ሰሞኑን ዶክተር ሚሊኬሳ፣ አቶ ታየ ደንዳና ጃዋር ሙሃመድ አብይ ዐማራን ማጥፋት አለብኝ ማለቱን አስረግጠው እየነገሩን ነው።
መቼስ ብሩኩና ሰው ማመን የማይሰለቸው ዐማራ እያደነቃቸው ነው።እነዚ ፖለቲከኞች በሰው ልጅ ላይ( በዐማራ) የቆመሩት በተለይም ደግሞ መላው የኦሮሞ ህዝብ አእምሮ በዐማራ ላይ የማይሽር የጥላቻ ግንብ እንዲሰራ ጠላትነትም እንዲያዳብር ማድረጋቸው ጸጽቷቸው ንስ ሃ እየገቡ ከሆነ እጅግ መልካም ነው።
ነገር ግን ባዶ ንሰሃ ዋጋ የለውም። ንስሃ ፍሬ ሊያፈራ ይገባዋል፤ የንስሀ ፍሬ ማለት ደግሞ ያጠፉትን ጥፋት መተው ወደነበረበት መመለስና መካስን ይጨምራል። ዐማራ ጨቋኝ ነው፣ ዐማራ ወራሪ ነው፣ ዐማራ ቀማኛ ነው፣ ከዐማራ ጋር የምንጋራው ታሪክም ሆነ ባህል የለንም፣ ዐማራ የኦሮሞን ጡት ቆርጧል፣ ዐማራ ኦሮሞን ፈጅቷልና ሌሎችንም ለጊዜው በሚዲያ መናገር የማንደፍራቸውን ጸያፍ ፕሮፓጋንዳዎች ሲተርኩ የኖሩና ለዐማራ ጭፍጭፋ የአንበሳውን ድርሻ ሲዎስዱ የኖሩ ጉምቱ ፖለቲከኞች ናቸው።
ቤተልሄም ታፈሰ ሁሉንም ስታንቋሽሽ ሰምተናል፣ እነሱም ዐብይ አህመድ አውሬ እንጂ ሰው ያለመሆኑን በተለይም ዐማራን በተመለከት የሚከተው ፖለቲካ ዐማራን ለማጥፋት መሆኑን በሚገባ እየነገሩን ነው። እነሱንም ሆነ ዐብይ አህመድን ዐማራን ለማጥፋት ትርክት እንዲፈጥሩና ለዚያም ተግባራዊነት ፕሮፓጋንዳ በመስራት በኦሮም ሆነ በሌላው ህዝብ አእምሮ ጸረ ዐማራ ሪእዮት እንዲሰርጽ ያደረጋቸው ስርዓቱ መሆኑንና እነሱም የስርዓቱ አገልጋይ ወንጀለኞች መሆናቸውን ግን አንድም ቦታ አልነገሩንም ።
ራሳቸውን ግን መልዓክ አድርገው እየነገሩን ነው። የንስሃ ፍሬም እያየን አይደለም፤ እውን በዐማራ ላይ የተፈጸመው የዘር ጭፍጭፋ ፣ አኖሌ ሃውልትን ጨምሮ በትውልዱ የሰረጸው የሃሰት ትምህርትና ታሪክ የፈሰሰው ደም የጠፋው የሰው ልጆች ህይወት አሳስቧቸው ፣ ጸጽቷቸውና ራሳቸውንም በደለኛ አድርገው የሃሰት ትርክቱን ለመቀልበስና ለሰሩት ወንጀል ለመጠየቅ ወስነው ይሆንን ? ጊዜ ሁሉን ያሳይናል፤ ዐማራም ”አያሌው ሞኙ ሰው አማኙ ” ሆኖ የሚቀጥልበት ዘመን አብቅቷል፣ አብይም ሆነ ሌላው የስርዓቱ አገልጋይና በዐማራ የዘር ጭፍጨፋ ተዋናይ ሁሉ ወደ ሚገባው የፍርድ ወንበር ይቀርባል።
ዐማራ ለህልውናው እየታገለ ብቻ ሳይሆን የሚሆነውን ሁሉ እያየ፣ እየሰማ ሰነዶችን እየሰነደ ማስረጃዎችን እያሰባሰበና ወንጀለኞችን ሁሉ በፈጸሙት ወንጀል መጠን ለመጠየቅ ትውልድ እያነቃ ነው።
ዐማራ ያሸንፋል !
ድል ለተገፋው ህዝባችን !
ጋሽ አዲስ ⇓
@Amharasurv78790