>
5:18 pm - Tuesday June 15, 2827

የህወሀት የጥላቻ መርከብ በኢትዮጵያ እየሰመጠ ነው?

ኢትዮጵያ፡ የህወሀት የሰመጠ የጥላቻ መርከብ ናትን

ከፕሮፌሰር አለማየሁገብረማርያም  

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የህወሀት  የጥላቻ መርከብ በፍርሀት እና በጥልቅ የጥላቻ ውቅያኖስ ውስጥ ሰምጧልን?

እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ እያለ የሚጠራው ወሮበላ Harvest-of-Hate Almariamየዘራፊ ቡድን ስብስብ ገዥው ወንጀለኛ ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ በማጭበርበር እራሱን መንግስት አስመስሎ ሆኖምግን ትክክለኛ የመንግስት ባህሪያትን በምንም ዓይነት መልኩ ሳይላበስ እስከ አሁን ድረስ በመግዛት ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ ባለፈው ግንቦት ወር ተካሄደ በተባለው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ይፋ በሆነመልኩ 90 የፖለቲካ ፓርቲዎች ተመዝግበው በሚንቀሳቀሱበት የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ለዝንጀሮ/ጦጣው የይስሙላፓርላማ ከተያዙት 547 መቀመጫዎች ውስጥ እንደ ቀድሞው ለይስሙላ አንድ እንኳ መቀመጫ ለሌላ የተቃዋሚፖለቲካ ድርጅት ሳያቃምስ 547ቱንም መቀመጫዎች መቶ በመቶ ድል አሸነፍኩ  ብሎ አለሃፍረት አወጀ፡፡

ሆኖም ግን ባለፈው ሳምንት የህወሀት የይስሙላ (አሻንጉሊት) ጠቅላይ ሚኒስትር የሆነው ኃይለማርያም ደሳለኝ ሁሉንምመቀመጫዎች መቶ በመቶ እንዳሸነፈ ሳይሆን እንደተሸነፈ ቅስሙ የተሰበረ አነጋገር አድርጎ ነበር።

 ኃይለማርያም እርዳታ እንዲደረግለት የመማጸን እና የመጮህ እንደምታ ያለው ስብዕናን በመከናነብ ይናገር ነበር፡፡ 

በእውነት ኃይለማርያም በስሜታዊነት መንፈስ ውስጥ በመዘፈቅመርከባችንን ልትሰምጥ ነው አድኑን” የሚል መልዕክትየሚያስተላልፍ መስሎ ታይቷል፡፡

…_ _ _… (በሞርስ ኮድ ማለት )

ኃይለማርያም ከየት እንደመጣ በማይታወቅ መልኩ የጦርነት መጥረቢያውን ከፍ አድርጎ በመያዝ በስሜታዊነት ከወዲያወዲህ እየተቅበዘበዘ በጎሰኝነት፣ ቡድናዊነት፣ የኃይማኖት ጽንፈኝነት፣ የጎሳ ትምክህተኝነት፣ የጎሳ ክፍፍል፣ የእራስን ባህልከሌሎች ብሄረሰቦች አስበልጦ በማየት፣ በእብሪት እና የጠባብነት አመለካከት ስሜት ላይ በመዝመት ድንፋታውን ሲያሰማተስተውሏል፡፡

በአጭሩ በእራሱ ጥላሞት ላይ ገጀራ በመያዝ ጥላሞቱን ቆርጦ ለመጣል እንደሚንቀሳቀስ የለየለት እብድ መስሎ ታይቷል፡፡

የኃይለማርያም ህወሀት በጎሰኝነት፣ ቡድናዊነት፣ የኃይማኖት ጽንፈኝነት እና በሌሎች  ለሩብ ምዕተ ዓመት ድረስ በፖለቲካፕሮግራሙ ውስጥ በማስገባት እራሱን በስልጣን እርካብ ላይ ለማቆየት ከፍተኛ ቅስቀሳ እና የፕሮፓጋንዳ ስራ እየሰራሲሆን በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ኃይለማርያም በእነዚህ እኩይ ምግባሮች ማለትም በጎሰኝነት፣ በቡድናዊነት፣ በኃይማኖትጽንፈኝነት ላይ እና በሌሎችም የሀሰት ውንጀላ ክስ እንዲያሰማ እርሱን አስቀምጠውታል፡፡

ስለጎሰኝነት፣ ቡድናዊነት እና የኃይማኖት ጽንፈኝነት ሰይጣናዊነት የኃይለማርያምን ድንፋታ ስሰማየቬኑሱ ነጋዴበሚል ርዕስ በሸክስፒር የተጻፈው እና እንዲህ የሚለው አባባል ትዝ አለኝ፡

ሰይጣን ለእራሱ እኩይ ምግባር ማስፈጸሚያ ሲል ከመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል/ሰይጣናዊ የሆነች ነብስ የቅዱስነትምምስክርነት ትሰጣለች የሚለው አባባል ከሚስቁ የሰይጣን ጉንጮች ጋር እኩል የመሆን ያህል ነው፣ በጣም የሚስበው እናየሚያስጎመጀው የትርንጎ ፍራፍሬ መሀሉ በስብሷል ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ እናም ከለየለት ቅጥፈት በላይ ምንየሚስብ ነገር ሊኖር ይችላል!” (ጅራፍ ራሷ ገርፋ ራሷ ትጮሃለች አነደሚሉት።)

ኃይለማርያም ለብሄራዊ አንድነት፣ ለፍቅር፣ ለጋራ መግባባት እና ዕርቀ ሰላም ለማውረድ እንዲህ በማለት እራሱን እንደቅዱስ ምስክር ሰጭ አድርጎ አቀረበ። ያስቃል ያስገረማል

ስለኪራይ ሰብሳቢነት [በዘይቤ አነጋገር ሙሰኞች] የተለያዩ አመለካከቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው ጠባብነት ነው፡፡ሁለተኛው ደግሞ እብሪተኝነት ነው፡፡ ሶሰተኛው የኃይማኖት ጽንፈኝነት ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች ሀገራችንን የሚበታትኑ እናየሚያጠፉ ስለመሆናቸው አምነን ከስምምነት ላይ መድረስ መቻል አለብን፡፡ እንደዚህ ያሉ የአውዳሚ ዘሮች አስተሳሰብንመዝራት መሰረቱ መምህራን ናቸው፡፡ እነዚህ አስተሳሰቦች በተማሪዎች ቀልብ ላይ ያርፋሉ፣ እናም ግጭቶች እና ጦርነቶችእንዲከሰቱ ያደርጋሉ፣ ሆኖም ግን ዘሩ የተዘራው ከላይ ከቆንጮው ነውአለ ኃይለማርያም

ኃይለማርያም ስለኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት መጠበቅ፣ ስለማንነት እና ስለኃይማኖት መቻቻል የቅዱስነት ምስክርነትንመስጠት መቻል ማለት ለእራሱ እኩይ ምግባሮች ሲል ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በመጥቀስ ከሚሰብከው ፈጣጣ ሰይጣንጋር መሳ ለመሳ ነው፡፡

ቅዱስ _ _ _ ! ድንቄም ቅዱስ!

በዓለም ላይ ከሚደረጉ ነገሮች ሁሉ በኢፍትሀዊነታቸው ምክንያት ብስጭት ይዞት ኃይለማርያም ካደረጋቸው የእዩልኝእመኑልኝ ንግግሮች እውነታዊ ነገሮች ሁሉ ምን የቀረ ነገር አለ?

ኃይለማርያም የእዩልኝ እመኑልኝ ንግግሮች እውነታዊ ነገሮች በማለት በአፋ ላይ በማድረግ የሀሰት የቅሌት ሸፍጡን እየዘራያለው ለምንድነው?

ኃይለማርያም ከወያኔ ኃይለኛ ምት እና የመርከብ የአቅጣጫ መጠቆሚያ መሳሪያው/ራዳር ጠፍቶበት ከአደጋ አድኑኝ፣ነብሴን ከመከራ ታደጓት እያለ ጠቋሚ ምልክቶችን በመጠቀም የክላዊ ጎሰኝነትን ማቆሚያ በሌለው መልኩ (እንደ 21ኛውክፍለ ዘመን የደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ ዓይነት ባንቱስታን) የበረዶ ክምሩን በኃይል ለመምታት እና ለመደረማመስጥረት እያደረገ ነውን?

የኃይለማርያም የአድኑኝ ዋይታ እና ጩኸት ላለፉት ሩብ ምዕተ ዓመታት ያህል የደደቢቱ (ደደብ አላልኩም) የወያኔወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የፍርኃት እና የጥላቻ መርከብ ቀስ በቀስ እየሰመጠ እና እየዘቀጠ ወደ ጥልቁ እና የመጨረሻወደሆነው የውቅያኖስ ክፍል በመሄዱ ምክንያት ነውን?

ኃይለማርያም የወያኔን የትዕዛዝ መስጫ የመለስ ዜናዊን መርከብ መስመጥ እየተመለከተ አድኑኝ የሚል እገዛን ለማግኘትፈጣን የተስፋ መቁረጥ መልዕክት እያስተላለፈ ሊሆን ይችላልን? በርካታ የመርከቡ ነጅ ካፒቴኖች በደቦ ሆነውእየተተራመሱ የመለስ ዜናዊን የጥፋት መርከብ ወደ ጥልቁ እና የመጨረሻ ወደሆነው የውቅያኖሱ ክፍል እየነዱትበማስመጥ ላይ ናቸውን?

ኃይለማርያም በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ውስጣዊ የቡድን ሽኩቻ ላይ የበላይነቱን ለመቀዳጀት እንዲመቸው በማሰብብልህነትን በተላበሰ መልኩ ብሄራዊ አንድነት እና ኢትዮጵያዊነት በማለት ጩኸቱን ከፍ አድርጎ በማሰማት የህዝቡንቀልብ ለመሳብ እንዲመቸው ያደረገው ጥረት ሊሆን ይችላልን?

ኃይለማርያም ሀገራዊ የአርበኝነት ስሜት ያለው በማስመሰል እና በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ውስጣዊ የቡድን ሽኩቻላይ ድልን ለመቀዳጀት ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ድጋፍን ለማግኘት ሲል እያደረገው ያለ ነገር ሊሆን ይችላልን?

ኃለማርያም በወያኔ አለቆቹ አማካይነት አዲስ የተገኘ የጎሳ ስምምነት ኃይማኖት እና ስለኃይማኖት መቻቻል አዲስተንሳፋፊ ፊኛ ወደ ህዝብ አየር ላይ በመልቀቅ የሚሰራ እና የማይሰራ መሆኑን ለማረጋገጥ ህዝቡም ምን ዓይነት ምላሽሊሰጥ እንደሚችል ለማወቅ  የተሰጠው የቤት ስራ እና የተነገረው ምክር ነበርን?

በእርግጠኝነት ኃይለማርያም ከወያኔ የመነጋገሪያ ነጥቦች መጽሐፍ ውስጥ በመውሰድ ነበር ንግግር እያሰማ የነበረው? (ኃይለማርያም የወያኔ የህዝብ ግንኙነት አገልጋይ ሎሌ እንደሆነ ማንም ያውቃል፡፡ እርሱ በደመወዝ ከፋይ የወያኔ አለቆቹእንዲያደርግ ካልተነገረው በስተቀር በእራሱ ስብዕና ድፍረት ኖሮት እንደዚህ ያሉ ንግግሮችን ለማድረግ የሚችልአይሆንም፡፡)

ኃይለማርያም አመልካች ጣቱን ወደየጠባብነት ስሜት አራማጆችበመቀሰር ሲጠቁም ሶስት ጣቶች አሱ ላይአንደሚጦቁሙ ለማየት አልቻለም፡፡

ኃይለማርያም የጠባብ ስሜት፣ የጥላቻ አራማጆች እና ጦር ናፋቂዎች የሚላቸው የትኞቹን የህብረተሰብ ክፍሎች ነው?

ኃይለማርያም ኢትዮጵያን ለማጥፋት ደባ እየሸረቡ እና እየዶለቱ ያላቸውን የጠባብ ጎሰኝነት ስሜት አራማጆች እና በጥላቻየተሞሉ ጦር ናፋቂዎች እያለ ስለተናገራቸው ሰዎች ስም ዝርዝር ምንም የተናገረው ነገር የለም፡፡

ሆኖም ግን የጠባብ ጎሰኝነት አራማጆች መለያ ልዩ ባህሪያት ምንድን ናቸው?

አለመቻቻል ማለት ነውን? የጠባብነት አስተሳሰብ ማለት ነውን? በጥላቻ መሞላት ማለት ነውን? ትዕግስትየለሽነት መሆንማለት ነውን? ድንቁርና ማለት ነውን? መንደርተኝነት ማለት ነውን? አዲስ ሀሳብ የማያመነጩ ማለት ነውን? ጠባብጎጠኝነት ማለት ነውን?

ይህንን ጉዳይ እንዲህ በማለት እውነታውን እንደ እምቧይ ፍርጥ በማድረግ ፊት ለፊት እንጋፈጥ፡ ምድር ተብላበምትጠራው ፕላኔት ላይ ከወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች እና አባላት የበለጠ የጠባብ ጎጠኝነት አራማጅሰው ይኖራልን?

የጠባብ ጎጠኝነት አስተሳሰብ ተቃራኒው ግልጽ አስተሳሰብ ያለው እና ከጠባብነት የአስተሳሰብ ስሜት ነጻ የሆነ ማለትነው፡፡

ግልጽ አስተሳሰብ ያለው እና ከጠባብነት ስሜት ነጻ የሆነ ሰው አዕምሮው ለአዳዲስ ሀሳቦች እና ጥያቄዎች እራሱንም/ሷንምጨምሮ/ጨምራ ባካተተ መልኩ ክፍት ነው፡፡

ከጠባብነት ስሜት ነጻ የሆነ እና ግልጽ አስተሳሰብ ያለው ሰው ሁልጊዜ ሰዎችን ለማዳመጥ ፈቃደኛ ነው፣ እናም ግልጽበሆነ መልኩ በተለያዩ እና ተጻራሪ በሆኑ አስተሳሰቦች ላይ በግልጽ ወይይት እና ክርክር ያደርጋል፡፡

ከጠባብነት ስሜት ነጻ የሆነ እና ግልጽ አስተሳሰብ ያለው ሰው ስህተት ሊሰራ/ልትሰራ እንደሚችል/ምትችል አምነውይቀበላሉ፣ እናም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እራሳቸውን ለማረም ፈቃደኞች ናቸው፡፡

ከጠባብነት ነጻ የሆነ እና ግልጽ አስተሳሰብ በማራመድ ላይ ያለ ሰው ማንም የፈለገውን ቢያስብ እውነቱን ይናገራል፡፡

እንዲያው ለመሆኑ ከጠባብነት አስተሳሰብ ነጻ የሆነ እና ግልጽ አስተሳሰብን የሚያራምድ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድንስብስብ አመራር ወይም ደግሞ አባል በባትሪ ተፈልጎ ይገኛልን?

ዳዮግነስ ሲኖፔ (የግሪክ ፈላስፋ እና የሳይኒክ [የፍልስፍናው መርህ ተከታዮች የሕይወት ዓላማ በክብር ለመኖር ነውየሚል ሀሳብን የሚያራምዱ]) ፍልስፍናን ከመሰረቱት ሰዎች መካከል አንዱ የነበሩት በቀን ብርሀን በከተማ ውስጥ የበራፋኖስ በእጃቸው በመያዝ ጉዞ ማድረግ ጀመሩ፡፡ እንደዚህ ያለ አዲስ የሆነ ነገር ለምን እያደረጉ እንዳሉ ሲጠየቁ እንዲህየሚል መልስ ሰጡ፣እኔ በእርግጥ በዚህ የፋኖስ ብርሀን እውነተኛ ሰው ለማግኘት እየፈለግሁ ነው፡፡ዳዮግነስበእርሳቸው የፍለጋ ጥረት መሰረት አንድም እውነተኛ ሰው ያላገኙ ሲሆን ይልቁንም በተቃራኒው ታማኝነት የሌለውአታላይ እና ክበርየለሽ መርህ አልባ የሆኑ ሰዎችን ነው ማግኘት የቻሉት፡፡

