ከ 10 ቀናት በኃላ ከ30 ደቂቃ በፊት ለ 3 ደቂቃ በዝዋይ እስር ቤት በልዩ ጥበቃ ለብቻው በ 7 ወታደሮች ተከቦ ተመሰገንን አግኝተነዋል። ተመስገንን ሰናገኝው ምንም ማውራት ባንችልም ሲራመድ እንደሚያሰቸግረው አይተናል። እሱም ከሌሎቹ ህመሙ ውጪ ጨጓራው እጅጉን መታመሙን ነግሮናል። እስካሁን የት እንደነበረ ምን እንዳረጉት በንጠይቅም ወታደሮቹ መመለስም ሆነ መጠየቅም አይቻልም ብለው ከልክለውናል። ተመሰገንን ከበው ካመጡት ወታደሮች መካከል ሀላፊያቸውን እስካሁን ለምን እዚህ እንዳለ አልነገራቹህንም ስንለው ተመስገን እዚህ ያገኘነው ዛሬ ነው ብሎናል። የሆነው ሆኖ ተመሰገንን አግኝተነዋል። እናታችንም ከገኛቹሁት ብላ እንደ ሌሎቹ ቀን ዛሬም የቆጠረችውን ስንቅ አልተመለሰም አቀበለነዋል። እናታችን ዛሬ ሰሀን ይዘን አንመጣም እንባሽ ታብሷል። ተመስገንን አጣነው ካልንበት ግዜ አንስቶ ከጎናችን መሆናቹህን ላሳያቹሁን ሁሉ እጅግ በጣም እናመሰግናለን።
ታህሳሰ 7/09ዓም