>

ቪኦኤ ከሰዓታት በፊት [በጋዜጠኛ ወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን]

wosenseged-gebrekidanኢዩኤል ባዬ የ7 አመት ልጅ ነው። በቆሼ በተፈጠረው አደጋ የተነሳ ጉዳት ደርሶበት አለርት ሆስፒታል ይገኛል።ከ #VOA ፅዮን ግርማ በስልክ አነጋገረችው።
~ ችግሩ ሲፈጠር አንተ የት ነበርክ?
~ ከጓደኞቼ ጋር እየተጫወትኩ ነበር፣ ቆሼ ላያችን ላይ ወረደብን።
~ አንተን ማን አወጥህ ከዛ?
~ ራሴ እየሮጥኩ /በጣፋጭ የልጅ አንደበት/
(የኢዩኤል አስታማሚ አክስቱ ናት። በመሃል ገብታ እንደተናገረችው ለእሱ አልተነገረውም እንጂ ወላጅ እናቱና እህቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል)
====
ሌላዋ ተጎጂ ምልዕተ ደበበ ትባላለች። እዛው አለርት በህክምና ላይ ትገኛለች።
~ በወቅቱ አንቺ የት ነበርሽ?
~ ቤቴ፣ ከቤተሰቦቼ ጋር ••• አደጋው ሲፈጠር ህፃኗን ልጄን ይዤ ልወጣ ስል አፈሩ ተጫነኝ።
~ ማን አወጣሽ?
~ ሰዎች ናቸው ቆፍረው ያወጡኝ።
~ ቤተሰቦችሽስ?
~ የት እንዳሉ አላውቅም።
~ ባለቤትሽ ምን ነበር ስራው።
~ በየቤተክርስቲያኑ እየሄደ ጧፍ ነበር ሚሸጠው።
~ ልጆችሽ ስንት ናቸው? ዕድሜያቸውስ?
~ አንዷ 7 አመት ከ8 ወር አንዷ ደግሞ 1 አመት ከ7ወር
(ከምልእተ አጠገብ ያሉ ሰዎች ለጋዜጠኛዋ እንደነገሯት እሷ ከህመሟ ስላላገመች አልተነገራትም እንጂ ባለቤቷም፣ ሁለቱም ልጆቿም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። አስከሬናቸው ተገኝቶም ተቀብሯል)

አህ!••• ልብ ያደማል!!
በህይወት ያጣናቸውን ወገኖች ሁሉ ነፍስ ይማር!!

Filed in: Amharic