>
5:13 pm - Sunday April 19, 7243

"የትግራይ የበታችነት" ብለን ደግሞ እንሞክረው! (መልካሙ ተመስገን)

“የትግራይ የበታችነት”.. ተቀባይነት ከገኘ፣ሌሎቹ ክልሎች”… ያደጉ፣በእንዱስትሪ የዳበሩ፣በጦርነትና በተፈጥሮ አደጋ ያልተጎዱ ናቸው…” እንበላቸው?
መንግሥቱ ኃ/ ማርያም ወያኔ ሥልጣን ሳይዝ ከአንድ አመት
አሰቀድሞ በ1990 ሸንጎው በደረገው ስብሰባ ላይ፣የትግራይ አስተዳዳሪ የነበረውን ሙልጌታ ሐጎስን የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቆት ነበር።
“…ለመሆኑ በዚህ አስራ ስድስት አመታት (በደርግ ዘመን)
ውስጥ፣የትግራይን ህዝብ ግብር ክፈል ብለነዋል? ትግራይስ
ግብር ከፍሎ ያውቃል? ለመሆኑ አንድ ቁና እህል ከገበያ ተሸምቶ ለመንግሥት ሠረተኛው ፍጆታ ቀርቦ ያውቃል? …ሙልጌታ መልስልኝ እባክህ!” በማለት መንግሥቱ ለጠየቀው ሙልጌታ ሐጎስ የሰጠው መልስ አሉታዊ ነበር።
በደርግ ዘመን ሁሉም ህዝቦች በአቅማቸውና ሁኔታ ባመቻቸው መጠን ጭቆናን ተዋግተዋል።የሲዳማ ህዝብ 10ሺህ ልጆቹን መሰዋዕት አድርጓል።ብዙ የኦሮሞ ልጆችም ለነፃነት ተሰዉተዋል።እንደ ትግራይ አይሁን እንጅ በቀይ ሽብር ብዙ የአማራ ህዝብ ልጆች ተገድለዋል።በታሪክ አጋጣሚ ለኤርትራ ተዋጊዎች በነበራቸው ቅርበት የትግራይ ልጆች ጠመንጃ አግኝተው ከመንግሥት ጦር ጋር በውጊያ መስመር ተፋልመው ብዙዎች ተሰውተዋል።ነገር ግን ትግራይ ውስጥ ደርግ ያወደመው እንዱስትሪ የለም፤አልነበረምምና።የደርግ ወታደር ያስተጓጎለው የሰፋፊ እርሻ ልማት የለም።ቀድሞም ለዚያ የበቃ መሬት አልነበረምና።በደርግ ወታደር የወደመ ድልድይና የልማት ፕሮጄክትም ያለ አይመስለኝም፤እንዳውም በተቃራኒው “ፀረ ድልድይ ትግሬ” ሲባል ይሰማ ነበር።

ያም ቢሆን “የጮሌዎች ” ጨዋታ ማድነቅ ከልሆኔ መፍረስስ የሚገባቸው ስንት ድልድዮች ትግራይ ውስጥ ነበሩ?
ወያኔዎች ” ከደርግ ሠራዊት ለመከላከል አፈረሱት “ቢባል እንኳን ማለቴ ነው።መታወቅ ያለበት ደርግ ኦሮሞን፣አማራን
ሶማሌን፣ሲዳማንም ገድሏል።እነዚህ ህዝቦች እስከ ዛሬ የተለየ የድጋፍ በጀትና ካሣ የላቸውም።የህዝብ ሀብት ተዘርፎ በትግራይ እንዱስትሪ ሲገነባ “….ከደረሰባቸው ጉዳት አንጻር”ይባል የነበረው አግባብነት የለውም።ኃይለማርያም ደሳለኝ ለደመወዝና ለጠ/ሚንስቴሪነት ማዕረግ ያበቁትን በማወደስ ዘረፋውን ስያመቻችላቸው እንሚደጋግመው ቃል።ለሁሉም ዜጎች ትክክለኛ የሀብት ክፍፍል መብትን ማስጠበቅ ቢቻል
ኖሮ ፍትሃዊነቱ በቂ ነው።ለሀገር ኢኮኖሚና ለህዝቡ የጋራ ሀብት አስተዋጽኦ የትግራይ ህዝብ ከሶማሌም ሆኔ ከሲዳማ ህዝብ የሚበልጥበት ሁኔታ አልነበረም።በምርት አቅርቦቱና በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ባለው ድርሻ ትግራይ ከሲዳማ ያንስ ነበር እንጅ አይበልጠውም።የህዝብ ብዛቱም ብዙ የተራራቀ አይደለም።ወያኔ ከጫካ ጠመንጃ እንጅ ዶላር ይዞ አልመጣም።
የኤፈርትም ይሁን የሌሎች የንግድ ተቋሞቻቸው መነሻ ከፒታል የተሰረቀና የማይመለስ ብድር ፣የተቀማ የህዝብ ሀብት ነው።እንኳን የወያኔ “የወል” የንግድ ድርጅት ግለሰብ ትግሬም” ብድር ወስዶ ያለመመለስ መብቱ” የተጠበቀ ነው። ይህ በመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሽያጭ (privatization) በጋምቤላ እርሻና በልማት ባንክ ብድሮች አይተናል።
አባይ ፀሐዬ እሰከ ዕለተ ሞቱ በንግድ ባንክ ቦርድ ሰብሳቢነት የሚቀመጠውም ሙያ ኖሮት ሳይሆን የዘረፋ ሚስጢር እንዳይወጣ ለመከላከል ነው።የትግራይ ልጆች በአብዛኛዎቹ የሀገሪቱ እንዱስትሪና ኢኮኖሚ ተቋሞች ውስጥ ቦርድ ሊ/መንበር፣ምክትል ቦርድ ሳብሳቢ ፣ሥራ አስፈጻሚ ሆኔው የሚመደቡት በኢትዮጵያ መንግሥት ጥናትና መመዘኛ አይደለም።በህወሃት ምደባ ነው።ይህን ምደባ “የሚያፀድቀው “ኃይለማርያ በፖሊሲ ጥናት በአባይ ፀሐዬ፤በኢኮኖሚ አለቃው አርካቤ ዕቁባይ፣በደህንነት መመዘኛው ፀጋዬ በረሔ ይመሩታል።
ከታች፣ከ1-7 ተራ ቁጥር ያሉት “በልማታዊዉ መንግሥት” የዜጎች ኢ-ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል በጥቅት ጊዜያት ውሰጥ በትንሹ በትግራይ ውስጥ የተሰሩትን ታላላቅ ፕሮጄክቶች ያመለክታሉ።
የመቀሌን ባቡርና ሌሎች ቀደም ስል የተጀመሩና ያላላቁትን ግንባታዎች አያጠቃልልም።ቀናትና ወራትን በሚገባ እዩ!የመጀመሪያዎቹ ሶስት የግንባታ ክንዋኔዎች
በአንድ ሳምንት ውስጥ የተገለጹ ሥራዎች ናቸው።በነዚህ ጊዜያት ውሰጥ የኦሮሞ ህዝብ ይደማል፣700ሺህ ህዝብ
ይፈናቀላል፣10ሺህ ይገደላል፣አሁንም ይዛትበታል።
በአመት ከስምንት ወር ውስጥ በትግራይ ውስጥ ከተከናወኑ ሥራዎች፤
1.የእንግሊዙ ኢንትሬድ ኩባንያ በመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ዘርፍ ሊሰማራ ነው ። ኩባኒያው $100,000,000.00 (አንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር) ሥራ ላይ ያውላል። 8.Jan.2018(ታህሳስ 30፣2010 ፋና)

2.መሰቦ ሲሚንቶ $70,000,000.00 (መቶ ሚሊዮን ዶላር) ኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈራረመ ። 7.Jan. 2018
(ታኅሳስ 29-2010 ሪፖርተር)

3.አስገደ ፅምብላ ወረዳ በዓመት $40,000,000.00 (የአርባ ሚሊዮን ዶላር)የወርቅ የሚያመርት ፋብሪካ ወደ መደበኛ ምርት ገባ ። ይህንን ፋብርካ ገንብቶ ለማጠናቅ የወጣው ወጪ 745ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ነው።
2 .Jan.2018(ታህሳስ 24፣ 2010)

5.መስፍን ኢንዱስትሪያል በውቅሮ ያቋቋመውን የትራክተር መገጣጠሚያ በ2 ቢሊዮን ብር ሰርቶ አስመረቀ። 23July 2017(ሃምሌ 16፣ 2009 ፋና)

6.ዓራቶ (ከመቀሌ በስተምስራቅ 25 ኪሎሜትር) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኬሚካል ማምረቻ ፋብሪካ በ5 ቢሊየን ብር እየተገነባ ነው። 24 march 2016 (መጋቢት 16፣ 2008 ፋና)

7.በ2009 ዓ/ም(2017) የበጀት ዘመን አንድ የ53 ኪሎ
ሜትር አስፋልት መንገድ በኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን
ትዕዛዝ በ2 ቢሊዮን ብር እንዲሰራ ተደርጓል።

በ2011 የፈረንጆች አቆጣጠር በአሜርካን የዕርዳታ ድርጅቶችና በኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታቲክስ መ/ቤት ጥምር ጥናቶች ቀርቦ በነበረው ዘገባ የሚከተለው ሰፍሮ ይገኛል።

1/ ምንም ገቢ የሚያገኙበት የሥራ መስክ የሌላቸው ሴቶች ከጠቅላላው የአቅሜ ሔዋን ዕድሜ ከደረሱት:
በትግራይ 24%፣ በአማራ38.4%፣በኦሮሚያ 43.9%፣
በደቡብ ህዝቦች 44.8% ነው።
2/ በዕርግዝና ጊዜ በሰለጠነ የጤና ባለሙያ ምርመራ
የሚደረግላቸው ሴቶች በትግራይ 50.1%፣በአማራ 33.6%
በኦሮሚያ31.5%፣ በደቡብ ህዝቦች 27% ነው።
3/ በ2011 የአውሮፓ አቆጣጠር የተከተቡ ህጻናት
በትግራይ 73%፣በአማራ 38.4%፣በኦሮሚያ 26.8%፣
በደቡብ ህዝቦች 38.1% ነው።
በዘህ በኩል የትግሬዎችድርሻ “ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ ወይም ምክትል ዳይሬክቴር)ሳይሆን ሁሉንም በዋናነት አሰምሮ ሰርቶታል።
በትግራይ ውስጥ ለተሰሩት ብቻ ሳይሆኑ በሌሎች ክልሎችም ለሚከናወኑት ሥራዎች በጀቱ ትንሽ ከፍ የሚል ከሆኔ የግዴታ አመራሩ በህወሃት ስምሪት መጽደቅ ይኖርበታል።
ለምሳሌ ያዩ ማደበሪያ ፋብርካ ግንባታን በበላይነት የሚመራው የጄኔራል ክንፌ ዳኘው ሜትክ ሲሆን ይህ የ700 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጄክት ሲጀመር፣የተወሰኑ ግንባታ ሥራዎች ለተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሸን የሁለት ቢሊዮን ብር ዉል ተደርጎ ክፍያ ተፈጽሟል። የግዴታ አንዱ ሌላውን “ለመጥቀም ሁኔታን ማመቻቸት” አለበትና።የትግራይ ልጅ ይሁን እንጅ የሀብት ምንጭ ይሰራለታል።..የያዩ ፕሮጄክቱ ሥራ አስፈጻሚ ደግሞ ገ/መድህን ሰብሃት ተጨማሪ የትግራይ ሰው ሲሆን ቀጥታኛ ባልሆኔ ግኑኝነት በጠቅላይ ሚንስቴር አማካሪነት ሥልጣኑ ትዕዛዝ ሰጥቶ ያለአንዳች ውልና ክፍያ በመከላከው ስም የብዙ መቶ ሚሊዮን ብር ድንጋይ ከሰል ከያዩ እንደዘረፍና እንዲሸጥ ያስደረግ የነበረው ደግሞ አርካበ ዕቁባይ ነበር።የያዩ ፕሮጄክት ግን ኦሮሚያ ውሰጥ ነው።

Filed in: Amharic