ።  አስፈላጊ ከሆነ ደግሞ የቻይና ሕዝብ የነጻነት አርበኛ ከነበረው ከማኦ ዜዶንግ (Mao Zedong) ተምረህ፣ ታማኝ ወታደሮችህን ይዘህ፣ ረዥም ጉዞ (Long March) ተጉዘህ፣ ራስህንና ወታደሮችህን በቀላሉ እየተከላከልክ ይህን ክፉ ቀን ማሳለፍ ወደምትችልበት መቀደላ አምባን ወደሚመስል ምሽግ አምራ።  እዚያ መሽገህ ደግሞ እራስህንና ጦርህን ካዘጋጀህና ካደራጀህ በኋላ የቻይናዊውን የጦርነት ጠቢብ የሰንሹን (Sun Tzu) መመሪያ በመከተል በመላዋ ጦቢያ ላይ ስፋ፣ ተንሰራፋ።     

በጥበበኛ አዛዥ የሚመራ ጦር ሳይታሰብ ግድቡን ጥሶ በሚጎርፍ ደራሽ ውሃ ይመሰላል፡፡  ደራሽ ውሃ ከፍተኛ ቦታን እየለቀቀ፣ ወደ ዝቅተኛ ቦታ እያዘቀዘቀ፣ ዝቅዝቅ በመጉረፉ በሚያገኘው እየጨመረ የሚሄድ እንድርድረት (increasing momentum) እንቅፋቶቹን እየጠራረገ ረባዳን ያጥለቀልቃል፡፡  በጥበበኛ የጦር አዛዥ የሚመራ የጦር ሠራዊትም የጠላትን ጠንካራ ጎን እየራቀ፣ ደካማ ጎኑን እየሰነጠቀ፣ እየጎለበተ በመትመም፣ የጠላት ጦር ያልሰፈረበትን የጠላት ግዛት እንበለ ውጊያ በመቆጣጠር ይንቦራቀቅበታል፡፡  ደራሽ ውሃ ወደ መዳረሻው የሚወንዘው አወናነዙን ከመሬቱ አቀማመጥ ጋር እያዛመደ ፍጥነቱን፣ ስፋቱንና ጥልቀቱን በመለዋወጥ እንደሆነ ሁሉ፣ በጥበበኛ የጦር አበጋዝ የሚመራ ሠራዊትም ወደ ግቡ (goal) የሚያመራው የጠላቱን ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ትልሙን (strategy) እና ስልቱን (tactic) እንዳስፈላጊነቱ በመለዋወጥ ነው፡፡”  ሰንሹ (Sun Tzu)

ውድ ወንድሜ አርበኛ እስክንድር ነጋ ሆይ፣ ሁሉ ይቅርብኝ ብለህ ሁሉን ዓይነት መስዋእትነት ለጦቢያ እየከፈልክላት ነውና፣ የጦቢያ አምላክ በሄድክበት ሁሉ እየጠበቀህ ያሰብከውን ሁሉ ያሳካልህ ዘንድ፣ ጦብያን ከጠላት ለመታደግ ታቦታቸውን ተሸክመው ፣ ዳዊታቸውን አንግበው አድዋ የዘመቱት ያያቶቻችን ጸሎት መቸም አይለይህ ዘንድ የዘወትር ጸሎቴ ነው።  የጦቢያ መሠረታዊ ጠላቶች የሆኑት ኦነግና ወያኔ እንዲሁም የነሱ ደጋፊወች የሆኑት ምዕራባውያን የወረቀት ነብሮች (paper tigers) ናቸውና፣ የነዚህን የወረቀት ነብሮች ጭራወች ደግሞ እንዴ ይዘሃልና መቸም እንዳትለቃቸው የጦቢያ አምላክ ይርዳህ።   

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic