>

“አዲሱን የወይን ጠጅ በአሮጌ አቅማዳ አይፈቀድም” ተኳሹም ነጋሹም ፋኖና ፋኖ ብቻ ነው

አዲሱን የወይን ጠጅ በአሮጌ አቅማዳ አይፈቀድም”

ተኳሹም ነጋሹም ፋኖና ፋኖ ብቻ ነው

 

“ሱሪውን ብቻ ሳይሆን ቀበቶውንም ጭምር በሶሰት ሳምንት እናስፈታዋለን”ያለው ምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ ከአጋንንቱ አለቃውና ጨፍጫፊው (Genocider) አብይ አህመድ በተሰጠው ትዕዛዝ የተጀመረው አማራን እንደ ህዝብ ከኢትዮጵያ ምድር የማጥፋት ዘመቻ እንደተባለው ሳይሆን በተቃራኒው ወደ ሶስተኛ አመት በፋኖ የበላይነት ተሸጋግሯል ።ቀበቶ አሰፈቺው ሃይልም የራሱን ቀበቶ በአግባቡ መታጠቂያ ጊዜ እና ወገቡ ጠፍቶበት ቀንዱን እንደተመታ በግ ሲዞርበት እያየን ሰነባበትን ።የአማራ ህዘብ ራሱን ከመጥፋት ለመከላከል በጀመረው የህልውና ትግል ሂደት ብዙ ሊታመኑ የማይችሉ ድሎችና ለመጪው የአማራ ትውልድ መማሪያ መፃህፍት የሚሆኑ የጀግንነት ድርሳኖች ተፅፈው እያለፋ ነው።

ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በተከማቸ ግፍ :ግድያ :ማፈናቀል :አስገድዶ መድፈር መሰወርና በፓለቲካ በኢኮኖሚ :በማህበራዊ እንዲሁም በሥነ ልቦና ጥቃት የተማረረው ህዝብ በቁጭት ከመብሰልሰል ተሻግሮ በአባቶቹ የአሸናፊነት ወኔ በመነሳቱ ወራሪውን የኦነግ አራጅ ሃይል በሚገባው ልክ መልስ ሰጥቶታል ።በድሉና በጀግንነቱም አለም ተገርሞበታል።

ይህ በእልህና በጀግንነት የተገኘው የህልውና ትግል ውጤት ከትናንት ዛሬ የበለጠ እየጠራ ሲመጣ ብዙዎች ጀግኖች የተሰውለትን የፋኖ ትግል በገረጀፈው የሴራ ፓለቲካ ጠልፎ ስልጣን ላይ ለመንጠላጠል ያሰፈሰፉ በርካታ ቡድኖች ትናንት በሄዱበት መንገድ ዛሬም ከፊት ለመሰለፍ ሻንጣ ሲያማራጡ እያየን እንገኛለን ።

በአንድ በኩል ፋኖ አንድ ወጥ አደረጃጀት የሌለው በመሆኑ ድሉ ዘገዬ እያሉ የፋኖ አደረጃጀት እንዳይሰማማ መርዝ እየረጩ በሌላ በኩል አሸማጋይና አማካሪ በመሆን የተሰለፉ ትግል ጠላፊዎች ከወዲሁ አደብ እንዲገዙ መደረግ ይኖርበታል ።

ከአንድ ወር በፊት በሰሜን አሜሪካ ሲሊቨር ስፕሪንግ የምስጋና ፕሮግራም የተዘጋጀላቸው ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ የሚመሩት ሰብስብ :ልደቱ አያሌው ያከማቸው የኦነግ የህወሓት እና የአብይ አባባ አቀባይቹ እነ አንዳርጋቸው ፅጌን ነአምን ዘለቀንና ሌሎችም የኢትዮጵያ ፓለቲካ ደላሎችን የያዙ ሰዎች በደም የተገነባውን የፋኖ ትግል አራት ኪሎ ለመቀበል በልዩ ልዬ እንቅስቃሴ ውሰጥ መሆናችሁን አውቀናልና እረፉ።

አርበኛ እስክንድር ነጋ ወጥቶ መግለጫ በሰጠ ቁጥር የሚነሰራችሁ እነ መአዛ መሐመድ :ተስፋዬ ወልደስላሴ እንዲሁም ኢሳት ውስጥ እያለ “ከእንግዲህ ሰሜን መንገስ የለበትም “በማለት ጓዶችህ የሚያውቁህ መሳይ መኮንን የግል ሽቀላህ ላይ ብቻ እንድታተኩር እንመክራለን ።

በዚህ አጋጣሚ እነዚህ ሦሰት ሰዎች የራሳቸውን የፋኖ መሪ ለመሾም በሸረቡት ሴራ “ዝሆን ነኝ”የሚል የፓለቲካ ጅል ፈጥረው የአማራን ሞት እንዲራዘም የቀሰቀሱና ያደራጁ አፋህድ ከተመሰረተ በኋላም ምሬንና ዘመነ ካሴን ያሰኮበለሉ ሴረኞች ናቸው ።

