>

የ’መነሻችን የአማራ ህልውና መዳረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት’ እና የ’መነሻችን አማራ መዳረሻችንም አማራ’  ልዩነቶች

የ’መነሻችን የአማራ ህልውና መዳረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት’ እና የ’መነሻችን አማራ መዳረሻችንም አማራ’  ልዩነቶች


በርእሱ ላይ የተጠቀሱት ሁለት ሃሳቦች ልዩነት ዙሪያ፣ ትንተና እንዲሰጥባቸው እየጠየቁ ያሉ ብዙ ሰዎች አሉ።  አንዳንዶቹ ከፍተኛ ምሁራዊ ትንታኔን በመስጠት የሚታወቁት  የአማራን ትግል ሲያቀጣጥሉ የነበሩ ምሁራን ናቸው። ይኽ ጽሑፍ የነዚኽን ጥያቄዎች በከፊልም ቢኾን ሊመልሱ የሚችሉ ነጥቦችን የሚዳስስ ይኾናል።

‘መነሻችን የአማራ ህልውና መዳረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት’ የሚለውን ጽንሰ-ሃሳብ ለሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል በመጀመሪያው ‘መነሻችን የአማራ ህልውና’  የሚለውን ቀጥሎም ‘መዳረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት

‘መነሻችን የአማራ ህልውና’ ሲባል፣’ የሚለው እንይ።

መነሻችን የአማራ ህልውና ሲባል፣ በመጀመሪያ ደረጃ በአሁኑ ሰዓት የማእከላዊ መንገሥቱን የተቆጣጠረው የአውሬው ኦሮሙማ ቡድን በአማራው ህዝብ ላይ በመላው ኢትዮጵያ የከፈተውን ጥቃት መቀልበስ ነው።መነሻችን የአማራ ህልውና ሲባል፣  በመላው ኢትዮጵያ  የሚኖረውን አማራ ህልውና ማስከበር ነው። መነሻችን የአማራ ህልውና ሲባል፣  በክልልና በድንበር ሳይታጠር የእያንዳንዱን አማራ ህልውና ማስጠበቅ ማለት ነው።   መነሻችን የአማራ ህልውና ሲባል፣ አማራውን ላለፉት 35 ዓመታት ሲያስጠቃ የኖረውን የብአዴን ክልላዊ መንግሥት መዋቅር መበጣጠስ ነው። መነሻችን የአማራ ህልውና ሲባል፣ አማራው ላይ ተጭኖበት የነበረውን ብአዴናዊ  የሎሌነት ዝቅተኛ ስነልቦና ከሥር መሠረቱ መንግሎ መጣል ነው። መነሻችን የአማራ ህልውና ሲባል፣   በአዲሱ የአማራ ትውልድ እውነተኛውን የአማራ ማንነቱንና መገለጫዎቹ የኾኑትን ቁሳዊ፣ባህላዊ፣መንፈሳዊ፣ታሪካዊ እሴቶቹን መመለስ ነው። መነሻችን የአማራ ህልውና ሲባል፣  ፋኖ በሚቆጣጠራቸው ቦታዎች እያሠፈነው ያለውን    ፍትህንና ርትእን የተመረኮዘ አስተዳደርን ማሥፈን ነው። መነሻችን የአማራ ህልውና ሲባል፣  ፋኖ  በራሱ ላይ እየተገበረ ያለውን   ሥነምግባር ፣ ታማኝነት፣ አይበገሬ የአርበኝነት መንፈስ፣  መንፋሰዊነት፣ አጠናክሮ አማራው ቀድሞ ወደ ነበረበት ክብሩ መመለስ ነው። መነሻችን የአማራ ህልውና ሲባል፣  ዓማራው በወታደራዊ አቋሙ ማንም ባንዳ ተላላኪ የማይደፍረውና  የማይነቀንቀው   ደረጃ ላይ ማድረስ ማለት ነው። መነሻችን የአማራ ህልውና ሲባል፣  አማራው ዳግማዊ ግራኝ(አብይ አህመድ አሊ) አማራውን እንዳይጨፈጭፍ ፣ ቅርሱንና ሃይማኖቱን እንዳያወድም  አለመፍቀድ ማለት ነው።  መነሻችን የአማራ ህልውና ሲባል፣ አማራው አንድ ኾኖ ለአንድ ዓላማ የሚሰለፍ ህብረት ያለው ህዝብ እንዲኾን ማድረግ ማለት ነው።  መነሻችን የአማራ ህልውና ሲባል፣  አማራው አእምሮአዊ ሃብቱን(brain power) እንዳያበለፅግ፣ ተፈጥሮአዊ ሃብቱን ለልማት እንዳያውል ላለፉት 35 ዓመታት ከተደረገበት ገደብ ማላቀቅ ማለት ነው። መነሻችን የአማራ ህልውና ሲባል፣ በአጠቃላይ አማራው  ላለፉት 50 ዓመታት በቅጡ ያልተጠቀመበትን  እምቅ አእምሮአዊ ሃብቱን በማሳደግ  ላይ የተመሠረተ  የእድገት ጎዳናን  መጥረግ   ማለት ነው።


‘መዳረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት’ ሲባል፣ 

እስክንድር ነጋ የአማራ ህዝባዊ ግንባርን ሲመሠርት  የግንባሩን ዓላማና ግብ  በግልፅ  አማርኛ  “መነሻችን የአማራ ህልውና መዳረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት” የሚል የትግሉን መነሻና መዳረሻ  ወደ ትክክለኛው መስመር እንዲገባ ያደረገ ጽንሰ-ሃሳብን በማፍለቅ ነው።  ይኽ ጽንሰ-ሃሳብ ለኢትዮጵያ መሠረት የኾነውን  አማራውን ከጥፋት ለማዳንና ህልውናውን ለማረጋገጥ ቅድሚያን የሚሰጥ ኾኖ፤ መዳረሻውን አማራው እጅግ የሚወዳት ሀገሩ ኢትዮጵያን፤ ከባንዳ ተላላኪ ሀገር አፍራሽ፣ ፀረ-ኢትዮጵያ፣ ፀረ-አንድነት ኃይሎች መንጋጋ በማላቀቅ፤  ታሪካዊ የመሪነት ሚናውን በመጫወት፣ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ  በሀገሩ ሰንደቅ ዓላማ  በአረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ዙሪያ፤ በማሰለፍ፣  የኢትዮጵያን አንድነት ማረጋገጥ ነው።

አማራና ኢትዮጵያ

በመሠረቱ አማራው  ከኢትዮጵያዊነቱ ጋር የሚነጣጥለው  ታሪክ ሊኖረው አይችልም።  አማራው አሳምሮ የሠራትን  ኢትዮጵያ ሀገሩ በታሪክ አጋጣሚ በፈረንጅ ተላላኪ ባንዳዎች ላለፉት 50 ዓመታት ቢቀማም።  አማራ ካለ ኢትዮጵያዊነት፣ ኢትዮጵያዊነት ካለአማራ ሊኖር አይቻላቸውም። አማራው  ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ሊተው አይችልም። አማራና ኢትዮጵያ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። አማራና ኢትዮጵያን መለያየት  ማለት፣  አማራው የሞተላትን፣ አማራው የፀለየላትን፣ አማራው ሥልጣኔውን ያስፋፋባትን፣ አማራው የገነባትን፣ አማራው የብዙ ጎሳዎችን አንድነትና መብትና እኩልነት ጠብቆ ያቆያትን ሀገር፣ እፍኝ የማይሞሉ የአስተሳሰብ አድማሳቸው ጠባብ የኾኑ  በኮሎኒያሊስቶች የከፋፍለኽ ግዛው ሴራ ወጥመድ ውስጥ ወድቀው አስተሳሰባቸው የተበላሸ ከ1966ቱ ለውጥ ዋዜማ ጀምሮ እንደሃሸን የፈሉ የትግሬና የኦሮሞ ጎሰኛ የተማሪ ፖለቲከኞች እንዲበታትኗት አሳልፎ መስጠት  ማለት ነው።

አማራው አንድነቱንና ህልውናውን ካረጋገጠ ታሪካዊዋን ኢትዮጵያ ሀገሩን ለማዳንና ከገባችበት የባንዳ ፖለቲካ ማጥ ውስጥ ለማውጣት ብዙ አያስቸግረውም። አማራው ልክ እንደ ገናናዎቹ የኢትዮጵያ ነገሥታት በትልልቅ ሀገራዊ ሃሳቦች (grand national ideas and strategies) ዙሪያ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ በማሠለፍ  ኢትዮጵያን  ለመምራት የሚያስችል በቂ የአስተዳደርና ፣ የፖለቲካ አመራር ክህሎትና ልምድ አለው።   አማራው ኢትዮጵያ የባንዳ ሽብርተኛ ኦነጋውያን ሸኔዎች መፈንጫ እንድትኾን አይፈቅድም። አማራው   በኢትዮጵያ ምድር የሚኖሩ ከ80 በላይ የኾኑ ኢትዮጵያዊ ጎሳዎችን እንዲኹም በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ  ሀገርን ያቀኑ የጀግኖች አማሮችን ልጆችና የልጅ ልጆች፣ ሃይማኖት የለሹ  (pagan) የኦሮሙማ አጥፊ ቡድን በሚዘረጋው የጎጥ አገዛዝ  ተጨፍልቀው እንዲጠፉ የሚፈቅድ ሞራልም የለውም።

የአማራው በግልፅ ዘመቻ በተከፈተበት ባለፉት ቅርብ ዓመታት ውስጥ፤ እራሱን ከህልውና አደጋ ለመታደግ ብሎም ኢትዮጵያን ከገባችበት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለማውጣት የሚያስችል የጦር፣ የአስተዳደርና የፖለቲካ አመራር አቅም ያላቸው፤ ከህዝብ ቀድመው የነቁ፣ ለአማራው ህልውናና ክብር ሲሉ የተሰዉ፣ እንደ ጀነራል አሳምነው ጽጌ ያሉ አሁን ደግሞ ወደ ትግል ሜዳ ወርደው የአማራን የህልውና ትግል ለማስተባበርና  ከግብ ለማድረስ እየታገሉ ያሉ እስክንድር ነጋን የመሳሰሉ በርካታ ጀግኖችን ልጆችን ማፍራት የቻለ ነው። ሃምሳ ዓመት ወደ ዃላ ትንሽ ብቻ ገፋ አድርገን ታሪክን ስንፈትሽ ፤ በዐፄ ምኒልክና በዐፄ ኃይለሥላሴ ዘመን የተፈጠሩ በእውቀት የበለፀጉ ብልህና  ጥበበኛ፤ ተከብረው ሀገራቸው ኢትዮጵያን ያስከበሩ እንደ  ፊታውራሪ ተክለሐዋርያት ተክለማርያም፣ አዛዥ ሃኪም ወርቅነህ እሸቴ፣ ፕ/ር አፈወርቅ ገ/ኢየሱስ ፣ ልኡል ራስ ካሳ ኃይሉ፣ ጸሃፌ ትእዛዝ ወልደጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ፣    ብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደሥላሴ ፣ ብላቴን ማኀተመሥላሴ  ወልደመስቀል፣ ራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው ፣ ልጅ እንዳልካቸው መኮንን፣ሀዲስ አለማየሁ ፣ የሀብተወልድ ወንድማማቾች እነ አክሊሉ ሃብተወልድ  ፣ አምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ፣ ከተማ ይፍሩ፣  ይድነቃቸው ተሰማ ፣  ተመስገን ገብሬን ፣   የመሳሰሉ  ፣  በዓለም ላይ በጊዜው ከነበሩ የዓለም  የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ልሂቃን (world class elites) ተርታ የሚመደቡ የአማራው ማህበረስብ ትሩፋቶች የኾኑ ልሂቃንን  እናገኛለን።  በቅርብ ጊዜ ታሪካችን ደግሞ እንደ  ፕ/ር አሥራት ያሉ ሥመጥር  የህክምና ባለሞያና የአማራውን ህልውና ለማስከበር ለሚደረግ ትግል መሠረት የጣሉ ሀቀኛ የፖለቲካ መሪ፤  እንደ አፈወርቅ ተክሌ ያሉ ስመጥር  ሠዓሊያንን፤  በሥነ ጽሑፉ ዘርፍ እንደ  ፀጋዬ ገብረመድህን  ያሉ  ደራሲያንን፤   በተፈጥሮ ሳይንሱም ዘርፍ ቢኾን እንደ ሳይንቲስት ቅጣው እጅጉና፣ ሳይንቲስት ዶ/ር መላኩ ወረደን ፣ ሳይንቲስት  አክሊሉ ለማን ፣    ኢንጅነር ኃይሉ ሻወልን የመሳሰሉ የሀገራቸውን ሥም በዓለም ያስጠሩ ምርጥ ሀገር ወዳድ የአማራ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ልሂቃንን እናገኛለን።   የአማራው ማህበረሰብ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያልተቋረጠ እድገትና ክብር ያበረከተውን ወደር የለሽ አስተዋጽኦ ለማበርከት ያስቻለው ሥልጣኔው የወለደው እምቅ አእምሮአዊ  አቅሙን ስንመለከት፤ አማራውን ወያኔ በሠራለት ክልል ዙሪያ  አስተሳሰቡን አጥሮ ማስቀረት እንደማይቻል እንረዳለን። የአማራ ንቃተ ህሊና (spiritually oriented brain power)  ኢትዮጵያን አካሎ ዓለም ላይ ለሚከናወኑ  በጎም ኾነ አሉታዊ ክስተቶችና ክንውኖች የመፍትኼ አካል በመኾን  አስተዋጽኦ ማድረግ የሚችል አቅም ያለው ነው። ለዚኽ ነው  እነ እስክንድር ነጋ ‘መነሻችን የአማራ ህልውና መዳረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት’ የሚለውን ጽነሰ-ሃሳብ ሲያመነጩ  የአማራን አእምሮአዊ፣ ስነልቦናዊ፣ መንፈሳዊ  ልእልናውን የሚመጥን   ኢትየጵያዊ  ማንነቱን  ግንዛቤ ውስጥ የሚያስገባ ያደረጉት። ከኢትዮጵያ ያነሰ መዳረሻ የአማራውን ማህበረሰብ አይመጥነውም የሚባለውም ለዚኽ ነው።  ነብር ዥንጉርጉርነቱን እንደማይቀይር አማራም ኢትዮጵያዊ መልኩን አይቀይርም። አማራው በቅዱስ መጻህፍት ከ40  ጊዜ በላይ  የተጠቀሰበትን ኢትዮጵያዊ ሥሙን ሊቀይርም አይችልም። ለአማራው ኢትዮጵያዊነቱን ተው ማለት፤  የአንገት ማተብህን በጥስ እንደማለት የሚቆጠር ነው።   አማራው አሁን እየተፈጠረ ባለው  የዓለም ኃያላን ሀገራት አዲስ  አሰላለፍ (Multi polar world)   ሀገሩ ኢትዮጵያን  በዓለም ላይ ካሉ የአካባቢ ሀገራት ኃይሎች (Regional Powers) አንዱ የማድረግ አቅምም አለው። ከዚኽ በፊትም አድርጎት ያውቃል። በዓለም ዲፕሎማቲክ መድረክ  ላይ ከፍተኛ የአእምሮ ብቃትን የሚጠይቀውን የሀገር ጥቅምን ለማስከበር የሚደረግ ዲፕሎማሲያዊ ድርድሮች (art of negotiations) በጥበብ በመጫወት ኢትዮጵያን   ከዲፕሎማሲ ሱፐር ፓወር ሃገራት ተርታ እንድትሰለፍ ያደረገው፣  የአማራው ነገሥታት የእነ ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክና የቀዳማዊ ዐፄ ኃይለሥላሴ ዘመን ጥበብና ብልሃት የተመላበት አመራር ነው። ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በዃላ ዓለም በሁለት አይዲዮሎጂካል ጎራ ተከፍላ፤    የቀዝቃዛው ጦርነት ተፋላሚዎች  በተፋጠጡበት ዘመን፣ በኹለቱም ተፋላሚዎች  በኒውዮርክ በጆን.ኤፍ ኬነዲ፣ በሞስኮ  በሶቭየት ህብረቱ መሪ ኒኪታ ክሩስቼቭና፣ በቤጂንግ የቻይናን አብዮትን በመራው ማኦ ሴቱንግ ይደረግላቸው የነበረውን ደማቅ አቀባበል ስናይ ኢትዮጵያ፣  በጊዜው የዲፕሎማቲክ ሱፐር ፓወር እንደነበረች  እንገነዘባለን።

A car driving on a road with a banner above it Description automatically generated

አማራው በአጭር ጊዜ ሀገሩ ኢትዮጵያን ወደ ትክክለኛው የሀገር አንድነት አቅጣጫ በመምራትና በማሳደግ በዓለም አቀፉ  የጂኦ ፖለቲክስ መድረክ ኢትዮጵያ የነበራትን ቦታ ለማግኘት የሚያስችሉ  የሥልጡን ህዝብ መመዘኛ የኾኑ  በቂ የባህል፣  የሃይማኖት፣ የቋንቋ ፣ የሥነ-ጽሑፍ፣  የሙዚቃ ፣ የፍልሥፍና  የጀግንነት ታሪካዊ እሴቶቿን በመጠቀም፣ ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለአፍሪካውያን ወንድሞቿ  ተምሳሌት  በመኾን አፍሪካን  ቀፍድዶ ከያዘው የልሂቃን አእምሮን የመቆጣጠር  (elite colonization)፣ ዘመናዊ የቅኝ ገዢዎች ስልት ለማላቀቅ  እየተደረገ ያለውን እውቀት-መር ትግል በመቀላቀል አፍሪካን  እንደቀደሙት አባቶቹ ወደ ነጻነት እንዲመራም ይጠበቃል።

የዛሬ 60 ዓመት ገደማ ነጮቹ በተለያየ መንገድ የመለመሏቸው፣ ከመላው ኢትዮጵያ የመጡ ተማሪዎች፤  በዃላ ነጻ አውጪ ግንባር በየፊናቸው በማቋቋም፣  ሀገራቸው ኢትዮጵያን  የወጉ፤ የአዲሱ የልሂቃን ቅኝ ቅአገዛዝ (elite colonization) ስልት ሰለባ በመኾናቸው ነው። አሁንም ኢትዮጵያዊነትንና ኢትዮጵያን የሚያስቀድመውን  አማራውን እየወጉ የሚገኙት የኦሮሙማ ፖለቲከኞች፣ የቀደሙት ኦነጋውያን ያስተላለፉላቸው የነጭ አምላኪነት የባንዳ አስተሳሰብ ላይ የተመሠረተ የጎጠኝነት አስተሳሰብ ወራሾች ናቸው። እነዘኺ  የነጮችን ጫማ መላስ የሚወዱ ታሪክ ጠል ባንዳዎች፣ ፍርፋሪ በተገኘበት የአረብ ሀገራት ሁሉ ልመና የሚሰማሩ የኢትዮጵያ ታሪክና ክብር ምን እንደኾነ የማይገባቸው፣  ሀፍረት የሚባል ነገር የማያውቁ ቁስ ብርቃቸው የኾነ ፤  የሀገረን ሉአላዊነት አሳልፈው ለጠላት የሚሰጡ (useful idiots) ናቸው።

እንግዲኽ ‘መዳረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት’ ሲባል የዘመናችን ዐፄ ላሊባል፣ የዘመናችን ዐፄ ዘራ ያእቆብ፣ የዘመናችን ንጉሥ ተክለሃይማኖት፣ የዘመናችን ፣ ዐፄ ቴዎድሮስ፣ የዘመናችን ዐፄ ምኒልክ፤  የዘመናችን ዐፄ ኃይለሥላሴ፤ ከአዲሱ የአማራ ፋኖ ትውልድ  እንዲበቅል መንገድ መጥረግ ነው። ይህን መንገድ በመጥረግም የኢትዮጵያን ህዝብ አድነትና ሉአላዊነት ማረጋገጥ ነው።

‘መነሻችን አማራ መዳረሻችንም አማራ’ ዋና አቀንቃኝ እነማን ናቸው?

የዚኽ የአዛኝ ቅቤ አንጓች  መርዘኛ ዓላማ፤  ዋና ባለቤት፣  አማራን ሲያስቀጠቅጥና ሲያስመታ የኖረው፤ አሁንም የአማራ ፋኖን የድል ጉዞ  ለማስተጓጎል፣ ሌት ተቀን እየሠራ ያለው  የብአዴን ቡድን ነው።  በሁለተኛ ደረጃ የመንግሥት ሥልጣንን የተቆጣጠረው በአውሬው የሚመራው የኦሮሙማ ኃይል  በተከፋዮቹ በኩል  ይህን መሰሪ ዓላማ እያሰራጨ ይገኛል። በሶስተኛ ደረጃ የተሰለፉት፣  ከብአዴን ጋር ንክኪ ያላቸው በአማራው ሥም የሚንቀሳቀሱ በሀገር ውስጥ ከብአዴን እንዲኹም በውጪ ከሚገኙ የብአዴን ክንፎች ጋር ተቧድነው የአማራን ህልውና እንታደጋለን የሚሉ ናቸው። እነዚኽ ኃይሎች የአማራን ህልውና  የመጨረሻ ግብ  አድርገው የተነሱ ቢኾኑም፣ የአማራን ህዝብ ከብአዴን ነጥለው ማየት ያልቻሉ ናቸው። በመጨረሻ ረድፍ የተሰለፈው ከጀርባ ከባድ ሥራ እየሠራ ያለው የወያኔ ርዝራዥ ኃይል ነው። ይኽ ኃይል አንድ አማራ የሚባል ግሩፕ በአማራው ትግል ውስጥ አስርጎ በማስገባት ከፍተኛ አማራውን ፋኖ ህብረት  ለመከፋፈል፣ምስጢር ለመለቃቀም በተለይም በእነ-እስክንድር ላይ በማተኮር መሰሪ  የፕሮፓንዳ ሥራ በሥፋት እየሠራ የሚገኝ ኃይል ነው።