ማንም ቢሆን በኢትዮጵያ በአውራ መንገዶች እና በጠባብ የህዝብ እና የትራፊክ መንቀሳቀሻ መንገዶች ላይ ቢጓዝ፣ ወደከፍተኛው ተራራ ቢወጣ እና ሸለቆዎችን ሁሉ በሞተር በመንቀሳቀስ ቢያቋርጥ እና ፓውዛ መብራት ይዞ ቢፈልግ ከወያኔወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራር ወይም አባላት ውስጥ አንድም ነጻ አስተሳሰብ ያለው እና ግልጽ ሀሳብንየሚያራምድ ሰው በፍጹም አይገኝም፡፡ ይልቁንም በጠባብ የአስተሳሰብ ስሜት እና በጎጠኝነት በሽታ ተለክፈው የሚገኙእምነተ ቢስ አታላዮች እና ቅሌታሞች  ክብርየለሽ መርህ አልባ ስብስቦች ብቻ ናቸው የሚገኙት፡፡

በተገላቢጦሽ አሳዛኙ ነገር ኃይለማርያም አመልካች ጣቱን ስም በሌላቸው የጠባብ ስሜት አራማጆች ላይ እንደቀሰረውሁሉ ሌሎቹ ሶስቱ ጣቶቹ ደግሞ ወደ እራሱ የሚያመለክቱ መሆናቸውን መገንዘብ ይኖርበታል፡፡

ኃይለማርያምግጭት የሚፈጥሩትን እና ጦርነት ናፋቂእብሪተኞችን ከሷል፡፡

ለመሆኑ በኢትዮጵያ የጥላቻን እና የጦርነት ናፋቂነት እኩይ ምግባራት እንዲከሰቱ ደባ የሚሸርብ እና ጎሰኝነትንለማስፋፋት፣ የኃይማኖት ጽንፈኝነትን፣ ቡድናዊነትን፣ ወዘተ እያስፋፋ ያለ እብሪተኛ ማን ነው?

ከዚህ አንጻር ኃይለማርያም አንድም በስም የጠቀሰው ሰው የለም፡፡

ሆኖም ግን ክብርም አለ እናም እብሪትም እንደዚሁ አለ፡፡

ኃይለማርያም እና የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አለቆቹ በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት ይገነዘቡታል ብየአላስብም፡፡

አንድ ሰው ስለእራሱ/ መልካም ነገር ሲያስብ ወይም ስታስብ፣ ወይም ደግ ነገርን ለመስራት ሲያስብ/ስታስብ በእራስመተማመን ይፈጠራል፣ እናም ከአታላይነት፣ ከአስመሳይነት፣ በሁለት ቢላዋ ከመቁረጥ፣ ወዘተ ነጻ በመሆን ክብር ያለውየኑሮ ዘይቤ መኖር በመሞከር ትክክለኛ ክብር ያለው ኑሮ ይኖራል/ትኖራለች፡፡

እብሪተኝነት የአስመሳይነት ክብር ነው፡፡ እብሪት በእራስ ወዳድነት ማዕከልነት የሚነዳ እና እራሱን በጠብ ኣጫሪኃይለኝነት፣ በጥርጣሬ እና በእምነተቢስነት የሚገልጽ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ክብርን የመውደድ የእብሪተኝነት መገለጫነው፡፡ እብሪተኛ ሰው ሁልጊዜ የበታችነት ስሜት ስቃይ ውስጥ ገብቶ የመዳከር ስሜት ይሰማዋል፣ እንደዚሁም ደግሞየብቃት የለሽነት እና ለእራሱ እርባና የሌለው ከንቱ ፍጡር የመሆን ስሜት ይሰማዋል፡፡

እንደገና ደግሞ ከጥሬ ሀቆች ጋር አንድ ጊዜ እስቲ እንዲህ በማለት እንጋፈጥ፡ ማንም ሰው ቢሆን በዚህች ምድር ፕላኔት ላይከወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራር ወይም አባላት የበለጠ ነጻ አስተሳሰብ የሌለው እና ግልጽ ሀሳብንየማያራምድ እብሪተኛ ሰው ሊኖር ይችላልን?

ለበታችነት ስሜት አስተሳሰባቸው፣ ለብቃት የለሽነታቸው እና የእራስን እርባናቢስነት ማካካሻ ለማድረግ በማሰብ የወያኔወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች እና የእነርሱ አገልጋይ ሎሌዎቻቸው የአካዳሚክ ክብርን ለመጎናጸፍ የመስቀልጦርነትን በማራመድ ላይ ይገኛሉ፡፡

በርካታዎቹ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቁንጮ አመራሮች ከዲፕሎማ መቀፍቀፊያ ወፍጮ ተቋማት ዲግሪበመግዛት ላይ እንደሚገኙ ሀገር ያወቀው ጸሐይ የሞቀው የማይካድ እውነታ ነው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የተጭበረበሩ ዲግሪዎችን በመግዛት ምንም ዓይነት የአካዳሚክ ብቃት ሳይኖራቸውየእምነታቸው አራማጅ የሆኑትን ታዛዥ ሎሌዎች እና መንፈሰ ደካማ ሰዎችን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ፕሮፌሰሮች እያሉይሾሟቸዋል፡፡ ሀገር ሲያረጅ ጃርት ያፈራል እንዲሉ!

አሁን በህይወት የሌለው እና ትንሹ አምላክ የነበረው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቀንደኛ አድራጊ ፈጣሪ መሪመለስ ዜናዊ ከኦፕን ዩኒቨርሲቲ በመመረቅ ዲግሪው ከቤተመንግስቱ ድረስ እንዲመጣለት ዝግጅት አድርጎ ነበር፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች እና ልሂቃን ተብዬዎች በርካታ የዲፕሎማ መቀፍቀፊያ የንግድወፍጮዎች አነሱ ባይኖሩ በከሰሩ ነበር። 

ለዚህ አባባል ማስገንዘቢያ አንዱ ቀላሉ ነጥብ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች እና ልሂቃን እነርሱከሚጨቁኗቸው ከሁሉም ህዝቦች የተሻሉ፣ ማራኪዎች እና የበለጡ ጠቃሚዎች፣ አዋቂዎች እንደሆኑ አድርገው በመቁጠርዓለም እንዲያረጋግጥላቸው ይፈልጋሉ፡፡ ሆኖም ግን እያንዳንዱ ሰው እንደሚያውቀው እነርሱ ምንም ነገር የሌላቸውእርባናየለሽ ፍጡሮች ናቸው::

የእነዚህ ደናቁርት እብሪት ስለ በፊቱ ያፍሪካ አምባገነኖች ያስታዉሰኛል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እና አሁን በህይወት የሌለው መሪያቸው ይፋ መጠሪያውየተከበሩ፣ የእድሜ ልክፕሬዚዳንት፣ ፊልድ ማርሻል አልሀጅ፣ / ኢዲ አሚን ዳዳ፣ የኮሙኒስት የሽምቅ ተዋጊ፣ የማሪን/ባህር ወታደር፣ የሁለምበመሬት ላይ የሚገኙ ኃይለኞች እና በውኃ ላይ ለሚገኙ ፍጡራን ሁሉ የበላይ ሀያል አለቃ እና በአፍሪካ የእንግሊዞችንግዛት በአጠቃላይ እና በዩጋንዳ በተለይ ድል ያደረገውን እና ስም የተባለውን ሁሉ ጠቅልሎ የያዘውንያንን የለየለትእብሪተኛ ኢዲ አሚንን አስታወሰኝ፡፡

መለስ ዜናዊም በተመሳሳይ መልኩታላቁ መሪ፣ ታላቁ ባለራዕዩ፣ የደደቢት ታላቅ ጀግና፣ በመሬት እና በባህር ላይለሚገኙ ፍጡራን ለሁሉም ኃይለኞች ሁሉ የበላይ አለቃ እና በደርግ እና በኢትዮጵያ ግዛት እንዲሁም በሁሉም የጎሳቡድኖች ላይ ድል አድራጊነትን የተጎናጸፈ፣ ወዘተ፣ ወዘተ፣ ወዘተ…“ የሚሉ ተቀጥያ ስሞችን ጠቅልሎ ይዞ ነበር፡፡

ኃይለማርያም ስማቸው ተለይቶ ባልታወቁ መምህራን እና ፕሮፌሰሮች ላይ አመልካች ጣቱን ቀስሯል፡፡ 

ለመሆኑ ኃይለማርያም ስለጎሳ ክፍፍል፣ ስለኃይማኖት ጽንፈኝነት እና የጥላቻ እና የጦርነት ነጋሪት የሚጎስሙት ብሎየወነጀሏቸው እነዚያ በስም ያልጠቀሳቸው መምህራን እና ፕሮፌሰሮች እነማን ናቸው?