ዛሬ ላይም አሰረስ ማረ በራሱ “መንግስት መስርተናል “እያለ ከፋፋይ ሃሳብ የሚሰጠው በነዚሁ የአማራ ጠላት በሆኑ ሴረኞች ሚዲያ ላይ ነው። በሌላ መልኩ እነዚህ ፀረ አማራ ኃይሎች የኦነግና ወያኔ ህገ አራዊት እንዲቀየርና የብሄር ፓለቲካ ከተነካ ሰሚ የለንም ብለው ስለሚያምኑ የአፋህድን ሥር ነቀል ለውጥም ይሁን የትግል ማንፌስቶ ስሙን ጠርተው አያውቁም ።ይልቁንም አርበኛ እስክንድር ነጋን ማውገዝና ስም ማጥፋት የእነሱ የትግል ምዕራፍ መነሻና መድረሻ አድርገው ደምድመዋል ።

ምንም እንኳን አፋህድ እንደ ጀማሪ ድርጅት ማስተካከል የሚገባው ጉዳዬች ቢኖሩትም እንደ እስክንድር ያለ ትልቅ ስምና ዝና ያለው ላመነበት ዋጋ የሚከፈል :ያለመታከት ሰለአማራ ጥቃት ለሶሰት አስርት አመታት የታገለ:በስጋው አንዳች ሳይጎድልበት መንፈሱን ለህዝብ ነፃነት አሳምኖ የኩሬ ውሃ እየጠጣ የአማራን ሰቃይ የተካፈለ :ብዙዎች የውሸት ታሪክ ፈጥረው ጥገኝነት ከሚጠይቁበት ሃገር ትቶ ስለህዝብ ነፃነት ሲል ድሎትን በመከራ የለወጠ የዘመኑ አርበኛ ማግኘት ምንኛ መታደል ነው ?

እስክንድር የአማራ ልጅና ኢትዬጲያዊ ሆነ እንጂ በሌላ ሃገር ቢሆን በህይወት ዘመኑ ብዙ ቃለ መጠይቅ የሚደረግለት።ብዙ መፃህፍት የሚፃፉለት።ብዙ ተራኪ ፊልሞች ሙዚቃዎችና ቲያትሮች የሚሰሩበት ከእነ ፕሮፌሰር አሰራት ጀነራል አሳምነው ቀጥሎ የተገኘ የአማራ ህዝብ ድንቅ ስጦታ ነበር ።ግን እኛ መርገም እንጂ መመረቅ መች ታደልንና።እንዲህ አይነት ባህልን መሻገር ያልቻለ ማህበረሰብ ደግሞ ሁሌም ለአፈ-ጮሌዎችና አምባገነን መሪዎች ተላልፎ መሰጠቱ አይቀሬነት ወደ ኋላ የመጣንበትን ማስታወስ ይበቃል ።የሚገርመው አማርኛ የተናገረው ሁሉ ለአማራ እየተቆረቆረና ለትግሉ እገዛ እያደረገ በማስመሰል መሪ አልባ ሊያደርገን ሲሯሯጥ እኛም አብረን አጨብጫቢ መሆናችን ።

ወደ ማጠቃለያው እንጓዝ…

ዛሬ የአማራ ህዝብ እንዴት መታገልና ማሸነፍ እንዳለበት ከትናንት ሳይሆን ከአምና ተምሯል ።መሪ ማን ይሁን ብሎ በሩን ዘግቶ ይመክራል እንጂ ሽምግልናን እንደ እጩ ማቅረቢያ “ራስን የማስተዋወቂያ መድረክ “አድርጎ ለሚግተለተል የከሰሩ ፓለቲከኞች ስም ማደሻ እድል የሚሰጥ ፋኖ የለም ።በሻለቃ ዳዊት የምስጋና ምሸት ለሹመት ደጅ የጠናችሁ:በልደቱ አያሌው ስብሰብ የታጨቃችሁ የወያኔና ኦነግ ገዳይ አስገዳይ የአማራ ጠላቶች ከአማራ ትግል ላይ እጃችሁን አንሱ ።ካለሆነ ግን ከአሥመራ እስከ እርዳታ ማስተባበሪያ ከመንግሥቱ ኃይለማርያም እሰከ አብይ አህመድ :ከ1997 የአዲስ አበባ እልቂት እሰከ ጌታቸው አሰፋና ስብሃት ነጋ የተዘረጋውን የፀረ አማራ እንቅስቃሴ ።ከአርባጉጉ አርሲ እሰከ ተከበበኩ ድረስ በህዝባችን ላይ የተፈፀመውን ለአእምሮ የሚከብድ ዘግናኝ ወንጀል በየምዕራፉ እና በየሥማችሁ እየገለጥን እናሰጣዋለን።ለያላችሁበት ሃገር መንግስትም መረጃዎችን እናደርሳለን ።ዝም ያልነው ተረሰቶ ሳይሆን የቅደም ተከተል ጉዳይ ሰለተዘጋጀለት እንጂ ከእስር ሚሊዮን በላይ ህዝብ በግድያ በማፈናቀል በመሰወርና ማንነትን በማስቀየር ወንጀል የተፈፀመበት አማራ የሚረሳውም የሚተወውም በደል የለውም ።አይኖረውም ።

ከእንግዲህ የአማራ ትግልም ሰልጣንም የሚመራው በራሱ በታገለውና ባታገለው የአማራ ፋኖ እንጂ አዲሱን የወይን ጠጅ በአሮጌው አቅማዳ የሚሞላ አማራ የለምና እረፉ! እረፉ!

አዳባይ

አማራ ያሸንፋል
ገዳዬቹን ይፋረዳል!!

Filed in: Amharic