>
5:13 pm - Saturday April 19, 7664

ህወሓት እየገደለ ነው ትግሉም ተጠናክሮ ቀጥሏል (ሃብታሙ አያሌው)

ህውሓት ነፍሰ በላ አልሞ ተኳሾቹን “የአጋዚ ጦር” በማሰማራት በአንድ ጀምበር በጨለንቆ 13 በወልድያ 3 በጎንደር 2 በአዴግራት 2 በአጠቃላይ የ20 ዜጎችን ነፍስ ቀጥፏል። ደሴ ሙሉ በሙሉ በመከላከያ እዝ ስር እንድትሆን መወሰኑም ታውቋል።
ባህርዳር፣ ወልዲያ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደብረ ታቦር፣ ወልዲያ ቆቦ፣ ጎንደር፣ ደሴ ሐይቅ፣ ሐረር ጨለንቆ ከፍተኛ ቁጥር ባለው የአጋዚ ኃይል ተከበዋል። የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በየቦታው የተሰማራ ሲሆን ከህወሓት ነፍሰ ገዳይ ወታደሮች ጋር መተባበር ባለማሳየቱ ሁኔታው በህወሓት መንደር ከፍተኛ ጭንቀት ፈጥሯል። የመከላከያ አንድ እዝ ከፌደራል ፖሊስ ጋር ተቀናጅቶ በአማራ ክልል ካሉ ዩኒቨርስቲዎች ከትግራይ የተመደቡ ተማሪዎችን ወደየ አዳራሹ እያስገቡ ልዩ ጥበቃ እያደረጉ እንደሆነ ከስፍራው የተገኙ መረጃዎች አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ደረጃ ተማሪዎች ለስርአት ለውጥ ያላቸውን ሚና ተገንዝበው እንዲታገሉ የቀረቡ ነጥቦች...
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሃገራዊ ሃላፊነት በእናንተ እጅ ወድቋል። በተማሪዎች ላይ የሚደረግ ማንኛዉም ጥቃት መወገዝ አለበት። በተለይ ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት መዘዙ ከባድ ነው። የከፋ ዋጋ ያስከፍላል። አማራና ኦርቶዶክስ መጥፋት አለባቸው ብሎ የተነሳው ወያኔ የትግራይን ወጣት ለዘመናት መርዝ ሲግተው ኖሯል። በቅርብ ጊዚያት ደግሞ አማራና ኦሮሞ ተባብረው ሊያጠፉን ነው እያሉ ቅዠት ለቀውባቸው ከአቅማቸው በላይ በትእቢት የተሞሉ የዘር ልክፍተኞች ለትምህርት የሄዱ ተማሪዎች ላይ ጭፍጨፋ እየፈፀሙ ነው።

በአሁኑ ሰአት ወያኔ ይህን ትውልድ ማስተዳደር ቀርቶ እንደለመደው እንኳን በሃይል መቆጣጠር አይችልም። ይህን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ተማሪዎች በቅጡ በመረዳት ለሃገርና ለወገን የሚበጅ አካሄድ እንዲከተሉ ወንድማዊ ምክሬን እለግሳለሁ፦

1) የተማሪውን ህብረት/አንድነት ማጠንከር። ይህ አሁን ጎልቶ ከምንሰማው የአማራና የኦሮሞ ከመሆን ልቆ የሁሉም ለውጥ ፈላጊ መሰባሰቢያ ማድረግ።
2) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ጥያቄ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እንዲቀላቀሉት ማድረግ በጣም ወሳኝ ነው።
3) የሚነሱትን የተማሪዎችም ሆነ ሃገራዊ ጥያቄዎች በጋራ እየወሰኑ ለህዝብ ቶሎ ቶሎ ይፋ በማድረግ ህዝብን ትክክለኛ ግንዛቤ ማስያዝና ይሁንታ መገንባት።
4) የኢትዮጵያ ተማሪዎች ሶስት ተከታታይ መንግስታትን በመቀየር ትልቁን ድርሻ እንደተወጡ በማስታወስ አሁንም ያ ታሪካዊ ሃላፊነት እናንተ ትክሻ ላይ መውደቁን ተገንዝባቹህ በማስተዋል ተራመዱ።
በግፍ ለተገደሉ ወጣቶች ነፍስ ይማር። ለቤተሰብና ለጓደኞቻቸው መፅናናትን ይስጥልን።

ወላጆች ከየዩኒቨርስቲው ልጆቻቸውን በቶሎ ወደቤታቸው እንዲመለሱ በማድረግ የህወሓት ነፍሰ ገዳይ የአጋዚ ኃይል ከሚፈፅመው እልቂት መታደግና ትግሉን በየቀየው ተቀናጅቶ መምራት እንዲቻል ሁሉም የተቻለውን ቢያደርግ መልካም ነው። ከዩኒቨርስቲ እየወጡ ያሉ ተማሪዎች በፍጥነት ወደየ ቀያቸው እንዲደርሱ በየቦታው ትብብር እንዲደረግ ሚዲያው የድርሻውን ይወጣ የሚል መልዕክት ከተማሪዎች በውስጥ መስመር ተልኳል።

Filed in: Amharic