ይድረስ ለዘመነ ካሴ እና ለአስረስ ማረ ዳምጤ (ክፍል ሁለት)
ዘላለም ይግዛው
ለአለፉት አስርት ዓመታት በፀረ አማራ እሳቤ በተጠመቁት በህወኃት እና በኦነጋውያን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ መነሻነት በአማራ ህዝብ ላይ በርካታ ዘግናኝ እና አሰቃቂ ግድያዎች ተፈፅመዋል፡፡ በአማራነታቸው ወጣቶች በወጡበት ቀርተዋል፡፡ በአማራነታቸው ሰዎች ተፈናቅለዋል፣ ተገድለዋል። በምዕራብ ሸዋ፣ በአርሲ፤ ፤በምስራቅ ወለጋ፣ በሆሮ ጉድሩ ዞን፣ በሆሮ ጉድሩ ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ እና አቤ ደንጎሮ ወረዳ፣ በምዕራብ ወለጋ፣ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ፣ ቆንዳላ ወረዳ፣ በምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ጅባት ወረዳ፣ ዳርጌ ቀበሌ፣ አምቦ ወረዳ መንቃት ቀበሌ፣ በቄለም ወለጋ ዞን፣ በዶዶላ፣ በአርባ ጉጉና በበደኖ፣ ሻሸመኔ፣ ዝዋይ፣ አርሲ፣ በመተከል፣ አጣዬ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ በኦሮሚያ፣ በደቡብ እና በሌሎችም ክልሎች በተለያዩ ጊዜዓት በተደጋጋሚ ከ1983 እስከ አሁን ድረስ የአማራ ተወላጆች በጥይት ተጨፍጭፈዋል፤ አሰቃቂ በሆነ አገዳደል ህይወታቸው አልፏል፤ በቀስት እየተወጉ ተገድለዋል፣ በኦነግ ሸኔ በጥይት ተጨፋጭፈዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦነጋዊው ጭራቅ አብይ አህመድ በአማራ ክልል ገብቶ የሚፈፀመውን ግፍ በመቃወም በርካታ ወጣቶች ወደ ጫካ በመፈነን የፋኖነት ትግሉን ተቀላቅለዋል፡፡ አብዛኛው የአማራ ወጣቶች በአማራ ላይ የተሰነዘረው ጥቃት ለመመከት የፋኖነት ትግሉን ቢቀላቀሉም እንደ ዘመነ ካሴ እና አስረስ ያሉ የታሪክ ባለእዳዎች በአማራ ወጣቶች ደም ለስልጣን ሲሻኮቱ ማየት ምንኛ ያሳፍራል፡፡
ዘመነ ካሴ እና አስረስ የራሳቸውን ያልተገራ ፍላጎት ማረቅ ያልቻሉ፣ በወንድሞቻቸው ደም ተድላን የሚናፍቁ፣ የትግል አጋራቸውን ስም የሚያጠለሹ፣ ከሚፈሰው የአማራ ደም ይልቅ በግል ጥቅማቸውን የታወሩ የታሪክ እና የህግ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡
ከእስክንድር ጋር ማናችሁም ልትወዳደሩ አትችሉም፡፡ አቅማችሁን እወቁ፡፡ እናንተ ወደ ጫካ የወጣችሁት ለስልጣን ብላችሁ እንጅ የአማራ ደም ግድ ብሏችሁ እንዳልሆነ ስራችሁ እየመሰከረ ነው፡፡ ከእስክንድር ጋር ሊወዳደር የሚችል እና እርሱን የመተቸት አቅምም ሆነ ድፍረት ማንም ሊኖረው አይችልም፡፡ “ነብይ በሀገሩ አይከበርም ” እንደሚል መፅሀፉ እስክንድርን ማክበር አልችል ብለን እንጅ እስክንድር እንደ መሀታማ ጋንዲ፣ እንደ ኒልሰን ማንዴላ፣ እንደ ማርቲን ሉተር ኪንግ ሊከበር ሊወደስ ሊዘከር የሚገባው እንቁ፣ እውነተኛ፣ ጨዋ፣ እና የፅናት ምልክት የሆነ ታጋይ ነው፡፡ እስክንድር በዘመናት መካከል የተከሰተ አብሪ አጥቢያ ኮከብ ነው፡፡ በሰልጣን የታወሩት ዘመነ እና አስረስ ይቅርና ማንም(አሁን ባለው የፖለተካ ሜዳ) ከእስክንድር ጋር ሊወዳደር የሚችል አንዳች ሰው የለም፡፡ አርበኞችን ባንዳዎች ሲተቹ አዝማሪ እንዲህ ብሎ ነበር፤ ይህች አባባል እናንተንም በጨረፍት ትመለከታለች፡
ቃርሚያ ውስጥ ያደጉ የነቀርሳ እባጮች
አፍ ሲከፍቱ ታዩ በነዚህ ቆራጥ ዘማች
እስክንድር አብሯችሁ ትግሉን ስለተቀላቀለ እኩያችሁ አይምሰላችሁ፡፡ አቅማችሁን እወቁ እንጅ፡፡ እናንተ እኮ በፋኖ ምርቃት ላይ እየተገኛችሁ ንግግር ማድረግ እንጅ ውስጥ ለውስጥ ስራ ስትሰሩ አትታወቁም፤ እናንተ እኮ የድል አጥቢያ ጀግኖች ናችሁ እንጅ ውጊያ ውስጥ ተገኝታችሁ አታውቁም፤ እናንተ እኮ የብዓዴን ርዝራዥ ናችሁ እንጅ ከገዥው ፓርቲ ንኪኪ የፀዳችሁ አይደላችሁም፤ እናንተ እኮ የፖለቲካ ትግልን ለሀብት ማፍሪያ እና ለስልጣን መወጣጫ እንጅ የአማራ ህዝብ ደም ከርፍቶዓችሁ አይደለም ወደ ትግል የገባችሁት፤ እናንተ እኮ የበርካታ ሰዎች ደም እጃችሁ ላይ ይጮኃል፤ እናንቶ እኮ ሀሳባችሁ፣ ልባችሁ፣ አንደበታችሁ ያልተገራ ወፈፌ ናችሁ፤ እናንተ እኮ በሚዲያ ድጋፍ የቆማችሁ ድል ነጣቂዎች ናችሁ፡፡ ተው አደብ ግዙ፡፡
የእነርሱን ዓላማ በምታስተጋቡ ሚዲያዎች (መረጃ ቲቪ፣ ግዮን ቲቪ፣ ሕብር ሬድዮ፣ ሮሀ ሚዲያ) በድርጊታችሁ ልታፍሩ ይገባል፡፡ በሸዋ፣ በጎንደር፣ በወሎ እና በጎጃም በርካታ ቆራጥ ፋኖዎች እንዳሉ እየታወቀ የፋኖ ምልክት ተደርገው እነዚህ ሁለት ግለሰቦች የሚቀርቡበት ምክንያት ምንድን ነው? የምታቀርቡት ዘገባ ሚዛናዊ አይደለም፡፡ የመዓዛ መሀመድ፣ በመስከረም አበራ፣ በዘመነ ካሴ፣ በይልቃል ጌትነት፣ በገዱ አንዳርጋቸው መካከል ያለውን እና የነበረውን ትስስር እናውቃለን፤ ሁኖም እናንተም አደብ ግዙ፡፡
ቸር እንሰንብት
አማራ እንደ ፈጣሪ ፈቃድ በክንዱ ታሪኩን ያድሳል
በትግሉ ለተሰው ታጋዬች ዘላለማዊ እረፍትን ፈጣሪ ይስጥልን