‘መነሻችን አማራ መዳረሻን አማራ’ የሚለው ቡድን ፕሮፖጋንዳ  ምን ይመስላል 

ኢትዮጵያዊነትን ከሚያክል፤ ፈሪሃ እግዚአብሄር ላይ የተመሠረተ ለሺ ዘመናት የኖረ፣  በቅዱሳን መጻሕፍት የተገለጠ፣  በእግዚአብሄር ህልውናው የሚታወቅን ረቂቅ    ማንነት፤ በአማራው ብቻ ሳይኾን በተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብም ጭምር የተወገዙና የተተፉ ባንዳ ፖለቲከኞች፤ ከእነ ብርሃኑ ነጋና አንዳርጋቸው ጽጌ(ግንቦቴዎች)  ጋር በማያያዝና ሌሎች ኢትዮጵያዊነትን ለመወከል፣ የእውቀት ውሱንነት ያለባቸው  ወያኔ ሠራሽ የፖለቲካ ቡድኖች፤  በአማራ ላይ የሚሰጡትን ወቅታዊ  አሉታዊ አስተያየቶች እያጣቀሱ ፤    አማራው የአስተሳሰብ አድማሱን አጥብቦ በነዚኽ ‘ኢትዮጵያኒስት’ ብለው በሚጠሯቸው አቅመ-ቢስ (incompetent) ፖለቲከኞች ሚዛን ኢትዮጵያን እንዲመዝናትና፣ እንዲጠላት ለማድረግ ነው።  ሌላው  አማራው ኢትዮጵያዊነቱን እንዲጠላ ለማድረግ እየተጠቀሙበት ያለው ትርክት፣   ነብሰ በላው ደርግንና፣ በ’አብዮቱ’ ዘመን የነበረውን የተማሪዎች እንቅስቃሴ የመሩ፣ ፀረ-አማራና ፀረ-ኢትዮጵ አቋሞችን ያራምዱ የነበሩ ተከታዮቻቸውን ያሳሳቱ፣  እግዚአብሄርን የካዱ የኮሙኒስት አይዲዮሎጂ አቀንቃኝ ኃይሎችን ቁንፅል ታሪክ በመጠቃቀስ   ‘ኢትዮጵያኒስት’ የሚል ስም  በመለጠፍ ነው።  ብአዴናውያን እንደዚኽ ያሉ እርባና ቢስ ሃሳቦችን በየሶሻል ሜዲያው ተከፋይ  በቀቀኖቻቸው(parroters) አማካኝነት ወደ ህዝብ በማሰራጨት፣  አማራው  ከ1966ቱ ለውጥ ጊዜ ጀምሮ ከመጠቃት ውጪ ከኢትዮጵያዊነቱ ምንም ትርፍ አላገኘም ስለዚኽ ኢትዮጵያዊነቱን ትቶ በአማራነቱ ብቻ መወሰን አለበት ወደሚል አደገኛ ድምዳሜ እንዲደርስ፣ አደገኛ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ እያደረጉ ነው። ብአዴናውያን አብዛኛውን ዘመናቸውን ለወያኔ አሁን ደግሞ ለአውሬው በመገበር ጊዜያቸውን ያሳለፉና እያሳለፉ ያሉ የአሽከርነት ጠባይ የተጠናወታቸው ድኩማኖች በመኾናቸው፣ ኢትዮጵያዊነትን የመወከል አቅም የላቸውም።  በመኾኑም፣ አዲሱ የአማራ ወጣት ትውልድ አባቶቹ የገነቧትን ኢትዮጵያን መልሶ በእጁ ከጠላት አውሬው መንጋጋ አውጥቶ ለመረከብ ቆርጦ  በተነሳበት በአሁኑ ወቅት፣ ‘መነሻችን አማራ መዳረሻንም አማራ’ የሚል ከእነ እስክንድር መሪ ቃል ተገንጥሎ በተኮረጀ ነገር ግን   ፀረ-አማራና ፀረ-ኢትዮጵያ  ይዘት ያለው  ሃሳብ ይዘው  ብቅ ብለዋል።