ኃይለማርያም የውንጀላ ክስ የመሰረተባቸው የኢትዮጵያ መምህራን እና ፕሮፌሰሮች በጣም ውሱን የሆኑ እና የሚያስፈሩናቸው፡፡ ኃይለማርያም በኢትዮጵያ በጣም የተማረው የህብረተሰብ ክፍል አባላት ለሀገሪቱ የፖለቲካ እና የማህበራዊችግሮች ዋና ምንጮች ናቸው ይላል፡፡ እነዚህን የህብረተሰብ ከፍሎች ስብዕና ጥላሸት ይቀባል፣ የጥላቻ አራጋቢዎች ብሎይፈርጃቸዋል፣ በተለይም ደግሞ ወጣቶቹን፡፡

ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ጥላቻን፣ ጎሰኝነትን፣ የኃይማኖት ጽንፈኝነትን፣ ቡድናዊነትን፣ ወዘተ ያስፋፉበጣም ደንቆሮዎች እና እምነተ ቢሶቹ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች መሆናቸው እውነታነት የለውምን?

በጣም እየደነቀኝ ያለሁበት ሁኔታ ነው፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሌላ ጅምላ፣ ህዝባዊ ማባረርን በዩኒቨርሲቲመምህራን እና ፕሮፌሰሮች ላይ ለመተግበር ሌላ ዙር ዝግጅት እያደረገ ነውን?

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊገመት የሚችል ሁኔታ አለው፡፡

ወያኔ በግፍ ሰለባዎቹ ላይ እርምጃ ከመውሰዱ በፊት በቅድሚያ ስም የማጠልሸት ስራ መስራት ይጀምራል፡፡ 

ከዚያም በኋላ የማዋረድ አስነዋሪ ድርጊቱን ይቀጥላል፣ እናም ህዝብ ግብር እየከፈለ በሚያስተዳድራቸው የመገናኛ ብዙሀንየተለመደ ስም የማጥፋት ዕኩይ ምግባሩን ይቀጥላል፡፡

በመቀጠልም እነዚህ የእርሱ የግፍ ሰለባዎች እራሳቸው ኃላፊነቱን እንዲወስዱ ያደርጋል፡፡ ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱይጮሀል እንዲሉ፡

ከዚያም በመቀጠል ገራፊ ወሮበሎቹን በማሰማራት በግፍ ሰለባዎቹ ላይ የማስፈራራት እና የማሰሸማቀቅ እኩይ ምግባራትንይሰራል፡፡

በመቀጠልም እባብ በመስክ ላይ እንዳለች አይጥ መርዙን በመርጨት ለምግቡ እንደሚያደርሳት ሁሉ ይህ እኩይ የማፊያስብስብ ድርጅት በሰላማዊ ምሁራን ላይ መርዙን በመርጨት  በድንገት በቁጥጥር ስር ያውል እና በሸፍጥ የታጀበ የጸረሽብር ክስ እንዲመሰረትባቸው ያደርጋል፡፡

ከዚያም በማጎሪያው እስር ቤት ገብተው በይስሙላው የዝንጀሮ/ጦጣ ፍርድ ቤት የተንዛዛ ቀጠሮ እየተመላለሱ ለዓመታትእንዲማቅቁ ያደርጋል፡፡

በግድግዳው ላይ የተጻፈውን  ነገር መምህራን ተጠንቀቁ፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን መስመር የማትከተሉ የኢትዮጵያ መምህራን እና ፕሮፌሰሮች ለመባረር መዘጋጀትይኖርባችኋል፣ ምክንያቱም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እናንተን ከምታስተምሩበት ቅጥር ግቢ ውስጥ መንጥሮለማባረር እና የእራሱን ቤት ለማጽዳት ተዘጋጅቶ መጥቷልና!

ለሌላ ዙር እስራት እና የጸ ሽብር የዱለታ የዝንጀሮ ክስ ዝግጁ ሁኑ!

.. 1993 የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እንደዚህ ያለ ተመሳሳይ ድርጊትን ፈጽሟል፡፡ ከፋፋይ እና የጠባብጎሰኝነት አፈራማጅ እና ከፋፋይ የእብሪተኝነት ዕኩይ ዓላማውን የማይደግፉትን አንቱ የተባሉ ምርጥ እና ምጡቅየዩኒቨርሲቲ መምህራንን እና ፕሮፌሰሮችን በድንቁርና እና በማንአለብኝነት ሀገሪቱ በስንት ዓመታት አስተምራያወጣቻቸውን አንቱ የተባሉ መምህራን በጅምላ በማባረር የሰው ሀገር ሲሳይ እንዲሆኑ አድርገዋል፡፡ ሄደውምስለሀገራቸው ጉዳይ ጸጥ ብለው ሳይቀመጡ ከስራዎቻቸው በተጓዳኝ በሀገራቸው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲመሰረት እናይህ ለህዝብ እና ለሀገሪቱ ዕኩይ የሆነ ስርዓት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ አፈር ድሜ በልቶ ወደ የታሪክ ቆሻሻማጠራቀሚያ ቅርጫት ውስጥ እንዲጣል ለለውጥ ተግተው በመታገል ላይ ይገኛሉ፡፡

አንዳንዶቹም በዓላማቸው ጸንተው በሀገር ውስጥ የግል ስራቸውን እየሰሩ ለሀገራቸው ነጻነት እና ለህዝባቸው ልዕልና ሌትከቀን በመታገል ላይ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ በእብሪተኝነት በደንቆሮዎች ውሳኔ ከሚያስተምሩባቸው ግቢዎች እንዲባረሩየተደረጉት የምርጦች ሁሉ ምርጥ መምህራን እና ፕሮፌሰሮች የሚከተሉትን ያካትታል፡

1) ፕሮፌሰር መኮንን ቢሻው

2) ፕሮፌሰር ሰለሞን ተርፋ

3) ፕሮፌሰር ስብሀት መርሴ ሀዘን

4) ፕሮፌሰር ታዬ ወልደሰማያት

5) ፕሮፌሰር ፍስኃ ዘውዴ

6) ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ

7) ፕሮፌሰር አየነው እጅጉ

8) ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ኃይሌ

9) ፕሮፌሰር መኮንን ዲልጋሳ

10) ፕሮፌሰር ታምሬ ሁዋንዳ

11) ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ

12 ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ተፈራ

13) ፕሮፌሰር አድማሱ ዋሴ

14) ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ

15) ፕሮፌሰር ዳዊት ዘውዴ

16) ፕሮፌሰር አስፋው ደስታ

17) ፕሮፌሰር ታዬ መኩሪያ

18) ፕሮፌሰር አየለ ተርፈ

19) ፕሮፌሰር በፈቃዱ ደግፌ

20) ፕሮፌሰር ኃይሉ አርአያ

21) ፕሮፌሰር ታዬ አሰፋ

22) ፕሮፌሰር ወርቁ ተፈራ

23) ፕሮፌሰር ንጋቱ ተስፋዬ

24 ሌክቸረር ሰለሞን ወንድወሰን

25) ሌክቸረር ኃይሉአንተን አባተ

26) ሌከቸረር ሽፈራው አጎናፍር

27) ልክቸረር መኩሪያ አሰፋ

28) ሌክቸረር ፈለቀ ደስታ

29) ሌክቸረር አክሊሉ ታደሰ

30) ሌክቸረር ብርሀኑ ባንካሸ

31) ሌክቸረር ለዓለም ብርሀኑ

32) ሌክቸረር አይናለም አሸብር

33) ሌክቸረር ፕሮፌሰር ጸሐዬ ብርሀኔ

34) ሌክቸረር ምንዳርያለው ዘውዴ

35) ሌክቸረር አየለ ታረቀኝ

36) ሌክቸረር ዘሪሁን ተሾመ

37) ሌክቸረር ፈቃደ ሸዋቀና

38) ታደሰ በዬነ

39) ተስፋዬ ሸዋዬ

40) ሰይፉ መታፈሪያ

41) ረዳት ሌክቸረር መስከረም አበበ ናቸው፡፡

.. 2015 ከሚያስተምሩበት ግቢ እንዲባረሩ ስም ዝርዝራቸው በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ውስጥየሰፈረው ፕሮፌሰሮች፣ መምህራን እና ሌሎች የትምህርት ባለሙያዎች እነማን ናቸው?

ይህንን እኩይ ድርጊት በጭንቀት እንጠብቃለን!

ኃይለማርያም ስለኃይማኖት ጽንፈኝነት፣ ስለጥላቻ ማራገብ እና ስለጦርነት ነጋሪት መጎሰም ብዙ ያወራል፡፡

ለመሆኑ ኃይለማርያም ስለኃይማኖት ጽንፈኝነት እየተናገረ ያለው ስለእነማን ነው?

