>

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሐኪም ቤት መግባቱ ተገለጠ [ዶይቸ ቬለ]

በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ረፋዱ ላይ ዝዋይ ባቱ ሐኪም ቤት እንደገባ የተመስገን ታናሽ ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ ለዶይቸ ቬለ ተናግሯል።

 ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሆስፒታል ገባ-ቤተሰቦቹ

በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ረፋዱ ላይ ዝዋይ ባቱ ሐኪም ቤት እንደገባ ተሰምቷል። የተመስገን ታናሽ ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ ለዶይቸ ቬለ ዛሬ እንደገለፀዉ  ጋዜጠኛ ተመስገን በምን ኹኔታ ላይ እንዳለ ለማወቅ ወደ ሐኪም ቤቱ ሄደው ቢጠይቁም መግባት እንደተከለከሉ ገልጧል።

ታሪኩ ጋዜጠኛ ተመስገንን ካለፉት ዐሥር ቀናት አንስቶ ማየት እንዳልቻሉ፥ በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝም እንደማያውቁ  አስታውቋል። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይገኝበታል የተባለው የባቱ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ኑራ ነገዎ «እንደዛ የሚባል ሰው እኛ ጋ አልገባም» ሲሉ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ

Filed in: Amharic