>

የትግራይ አለም አቀፍ ድንበር እየተሰመረ ነው! (ሙሉነህ ዮሃንስ)

ወልቃይት የጎንደር መሆኑን አፄ ዮሃንስ መሰከሩ እውነቱ ወጣ ብላቹህ እነደ ክስተት የምትቆጥሩ ሰወች ወያኔ በሃይል መውሰዱን መች ክዶ ያውቃል! ጉዳዩ እንዴት በሃይል እናስመልስ ነው። የወልቃይት አማራ ማንነት ኮሚቴ ያለው እኮ ወልቃይት ህዝቡ ትግሬ ሳይሆን አማራ ነው መሬቱም የጎንደር ነው።
ይልቅስ ወያኔ ትግሬንና ትግራይን ወደየት እየወሰዳቸው ነው የሚል ቁርጠኛ ጥያቄ እናንሳ።
1) የብአዴን አሽከሮቹን ተጠቅሞ ወደ ጎንደር የቀረችውን የጠገዴ ለም የግጨው ምድር ጠቅልሎ ትግሬ ነው ብሏል።
2) ቆላ ወገራ ውስጥ ያለው ደጀና ድረስ የእኔ ነው ብሎ አስምራል።
3)ሰፊውን የአርማ ደጋን በርሃ የዋልድባን ገዳም ጨምሮ በሙሉ ወደ ትግራይ ለመከለል ከፍተኛ የደህንነት የስለላ የወታደርና ተያያዥ ዝግጅት እያርረገ ነው።
4) በራስ ዳሸን በኩል አሁንም Google earth ገብታቹህ ብታዩ ተራራው እግርጌ ድስረ በአለም አቀፍ ካርታ ትግራይ አስብለውታል። ራስ ዳሸን ብዙ ቦታ ላይ ሆናቹህ ፎቶ ስትነሱ ቦታው ትግራይ ውስጥ መሆኑን አሁንም ይነግራቹሃል። ይህን የሚያደርጉት የኢትዮጵያ ካርታ ድርጅት ለአለም አቀፍ ተቋማት አሳልፎ በሚሰጠው የይፋ ካርታ ስራ ነው።
5) ራስ ዳሸን ላይ ያስገነቡት ትልቅ የመገናኛ ታወር/ማማ በሚደንቅ ሁኔታ ቢሮው ትግራይ ውስጥ ነው። መረጃ ይዘን ነው የምንግዘበው። ይህ ሁሉ ቅድመ ዝግጅትና እሩጫ መጨረሻቸውን እያዩት ስለሆነ የትግራይን አለም አቀፍ ደንበር እያሰመሩ ነው። ይህ ግን ሳይወዱ በግድ ይቀለበሳል። አርቀው ስለማያስቡ ቅንድባቸው ስር ያለው እንቅፋት አደናቅፎ ይጥላውዋል። እኛ ዝም ብንል ቁንጣናቸው ሆዳቸውን ይተረትረዋል። ሰው ቢታገሳቸው የንፁሃንን ደም የሚበቀል ፈጣሪ አይምራቸውም። የተኛህ ንቃ!።

Filed in: Amharic