ከጥቂት ሳምንታት በፊት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የይስሙላ የዝንጀሮ (የጦጣ) ፍርድ ቤት 18 ወጣትኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች (ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ዩኤስሲአርአይኤፍ/USCRIF የአፍሪካየሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና ሌሎች በርካታ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ሰላማዊየተቃዋሚ መሪዎች እና ወትዋቾች እያሉ የሚጠሯቸውን) ላይ የኃይማኖት ጽንፈኝነትን እና የቡድናዊነት ስሜትንበማራመድ በሚል የአሸባሪነት ክስ 7 እሰከ 22 ዓመታት የእስር ውሳኔ በየነ፡፡

ወጣት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የጸረ ሽብር ድርጊት ሙከራ፣ እስላማዊ መንግስት ለማቋቋም እና የአመጽ ቅስቀሳበማካሄድ በሚል የተቀነባበረ ሽረባ እና ደባ ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የዩስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤት በአቡባከር አህመድ፣ በአህመዲን ጀቤል፣ በያሲን ኑሩእና በከማል ሸምሱ በእያንዳንዳቸው ላይ እጃቸው ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ በሚታሰብ 22 ዓመት እስር በይኗል፡፡

በይስሙላው የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ሌሎች ተከላካዮች ላይ ማለትም በሙኒር ሁሴን፣ በሳቢር ይርጉ፣ በበድሩ ሁሴን፣በመሀመድ አባተ እና በአቡበከር አለሙ በእያንዳንዳቸው ላይ እጃቸው ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ በሚታሰብ 18 ዓመትእስራት በይኗል፡፡

እንደዚሁም ደግሞ በአህመድ ሙስጠፋ፣ በከሀሊድ ኢብራሂም፣ በሸክ መከተ ሙሄ፣ በሸክ ሰይድ ዓሊ እና በሙባረክ አደምበእያንዳንዳቸው ላይ እጃቸው ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ በሚታሰብ 15 ዓመት እስራት ወስኗል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤት በዩሱፍ ጌታቸው፣ በኑሩ ተርኪ፣ በሙራድ ሽኩር እናበባህሩ ኡመር በእያንዳንዳቸው ላይ እጃቸው ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ በሚታሰብ 7 ዓመት እስራት በይኗል፡፡

እሰከ አሁንም ድረስ ከትልቁ ቋጥኝ ጀርባ ተደብቀው ውድመትን ለመፍጠር የተዘጋጁ ሌሎች የኃይማኖት ጽነፈኞች አሉማለት ነውን?

ኃይለማርያም የኃይማኖት ጽንፈኝነትን በሚያወግዝበት ጊዜ በቅርቡ በቁጥጥር ስር የሚውሉ ሌሎች ያሉ እና በሌላ ዙርየሙስሊም አሸባሪዎችን እንይዛለን የሚል ዘገምተኛ ማስታወቂያ እያሰማ ነውን?

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የማታለያ ዘዴ፡የጎሳ ፌዴራሊዝም (ክልላዊነት)”

25 የአገዛዝ ዓመታት በኋላ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዋና ችግር የጎሳ ጥላቻ እና በኃይማኖት አለመቻቻልንእንደ አብይ የአገዛዙ ስልት በመቁጠር ሲያራምዱት የቆየው ዕኩይ ምግባር በአሁኑ ወቅት በጣም እያደገ በመምጣትእራሳቸውን ከጀርባ በመሆን ሊነክሳቸው እያኮበኮበ የመገኘቱ ሁኔታ ነው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብየጎሳ ፌዴራሊዝም (ክልላዊነት)” ምንድን ነው?

የጎሳ ፌዴራሊዝምኢትዮጵያ ወይም ደግሞ የኢትዮጵያ ታሪክ የሚባል ነገር የለም የሚል የተጠቃለለ የወያኔ ወሮበላየዘራፊ ቡድን ስብስብ ዋና ፍልስፍና ነው፡፡

ኢትዮጵያ የሚለው ቃል በንድፈ ሀሳብ ደረጃ በአንድ በተወሰነ የጎሳ ቡድን አባላት አዕምሮ ውስጥ የሚገኝ ምዕናባዊአስተሳሰብ ነው፡፡

ኢትዮጵያከአንድ ክፍለ ዘመን በፊት እውቅና አግኝታ ወደዚህ ዓለም የመጣች ሀገር ናት፡፡

ኢትዮጵያየተነጣጠሉየብሄሮች እና ብሄረሰቦችስብስብ ናት፡፡

ኢትዮጵያእርስ በእርሳቸው በማይደጋገፉ ህዝቦች እና ተጻራሪ የሆኑ ፍላጎቶች ያሏቸው በመሳሪያ ኃይል በግድ አንድእንዲሆኑ ተጨፍልቀው ተይዘው ያሉ ህዝቦች ናቸው፡፡

ኢትዮጵያውያንበተከፋፈለ ጎሳ፣ ቋንቋ እና ኃይማኖት ካምፖች እንዲሁም በተጻራሪ ፍላጎቶች በተሻለ ሁኔታ መገዛትይችላሉ፡፡

እንደ እነርሱ አባባል ኢትዮጵያዊ ነን ብለው የሚያስቡ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ድብቅ ዓለማቸው በሌሎች የጎሳ ቡድኖች ላይየበላይነትን የሚያራመዱ ብሄረተኞች ናቸው፡፡

በመሰረቱ ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ትርጉም ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ውድቀት እና በመጨረሻም እንዳይነሳሆኖ መደምሰስ ማለት ነው፡፡

ኢትዮጵያበሀሳብ፣ በታሪክ እና በሁለመናዋ መንገድ በእርግጥ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ግዛት ህልውናማግኘት እና መጠናከር የትኛውንም ያህል ዋጋ ተከፍሎም ቢሆን መደምሰስ እና መቀበር አለባት

ስለሆነም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በአሁኑ ጊዜ ምን ቀረው?

ደህና እንግዲህ በአሁኑ ጊዜ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የዘሩትን ማጨድያ ጊዜ ነው?  (ምናልባት?!)

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለሩብ ምዕተ ዓመታት ያህል የዘራውን የጎሳ ፌዴራሊዝም ዘር ሰብል ለማጨድበዝግጅት ላይ ነው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የጥላቻ አዝመራ አጨዳ፣

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ስልጣኑን አንቆ በመያዝ ለመቆየት እና ቁጥጥሩን ለማጠናከር እንዲችል የጎሳፌዴራሊዝምን ስርዓት ቀይሷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የጎሳ ፌዴራሊዝሙ በከፍተኛ ደረጃ አድጓል፣ ተጠናክሯል እናምበመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ቀስ በቀስ የእራሱን የወያኔን ጉሮሮ ያንቃል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በግድግዳ ላይ የተጻፈውን እየተመለከተ ነው፣ መምህራንን እና ፕሮፌሰሮችንእንዲሁም ወጣቱን ትውልድ እያዳመጠ ነው፡፡ ወያኔው ማንኛውንም የሚመለከተውንም ሆነ የሚሰማውን ነገር ሁሉአይወድም፡፡

ፒትሪም ሶሮኪን የተባሉ ሰው በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ጥላቻ ጥላቻን ይወልዳል፣ ኃይል ሌላ የኃይል አደጋንያስከትላል፣ አስመሳይነት በአስመሳይነት ምላሽ ያገኛል፣ ጦርነት ጦርነትን ይወልዳል፣ እንደዚሁም ደግሞ ፍቅር ፍቅርንይፈጥራል፡፡“ 

ቅዱሳት መጽሐፍት እንዲህ በማለት ያስተምሩናል፣ሰው የዘራውን ያጭዳል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች ፈታኙን ወቅት የሚጋፈጡበት ጊዜ ነውን?

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እንደውዳሴ ማርያም ሲደግመው እና ሲዘምርለት የከረመውን ስለብሄሮች ክፍፍል፣ስለጎሰኝነት፣ ስለቡድናዊነት፣ ስለኃይማኖት ጽንፈኝነት እና ስለሌሎች ስለቀሩትም ሁሉ እየመጣ ላለው ችግር ኃላፊነቱንጠቅልሎ ለመምህራን እና ለፕሮፌሰሮች ለመስጠት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ እንደ ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱየሚጮህ ግራ ገብቶት ግራ የሚያጋባ ስርዓት!

