>

ጠቅላይ ሚንስትሩ ፓርላማውን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብንም ንቀዋል!! (ደረጀ ገረፋ ቱሉ)

በአንድ ሀገር የፓርቲ  ስራ አስፈፃሚም ይሁን መዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ የፓርቲው ነው። ፓርላማ ግን የሚወክለው ህዝቡን ነው።በአንድ ሀገር በማንኛውም መስፈርት እና ስማቸውም እንደሚያሳየው የህዝብ ተወካዮች የሚያቀርቡት ጥያቄ የህዝቡን ነው ተብሎ ይታሰባል።ለህዝብ ተወካዮች የሚሰጠው ክብርም የሀገሪቷን ህዝብ እና ህግ እንደማክበር ይቆጠራል።
በየትኛውም ሀገር አንድ ጠቅላይ ሚንስትር ምንም ዓይነት ስራ ብበዛበት ማቋረጥ ካለበት የሚያቋርጠው ሌላኛውን ስራውን ነው እንጂ ከህዝብ ተወካዮች የቀረበለትን ጥር አይደለም። በየትም ሀገር አንድ ጠቅላይ ሚንስትር ፓርላማው ጥር ካቀረበለት አይደለም የፓርቲ ስብሰባ ሽንቱን ሁሉ አቋርጦ ወደ ፓርላማ ይሄዳል።ያውም ሽንቱን እያንጠባጠበ!!
እዚህ ሀገር ግን ሀገር ብቻ ሳይሆን ዓለም ጉድ እስክል ድረስ  የህዝብ ተወካዮች ጠቅላይ ሚንስትሩን አናግረን ብለው ደጅ መጥናት ከጀመሩ ሁለት ሳምንት አልፏቸዋል።
የሚገርመው ፓርላማው አልሰበሰብም ብሎ አድማ እስክያደርግ ድረስ ጠቅላይ ሚንስትሩ የህዝብ ተወካዮቹን ያላናገሩት ታመው ወይም በሌላ ምክንያት አይደለም። እሳቸው ሁለት ሳምንት ሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ምን እያወራ ስለማያውቀው የኢህአዲግ ስራ አስፈፃሚ ከሚሉት ህቡዕ ቡድን  ጋር በኢትዮጵያ  ህዝብ ላይ እየዶለቱበት ነው።አንድ ቡድን በህዝቡ ላይ የማይዶልትበት ከሆነ 15 ቀን ሙሉ ከህዝቡ ተደብቆ ስለህዝቡ የሚከራከርበት ምንም ምክንያት የለም። ነገሩ በህዝብ ላይ መዶለት ካልሆነ ምን አስደበቀው?
ለማንኛውም ወደ ጠቅላይ ሚንስትሩ ስንመለስ ፦
በኢህአዲግ ስራ አስፈፃሚ ስም በህቡዕ ተሰብስበው  በህዝብ ላይ እየዶለቱም ቢሆን ጣቅላይ ሚንስትሩ ፓርለማውን ንቀው ሄደው ስለ ደቡብ ሱዳን ስወያዩ አይተናል።
በአጭሩ ጠቅላይ ሚንስትሩ ፓርላማው ጥያቄ አለኝ እያለ የዓለም ሚዲያ ጭምር ስዘግብ እሳቸው እንዳላየ እና እንዳልሰማ ለሁለት ሳምንት ደጅ ስያስጠኑ የናቁት ፓርላማውን ብቻ አይደለም።እሳቸው እና ወዳጆቻቸው ፓርላማውን ብቻም ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብንም ንቀዋል።
የኢትዮጵያን ህግ ንቀዋል።
ለዚህ ደግሞ ይዋል ይደር እንጂ እሳቸውም ሆኑ እሳቸው ህዝብ እንድንቁ  አይዞህ ያሉአቸው የጀርባ ወዳጆቻቸው ዋጋ ይከፍሉበታል!!

Filed in: Amharic