ይህን መርዘኛ አስተሳሰብ በአማራው ላይ  ለማስረፅ   በፕሮፖጋንዳው መስክ   በዋነኛነት  ከብአዴን ጋር ንክኪ ያላቸው ከአማራ ክልል እስከ አሜሪካ ኔትወርካቸውን የዘረጉ ተከፋይ የፕሮፖጋንዳ ሠራዊት፤ በሰፈር  በጎጥ ተቦዳድነው በተለያየ ሥም የአማራ ማህበራትን በማደራጀት ዶላር የሚለቃቅሙ ብአዴናውያን፤  እንዲኹም የአማራው ትግል አስተባባሪና ደጋፊ በመምሰል ሰርገው በገቡ ‘አንድ አማራ’ የሚል ስያሜ ያላቸው  ወያኔ ያሠማራቸው ደፋርና አይን አውጣ ብልጣ ብልጦች ቀጥታ ተሳታፊነት እንዲሁም በአውሬው የሚመራው ኦሮሙማ የፕሮፖጋንዳ ሠራዊት በድጋፍ ሰጪነት እየተሳተፈ ያለበት ነው። ከነዚኽ በተጨማሪ በዶላር የተገዙ  አክቲቪስቶችን፤ የፋኖ ደጋፊ ማስመሰያ  ማስካቸውን አውልቀው፤  በግልፅ   የአማራ  ሕዝባዊ ሠራዊት ፋኖን ትግል ለማደናቀፍ፣  የሃሰት  የሥም ማጥፋት ዘመቻ ፕሮፖጋንዳ   በአማራ ህዝባዊ ሠራዊት ላይ እየሠሩ ይገኛሉ።    ከውጪ ነባር የዓማራ ጠላቶቻችን ደግሞ በተለይ፤  አውሬውን ወደ ሥልጣን ያመጡት ሳታኒስት ግሎባሊስት ኃይሎች፤  የአማራውን ፋኖ የህልውና ትግል የሚደግፉ እንደ ኢትዮ 360 ያሉ እውነተኛ የህዝብ ድምፆችን፤ ተከታትለው፣  የሜዲያ ቻናሎቻቸውን በመዝጋት  እየተባበሩ ይገኛሉ። በሌላ በኩል አውቀውም ይሁን ሳያውቁት አማራን ከኢትዮጵያ ለመነጠል ‘ኢትዮጵያዊ አስተሳሰብ’ ላይ ጥላቻን የመንዛት  የክህደት አካኼድን እንደ ልዩ አማራን ነፃ ማውጫ አቋራጭ ስልት በመውሰድ፤ የአማራው ፋኖ በፀረ-ኢትዮጵያዊነት አስተሳሰብ ከወያኔዎቹና ከኦሮሙማው ጎጠኛ ቡድኖች ጋር እንዲፎካከር ለማድረግ እየሰበኩ ካሉት እራሳቸውን፣ የዘመኑ የአማራ ብቸኛ ተቆርቋሪ ልሂቃኖች አድርገው የሚቆጥሩ እንደ ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኝ ያሉ ጅላጅል ምሁራን(intellectual morons)  ናቸው። በሚያሳዝን ሁኔታ እነ ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኝ  የአውሬውን የኦሮሙማ ሥርዓት የሚታገለውን የአማራ ፋኖ ሙሉ በሙሉ መደገፍ ሲገባቸው፣ በአሁኑ ሰዓት የአውሬውን  የኦሮሙማ ሥርዓትና ብአዴንን መሬት ወርዶ እየታገለ ያለውን ፋኖ እስክንድር ነጋን  ያለምንም  እረፍትና እፍረት በየሜዲያው ብቅ እያሉ ሥሙን ለማብጠልጠል ሰፊ ዘመቻ ሲያደርጉበት ስናይ የነዚኽ ኃይሎች ዋና ዓላማ በቅድሚያ የአማራን ህልውና ለማስገኘት ሳይኾን አማራውን ሲያስቀጠቅጥ የሮረውን የብአዴንን ቡድን ህልውና ለማስቀጠል እየሠሩ እንደኾነ መገንዘብ አያስቸግረንም።

‘መነሻችን አማራ መዳረሻችንም አማራ’ ዋና ዓላማው ምንድን ነው?