እውነት እንናገር!          

መምህራን እና ፕሮፌሰሮች ወጣቶችን በመንከስ የጥላቻን መርዝ ያሰራጫሉ ብለን ካሰብን እነዚህን መምህራን እናፕሮፌሰሮች እንዲሆኑ የሾማቸው ማን ነው?

የውርስ ታሪክእየተባለ የሚጠራውን አዲስ ፋሽን በማድረግ በዩኒቨርሲቲው ስርዓተ ትምህርት/curriculumውስጥ እንዲካተት ያደረገው ማን ነው?

የውርስ ታሪክ መሰረት ያደረገው በአሁኑ ጊዜ ያለው የኢትዮጵያ ታሪክ ለትርጉም የሚጋብዝ፣ የግል አመለካከትየተንጸባረቀበት እና አጠቃላይ ይዘቱ ሲታይ ሚዛናዊነትን ያልጠበቀ አንድ ዓይነት የሆነ በጽሁፍ ከተገኙት ሰነዶች ብቻተወስዶ እንደገና የተጻፈ ሆኖ ይገኛል፡፡ ብሄራዊ ታሪካችንን እንደገና የማደራጀቱ የመጻፉ ስራ ሌላ ተለዋጭ የመረጃምንጭ የማግኘቱ እና የመጠቀሙ ጉዳይ ጊዜ የሚሰጠው ነገር አይደለም

የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ስለእራሳቸው ጎሳ ቡድን እንጅ ስለሌላ ስለማንም እንዳይዘግብ ሆኖበስርዓት ትምህርቱ ውስጥ እንዲካተት ያደረገ ማን ነው?

የማለያየት ፖሊሲን በትምህርት ቤቶች ላይ በመቅረጽ እና ተማሪዎች እያደጉ ሲሄዱ ጓደኞቻቸው ወደፊት ጠላቶቻቸውእንደሚሆኑ የሚያስቡ እንዲሆን ከተደረገ ይህንን ከፋፋይ ፖሊሲ እንዲቀረጽ እና እንዲተገበር ያደረገው ማን ነው?

የተለያዩ ብሄሮች እና ጎሳዎች የጋራ መግባቢያ የሆነውን ሀገራዊ ቋንቋቸውን ትተው ወንዝ የማያሻግር እና የጠባብነትስሜትን ወደሚያዳብረው በብሄር ቋንቋ ብቻ እንዲማሩ ፖሊሲ የነደፈው እና እንዲተገበር ያደረገው ማን ነው?

የሚከተሉትን ክልሎች (የብሄር ቋንቋን መሰረት ያደረጉ ክልላዊ መንግስታት) ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ፣ አፋር፣ ሶማሊ፣ቤንሻንጉልጉሙዝ፣ ደቡብ ሕዝቦች፣ ጋምቤላ፣ እና ሀራሪ፣ (አዲስ አበባ/ድሬዳዋ በፌዴራል ደረጃ የሚተዳደሩ ከተሞች)የፈጠረ ማን ነው?

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሕገ መንግስቱን እንዲህ የሚለውን የመገንጠል እና የመገነጣጠል አንቀጹን አንቀጽ39ን፡እያንዳንዱ ብሄር ብሄረሰብ ወይም ህዝብ የእራሱን እድል በእራሱ የመወሰን እስከመገንጠልየጻፈው ማን ነው?የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አንቀጽ 39 በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሰውነት ላይ ለመጨረሻ ውድመት የቀበረውበሰዓት የተሞላ ቦምብ ወያኔ ግብዓተ መሬቱ ሲደርስ እና ወደ ታሪክ ቆሻሻ ማጠራሚያ ቅርጫት ውስጥ ሲጣል እንዲፈነዳታስቦ የተቀበረ ነውን?

በሀገሪቱ ውስጥ ሁሉንም የፖለቲካ ውክልናዎችን፣ የውሳኔ ሰጭነትን፣ በክልሎች የህዝብ መድረኮችን የተቆጣጠረው፣በበላይነት የሚይዘው እና በጥቅል ሁሉንም ነገር ጨምድዶ ይዞት የሚገኘው ማን ነው?

በህዝቡ መካከል ውጥረት እና የጥላቻ መንፈስ እንዲሰራጭ የሚያደርግ እና በጎሳ ቡድኖች እና በማህበረሰቦች መካከልየትጥቅ ግጭት እንዲፈጠር፣ የኃይማኖት ጽንፈኝነት እና በኢትዮጵያ ጦረኝነት እንዲነግስ ለሚደረገው እኩይ ምግባራትሁሉ በዋናነት ተጠያቂው ማን ነው?

ስውር በሆነ መልኩ በጎሳዎች መካከል ግጭት እንዲፈጠር በማድረግ አጋጣሚውን በመጠቀም ሁኔታውን ለማባባስ በጎሳግጭት እሳቱ ላይ ነዳጅ የሚያርከፈክፈው ማን ነው?

የጎሳ ፌዴራሊዝም (ወይም ደግሞ ጦጣ አየች፣ ጦጣ ሰራች ዓይነት ፌዴራሊዝም) ካስገኘው ተሞክሮ ምን የተገኘ ጥቅምእና የተመዘገበ ነገር አለ?

በጎሳ ፌዴራሊዝም ሁሉንም ጠቃሚ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ውሳኔዎችን የሚወስነው ማን ነው?  

በእርግጠኝነት የጎሳ ፌዴራሊዝም እንዴት ነው እየሰራ ያለው?        

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ለክልል ሎሌ መንግስታት ዴሞክራሲያዊማዕከልነትን በጠበቀ መልኩ ለትግበራ ይወስኑላቸዋልን?

የክልል መንግስታት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት እና የክልል ምክር ቤቶች የፌዴራሉን ውሳኔ በመያዝ ማህተምለማሳረፍ ብቻ የተቀመጡ ታዛዥ ሎሌዎች ናቸውን?

የክልል መንግስታትን ጉዳዮች የሚቆጣጠረው ማን ነው? የክልል እና የአካባቢ መንግስታትን የገቢ እና በጀት አጠቃላይጉዳዮችን የሚቆጣጠረው ማን ነው?

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እራሱ ሕግ ካወጣ በኋላ ያወጣውን ሕግ በመደፍጠጥ ለምንድን ነው በክልሎችጉዳይ ላይ ወታደራዊ ጣልቃገብነትን የሚያራምደው እና ሕጉን ጠብቀው የሚንቀሳቀሱ የክልል አመራሮችን ከስልጣንየሚያግደው?

የክልል መንግስታት በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አለቆቻቸው ከላይ ተወስኖ ከተሰጣቸው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚእና የማህበራዊ አጀንዳ ውጭ ሊያስቡ እና ሊሰሩ የሚችሉባቸው አሉን?

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እምነተቢስ ሁኔታ ክልሎች ቁራጭ ዳቦ ለማግኘት ሲባል በወያኔ ጠረጴዛዎች ላይጦርነት መግጠም አለባቸውን?

ክልላዊነት ለተጮቆኑት የጎሳ እና አናሳ ቡድኖች ወይም ደግሞ ለመገንጠል እንዲያመች በስውር ነዳጅ የሚጨምሩ ቡድኖችቀደም ሲል ያቀርቧቸው የነበሩት ታሪካዊ ቅሬታዎች መፍትሄዎቻቸውን አግኝተዋልን?

