>
5:13 pm - Tuesday April 19, 3672

ህወሓት በቤኒሻንጉል (ሃብታሙ አያሌው)

ቤኒሻንጉል የሚል ክልል ለመስራት ገሚሱን መሬት ከጎጃም መተከል ገሚሱን ደግሞ ከወለጋ ወስዶ ካርታ የሳለው ህወሓት ነው። ከዚያም አንድ ክልል ሰራሁ በማለት አፋን ኦሮሞም አማርኛም ተናጋሪውን ዜጋ ከዛሬ ጀምሮ ሀገር አልባ ናችሁ ሲል ህግ ፃፈ። ያ የጥላቻ ካርታ ያ ኢፍትሃዊ ህግ ዜግነትን ገድሎ ለህወሓት የፖለቲካ መጫወቻ ዋነኛ ካርታ ሆኖ ሲያገለግል ኖረ። መለስ የዘራውን መርዝ ዛሬም ከማመርቀዝ የሚታደገው አልተገኘም የዘራው በቅሎ ያሳደገው አፍርቶ ዜጎች በግፍ ሲፈናቀሉ እሱ በፓርላማ ሞፈር ዘመት እያለ የአማራ ጠላት ነው ማኒፌስቶውን ሲያስፈፅም ኖረ፤ ዛሬም የቤንሻንጉሉ አስተዳዳሪ የጌታውን የሙት መንፈስ ተቀብሎ እየተመራ በአደባባይ “መሬት ወራሪ አማሮች ተፈናቅለዋል” በማለት የግፉን ማረጋገጫ ሰጥቷል።

አያይዞም 600 ሺህ ብር መድበን የአውሮፕላን ትኬት በመቁረጥ የትግራይ ተወላጆችን ወደ ክልላቸው መልሰናል፤ ሲል አመላለሱ ቢለያይም ፍረጃው ለየቅል ቢሆንም። እሳቱ መርጦ እንደማይበላ መፃዒው ከዚህ እንደሚከፋም ምልክት ሰጥቷል። ህወሓትን እና አሽከሮቹን ተባብረን ካላስቆምናቸው ጉዳቱ ይብሳል ። እርስ በራሷ የምትለያይ መንግስት ትጠፋለች።

Filed in: Amharic