ከአውሬው ኦሮሙማ ቡድን መሪ  አብይ አህመድ ፍላጎት አንፃር ሲታይ ፦

  •  ፋኖ ከለቀቀበት ጭንቀት ለመገላገል፤  ፋኖ ከአማራ ክልል እንዳይወጣና፣ ወደ አባቶቹ ከተማ ወደ አዲስ አበባ የሚያደርገውን ጉዞ እንዲገታ ለማድረግ  ነው።
  •  አዲስ አበባ የጀመረውን የከተማዋን ነዋሪ ከጥንት ይዞታው የመንቀልና የከተማዋን ታሪካዊ ገጽታ የማውደም ሥራ ፤  ከፋኖ ”እየመጡ ነው”  ስጋት  ውጪ ኾኖ- የጥፋት ተልእኮውን ለማስቀጠል ነው።

ከብአዴን ፍላጎት አንፃር ሲታይ፦

  •  የብአዴን ቡድን ክልላዊ ሥልጣኑን በማራዘም በአማራው ጫንቃ ላይ ተቀምጦ የገነባውን ከአማራ እስከ አዲስ አበባና ፈረንጅ ሀገር የተዘረጋውን ከከርስ ያላለፈ በቤተሰብ የተጠላለፈ የሌቦች  የቢዝነስ ኢምፓየር  ለማስቀጠል ነው።

ፀረ-አማራ ፖሊሲ ካላቸው የሀገር ውስጥ ባንዶችና የውጪ ጠላቶቻችን   አንፃር ሲታይ፦ 

  • አማራው ተመልሶ  ወደ ማእከላዊ የሥልጣን መንበሩ እንዳይመጣ ለመከላከል ነው።
  • የአማራው ማህበረሰብ ኢትዮጵያን ከመሠረተበት የሃሳብ ልእልናው አውርዶ፣ ከተራ የጎጠኞች ረድፍ  በማሰለፍ፤  ልክ እንደ ፈረንጅና አረብ  አምላኪ ባንዳዎቹ ወያኔዎችና ኦነጋውያን ኦህዴድዶች፣ በትግሬ ህዝብና በኦሮሞ ወጣት ላይ ያሰረጹትን  ፀረ-ኢትዮጵያዊነት አይዲዮሎጂ  በአማራው ማህበረሰብ ወጣት ትውልድ ላይም በማስረፅ  መጽሐፍ ቅዱሳዊቷን ኢትዮጵያን ለማጥፋት ነው።
  • አማራውን ከኢትዮጵያዊነት በማራቅ ከጥንታዊ ታሪኩና ሥልጣኔው ጋር ያለውን ቁርኝት  ለመበጣጠስ የታለመም ነው።
  • አማራውን ብቻውን በማስቀረት፤ ወደ ትንንሽ  ጎጥ ተከፋፍሎ፣ ወያኔ በከለለት ድንበር ተወስኖ እርስ በርሱ እየተጣላ እንዲኖር   ለማድረግ ነው።
  • ወያኔ እንደሚመቸው ከሠራው የአማራ ክልል ድንበር ውጪ የሚኖሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አማሮች፣   አውሬው የኦሮሙማ ሸኔ ቡድን የጀመረውን ጭፍጨፋና፣  ከቅዬአቸው የማሰደድ ተግባር እንዲቀጥልበት መንገድ ለመክፈትም ነው።
  •  አውሬው አብይ አህመድ፤ ኒው-ሊበራል ግሎባሊስት አይዲዮሎጂ (neoliberal globalist ideology)  አራማጅ ኃይሎች፣  ወደ ሥልጣን ሲያመጡት ቃል ያስገቡትን  ሃይማኖትን የመበረዝ፣የማንቋሸሽና የማጥፋት ዘመቻውን፤ አማራውን ከኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረክ  በማግለል  በቀላሉ ተግባረዊ ለማድረግ ነው።
Filed in: Amharic