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኢትዮጵያ ሕዝቦች መካከል የጎሳ ማንነትን በመፍጠር፣ በጅምላ ተጠራጣሪነትን፣ፍርሀትን እና ጥላቻን በመዝራት በህዝቦች መካከል ለዘለቄታው የጎሳ ክፍፍልን ለማቆየት እንዲመቸው የጎሳ ፌዴራሊዝምንአዋቅሯል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኢትዮጵያን ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅበር እና በቀብር ቦታዋ ላይ የእራሱን ሐውልትለመገንባት የሚሉትን እንደመሳሪያ ለመጠቀም እንዲችል የጎሳ ፌዴራሊዝምን አዋቅሯል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አድራጊ ፈጣሪ ዋና መሀንዲስ ለኢትዮጵያ በቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ እራሱ ገብቶበትተገኝቷል፡፡

እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ግን የጎሳ ፌዴራሊዝም የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ዋና መሳሪያ እና ሌሎች ሁሉም የጎሳቡድኖች ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ታማኝ ሎሌዎች ሆነው እንዲያገለግሉ የሚያስችል ስርዓትን መፍጠርነው፡፡

ከሩብ ምዕተ ዓመት አገዛዝ በኋላ የጎሳ ፌዴራሊዝም ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኢትዮጵያን ለመግዛት አስቸጋሪእየሆነበት መጥቷል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የጎሳ ግንኙነቶች ከምንጊዜውም በላይ አስከፊ እየሆኑበትመጥተዋል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እራሱን እና ሌሎችን የጎሳ ቡድኖች ለማገዝ በማሰብ የጎሳፌዴራሊዝምን አዋቅሯል፡፡

ወሳኙ እና በመጨረሻ ሊነሳ የሚገባው ጥያቄ ሁሉም የኢትዮጵያ ጎሳዎች እና ኃይማኖቶች ቀደም ከነበሩበት የተሻለ ነጻነት፣ከፍ ያለ የኃላፊነት ስልጣን እና በእራስ የመተማመን ስሜት በሌላ ጊዜ ከነበሩበት ይልቅ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድንስብስብ አገዛዝ ስር አግኝተዋልን?

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዳንስ አብቅቷል!

እንዲህ የሚባል አባባል አለ፣ሁሉንም ሰዎች ለጥቂት ጊዜ ማሞኘት ይቻላል፡፡ ጥቂት ሰዎችን ግን ሁልጊዜ ማሞኘትይቻላል፡፡ ሆኖም ግን ሁሉንም ሰዎች ሁልጊዜ ለማሞኘት አይቻልም፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከፊሉን ህዝብ ሁልጊዜ አሞኝቷል፣ ጥቂቶችን ግን ሙሉ ለሙሉ 25 ዓመታትያህል ሲያታልል ቆይቷል፡፡ ሆኖም ግን አሁን ሁሉንም ለሁልጊዜ ማታለል ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ አብዛኛውህዝብ ነቅቷል

ስለሆነም በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሳይሆን እራሱን በማሞኘት ላይ ብቻታጥሮ ይገኛል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እራሱን በኢትዮጵያ በስልጣን ኮርቻ ላይ አደላድሎ ለመቀመጥ ላለፉት ሩብ ምዕተዓመታት በህዝቦች መካከል ለዘራው እና እየተጠናከረ ለመጣው የዘር ጥላቻ እራሱን ነጻ በማድረግ እኩይ ድርጊቱን ወደመምህራን እና ፕሮፌሰሮች ለማላከክ ድሁር ድሁር ይላል፡፡ የእምዬን ወደ አብዬ እንዲሉ!

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በአሁኑ ጊዜ ምን እንደሚሰራ የሚያውቀው ነገር የለም፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከለኮሰው የጎሳ እሳት ነበልባል ለመዳን ሲል ሊሰማው የሚችል ማንኛውንም ሰውካገኘ አስቸኳይ መልዕክት እንደሚልክ ምንም የሚያጠያይቅ ጉዳይ አይደለም የሚል እምነት አለኝ፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አዲስ ያገኘውን ብሄራዊነት እና አርበኝነት በህዝቡ ዘንድ ለመፈተን ኃይለማርያምንየተነፋ ፊኛ አስይዞ ወደ አየር እንዲንሳፈፍ ማድረግ የሚቻል ጉዳይ ነው፡፡ የሙከራ ፊኛ እንደ ዋና ፊኛ ሆኖ ሊያገለግልይችላል የሚል እምነት አለኝ፡፡

በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አለቆች ቆፍረውት በነበረው ስለኢትዮጵያ የጎሳ መቃብር በግድግዳውላይ የተጻፈውን ማንበብ ጀምረዋል፣ እናም እራሳቸውን ለማዳን ሲሉ ስለብሄራዊ አንድነት፣ የጋራ ማንነት፣ ስለአርበኝነት፣ወዘተ በድፍረት መናገር ጀምረዋል፡፡

የኃይለማርያምን ስሜታዊ የድንፋታ ንግግር ከሚገባው በላይ አንብቤዋለሁ ወይም ትንታኔ ሰጥቸበታለሁን? የወያኔወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች ሲያልቅባቸው ሌላ ማታለያ ይዘው ይቀርባሉን? በኃይለማርያም የማጭበርበርየጥፋተኝነት ኃላፊነትን በሌሎች ላይ ለመጫን በሚደረገው እርባናቢስ ገለጻ ላይ ህዝቡ አወንታዊ ምላሽ ካለውምናልባትም ከእርሱ ጋር መጓዝ ይችላሉን?

በግድግዳው ላይ የተጻፈው ጽሑፍ፣

የሕዝብ የውልደት ሱናሜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን አጥለቅልቆታል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሲያራምደው የቆየው የጎሳ ፌዴራሊዝም/ክልላዊነት እሳት ነበልባልእንደገና ወደ እርሱ ዞሮ ሊለበልበው እንደሚችል እና ዶግ አመድ እንደሚያደርገው በዚህም ሳቢያ ሊከተል የሚችለውንአሉታዊ እንደምታ በግልጽ ተመልክቶታል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የማታለያ ሸፍጥ ተይዘው ያሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩወጣቶች አሉ፡፡

ወጣቶቹ በጫካኝ የወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ መገዛትን አይፈልጉም፡፡ የእራሳቸውን መንግስት መመስረት ይፈልጋሉ፡፡እነዚህ ወጣቶች ነጻነት፣ ዴሞክራሲ እና የሰብአዊ መብት ጥበቃ እንዲኖር ይፈልጋሉ፡፡

ጊዚያቸውን ይጠብቃሉ፡፡ በየዕለቱ ስሞችን ይጽፋሉ፡፡ የእራሳቸውን ጓደኞች እና ጠላቶች ለይተው አሳምረው ያውቃሉ፡፡

25 ዓመታት በላይ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኢትዮጵያ መከራ እና ስቃይን ያሰራጨ ጨቋኙ እና ሰይጣኑበማለት የአማራን ህዝብ ጥላሸት ሲቀባ ቆይቷል፡፡ ዓይነት ገለጻ ለጊዜው ሰርቷል፣ ሆኖም ግን በዘላቂነት ሊሰራአልቻለም፡፡ አሁን የከሸፈ ጥይት ሆኗል፡፡

እንግዲህ የእርሱ አባባል እውነት ቢሆን እንኳ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ  “አማራ ጨቅዋኝ መንግስትአያለአንደሚተርከው በአሁኑ ጊዜ ራሱ  “አዲሱ አማራሆኗል፡፡ እነዚህ ግፈኛ ሸፍጠኞች በሁሉም ህዝብ በከፋ መልኩተጠልተዋል፡፡ (ይህንን እውነታ ሸፋፍኘ  ባልፈው ደስ ባለኝ ግን አልችልም ፡፡)

ይህ ሊካድ የማይችል ሀቅ ነው! ይህንን ነገር ያልኩት እኔ አይደለሁም ምክንያቱም እኔ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድንስብስብ ከሚሰራው እኩይ ምግባር በተጻራሪው የቆምኩ ሰው በመሆኔ ብቻ አይደለም። 

የእኛ ታላላቆች እንዲህ ይላሉ፣የዛሬ ፍሬዎች የነገ አበባዎች

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ 25 ዓመታት በፊት የዘራው ዘር በአሁኑ ጊዜ ጥላቻን ላዲስ ትውልድ ለማጨድበስሎ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን፣ ወይም ደግሞ አመራሮችን፣ ወይም አባላቱን የግል ችግር የለኝም፡፡ እንደግለሰቦችስለእነርሱ ምንም ዓይነት ጉዳይ የለኝም፡፡

እኔ ጉዳዬ ያለው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች በኢትዮጵያ ላይ የጎሰኝነት ጥላቻን እና የኃይማኖትጽንፈኝነትን በማራመድ ሀገሪቱን ለማጥፋት እና ህዝቡ ተሳስሮበት የሚገኘውን ገመድ ለመበጣጣስ ከሚያደርጓቸውሰይጣናዊ ድርጊቶች ነው ጋር ነው ጉዳዬ ያለው፡፡

ሆኖም ግን ከጎሰኝነት እና ከኃይማኖት ጽንፈኝነት ነጻ የሆነች አዲሲቱ ኢትዮጵያ ላይ ውይይት እና ክርክር እንዲደረግለማመቻቸት ታማኞች እና ቅን ልቦና ያላቸው ቢሆኑ ኖሮ እኔ ለእነርሱ ነበርኩ፡፡

/ ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዲህ በማለት አስተምረውናል፣ጨለማን ጨለማ አያስወግደውም፡፡ ይህንን ማድረግየሚችለው ብርሀን ብቻ ነው፡፡ ጥላቻን ጥላቻ አያስወግደውም፡፡ ይህንን ማድረግ የሚችለው ፍቅር ብቻ ነው፡፡

ምንም ዓይነት የፖለቲካ ስልጣን እንደማይፈልግ እና እንደሰብአዊ መብት ተሟጋችነቴ ጥላቻን በፍቅር ከማሸነፍ ጦርነትጋር ከማንኛውም ሰው ጋር ለመወያየት እና አስተያየቴን ለማካፈል ፈቃደኛ ነኝ፡፡

/ ኪንግ እንደዚያ ዓይነቱን ፍቅር በተቃራኒ ጾታ ላይ ሳይሆን ሰው በሰውነቱ ብቻ እራስን በተወ አኳኋን ሰውን እንደወንድም እና እንደ እህት ማፍቀር፣ በአጠቃላይም ማህበረሰቡን ማፍቀር ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት አምላክ ሰውንእንደሚወድ ሁሉ ሰውም አምላኩን እንደሚወድ ዓይነት ማለት ይሆናል፡፡

ጥላቻን እጠላለሁ ምክንያቱም፡

ጥላቻ በናዚ ጀርመን አገዛዝ ጊዜ 6 ሚሊዮን ህዝቦች እና ቁጥራቸው ላልተነገረ የክርስትና እምነት ተከታዮች እና ለሌሎችህዝቦች ሞት ምክንያት ሆኗል፡፡

ጥላቻ ህንድ .ኤአ. 1947 ነጻነቷን ከተጎናጸፈች በኋላ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህዝቦች እንዲያልቁ አድርጓል፡፡

ጥላቻ .. 1971 በባንግላዴሽ (ምስራቅ ፓኪስታን) በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህዝቦች እንዲያልቁ አድርጓል፡፡

ጥላቻ በቢያፍራ (በምስራቅ ናይጀሪያ) ከሚሊዮን በላይ ህዝቦች እንዲያልቁ አድርጓል፡፡ 

ጥላቻ .. 1972 በቡሩንዲ 10 ሺዎች የሚቆጠሩ ህዝቦች እንዲያልቁ አድርጓል፡፡

ጥላቻ .. 1985 – 79 ድረስ ባሉት ዓመታት ውስጥ ባካምቦዲያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህዝቦች እንዲገደሉአድርጓል፡፡

ጥላቻ .. 1994 በሩዋንዳ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎች ህይወት ህልፈት ምክንያት ሆኗል፡፡

ጥላቻ .. 1985 – 2015 ባሉት ዓመታት ውስጥ በደቡብ ሱዳን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህዝቦች እንዲያልቁአድርጓል፡፡

ጥላቻ በኢትዮጵያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎች እንዲያልቁ አድርጓል፡፡

ጥላቻ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቼን እና እህቶቼን ወይም ደግሞ ማንኛውንም የሰው ልጅ ፍጡር የሆነን ሁሉ ሲገድልብኝማየት አልፈልግም፡፡

ኢትዮጵያውያን/ ከታሪክ እንዲህ የሚል ትምህርት መማር አለባቸው፡ጥላቻ እነርሱን ከመግደሉ በፊት እነርሱ ጥላቻንከልቦቻቸው እና ከአዕምሯቸው ውስጥ መንጥቀው በማውጣት መግደል አለባቸው!”

ኔልሰን ማንዴል እዲህ ብለው ነበር፣ትምህርት ዓለምን ለመለወጥ ልንጠቀምበት የሚገባ ጠቃሚ መሳሪያ ነው፡፡

በሌላ በኩልም እንዲህ የሚል አባባል አለ፣ድንቁርና አምባገነኖች በእጃቸው ይዘው የሚጠቀሙበት ጠቃሚ መሳሪያነው፡፡

ዋነኛው እና ተመራጩ መንገድ እሳትን በእሳት ሳይሆን በውኃ ማጥፋት ነው፡፡

ዋነኛው እና ተመራጩ መንገድ ጥላቻን በጥላቻ ሳይሆን በፍቅር እና በእውቀት ብርሀን መዋጋት ነው፡፡

ዋናው እና ተማራጩ መንገድ ድንቁርናን በእውቀት እና በትምህርት መዋጋት ነው፡፡

ኢትዮጵያ የሩዋንዳን፣ የካምቦዲያን፣ የደቡብ ሱዳንን፣ ወይም ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ ያለ ዕደል ያላቸው ሌሎች ሀገሮችንዓይነት ዕድል እንዲገጥማት አልሻም፡፡

የኃይለማርያም የጩኸት እወጃ ከዚያም በላይ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ፍላጎት እና ሀሳብ ቢሆንም ጥላቻንማቆም እና ቁስሉን የማዳን እና የእርቀ ሰላም ሂደቱን መጀመር ከሁሉም በላይ የተሻለው እና ተመራጩ መንገድ ነው፡፡ከዚያም እኔ ሙሉ በሙሉ ከዚህ ሀሳብ ጋር ነኝ፡፡

በርካታ ሰዎች የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች በምንም ዓይነት መልኩ ጥፋታቸውን የማያምኑ እናእራሳቸውን ከሕግ በላይ ያደረጉ፣ ምንም ዓይነት ተስፋ የማይጣልባቸው እና ተስፋ የቆረጡ ስብስቦች ናቸው የሚሉ ሰዎችእንደሚኖሩ አውቃለሁ፡፡

ጠቃቀጠቋማው ጅብ ዥንጉርጉር ቆዳውን ለመለወጥ ቢፈልግም እንኳ መለወጥ አይችልም የሚል አስተሳሰብ ያላቸውሰዎች አሉ፡፡

ከድንቁርና እና ከጥላቻ ጉድጓድ ውስጥ ተመንጥቀን በመውጣት ከፍተኛ የሆኑ አወንታዊ ነገሮችን ማከናወን እንችላለንብዬ አስባለሁ፡፡

ሆኖም ግን  መማር እና አዕምሯችንን መጥፎ ነገሮችን ከመፈልፈል እንዲያቆም ማድረግ አለብን፡፡

መሞከር ከቻልን ብቻ ልንማራቸው እና ከመተግበር ልናቆማቸው የሚገቡ ነገሮች፣

ልንማራቸው የሚገቡ በርካታ ነገሮች አሉ፣ እንደዚሁም ሁሉ መሞከር ከቻልን ብቻ ከመተግበር ልናቆማቸው የሚገቡበርካታ ነገሮች አሉ፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች ከዶ/ ሴውስ (አዎ ድመት በባርኔጣ ውስጥደራሲ) መጽሐፍውስጥ እንዲህ የሚል ቁምነገርን መማር ይችላሉ፣ወደ ግራም አስብ፣ ወደ ቀኝም አስብ፡፡ እንደዚሁም ወደ ታች አስብ፣ወደ ላይም አስብ፡፡ ኦ፣ ማሰቡን መሞከር ከቻልክ ብቻ ነው አዲስ የአሰራር ዘዴ ወይም ሀሳብ ልታገኝ የምትቸለው!“

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እራሱን ከአደጋ ለመጠበቅ እና የሙጥኝ ብሎ በያዘው ስልጣኑ ላይ ለዘላለምለመቀጠል የሚያስባቸው ሀሳቦች አሉ፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጥላቻን ሲያራምድበት የቆየበትን መንገድ እንደገና የማየት እና ከዚህ መጥፎ ድርጊትታቅቦ እንደገና ፍቅርን ወደ መስበኩ ሁኔታ የሚያስባቸው ሀሳቦች አሉ፡፡

ሆኖም ግን እንደ ኢትዮጵያዊነት ዋና ቁልፍ ችግር ግራ ማሰብ እና ቀኝ ማሰብ መቻል ነው፣ ወደታች ማሰብ እና ወደላይማሰብ መቻል ነው፡፡ ኦ፣ ማሰቡን መሞከር ከቻልን ብቻ ነው አዲስ የአሰራር ዘዴ ወይም ሀሳብ ልናገኘው የምንችለው! 

ለማሰብ ደፋር ሁን! 

ለማወቅ ደፋር ሁን! 

ለመማር ደፋር ሁን! 

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ነሐሴ 26 ቀን 2007 .

 

Filed in: Amharic