“ሃይል” (power) ማለት አንድን ነገር መለወጥ (Change) የሚስችል አቅም ነው፡፡ ሃይል ቀጥተኛ የሆነ (active) እና ቀጥተኛ ያልሆነ (passive) በማለት ይከፈላል፡፡ ቀጥተኛ የሆነ ሃይል ለውጥን የማምጣት አቅም ሲኖረው ቀጥተኛ ያልሆነ ደግሞ ለውጥን የመቀበል አቅም አለው፡፡ ለምሳሌ ወርቅን የማቅለጥ ቀጥተኛ አቅም አለው፣ ደግሞ የመቅለጥ (ለውጥን የመቀበል) ቀጥተኛ ያልሆነ አቅም አለው፡፡ የመቅለጥ አቅም የለውም፡፡ ስለዚህ በእሳት ሙቀት እንደ ወርቅ ቀልጦ ቅርፁን በመቀየር ለውጥን አይቀበልም፡፡ አፈር በእሳት ይፈረካከሳል እንጂ አይቀልጥም፡፡ በመሆኑም አፈርን እሳት የምትጥደው ለመፈካከስ እንጂ ለማቅለጥ መሆን የለበትም፡፡ ኢህአዴግን ለመቀየር የሚያደርጉት ጥረት ህወሃትን ለመቀየር ሳይሆን ለመፈረካከስ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ህወሃት በኢትዮጲያ ፖለቲካ ውስጥ የማይገባው ጥቅም እያገኘ ያለ ጥገኛ (Parasite) ነው፡፡እስኪ አንድ …እንደው እንድ የህወሃት አመራር ወይም ደጋፊ “የኦህዴድና ብአዴን ጥያቄ ተገቢነት አለው ወይም ተገቢ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል” የሚል ነገር ሲናገር ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? በጭራሽ የለም! ዛሬ ብቻ ሳይሆን ከ18ኛው ክ/ዘመን በጥባጭ ራስ እስከ 20ኛው ክ/ዘመን የህወሃት መስራቹ ፣ ከአቦይ ስብሃት እስከ አባይ ፀሃዬ ብትመለከቱ ሁሉም ለማረጋገጥ የሚታትሩ ዱኩማኖች ናቸው፡፡ ሁሉም ጥገኞች ናቸው! ጥገኛ ሃይልን ነቅለህ ትጥለዋለህ እንጂ የጋራ ጥቅም (mutual benefit) እንዲኖር አትጠይቀውም፡፡ ምክንያቱም ለጋራ ጥቅም የሚሆን የሚያበረክተው የራሱ የሆነ ነገር የለውም!! አፈርን መፈረካከስ እንጂ ማቅለጥ አይቻልም፡፡ ጥገኛ ተውሳካን መንቀል እንጂ ማባበል አያስፈልግም!! ሺህ አመት ብታባብሉት ህወሃት ከጥገኝነቱና ከራሱ ጥቅም ሌላ ነገር ማሰብ እንኳን አይችልም!!
