>

የትግራይ ወታደሮች በወልዲያ ከተማ የቃና ዘገሊላ በዓልን ለማክበር በታደሙ ምዕመናን ላይ  ዘግናኝ ጭፍጨፋ ሲያካሂዱ ውለዋል! 

አቻምየለሕ ታምሩ

አማራ ለማጥቃት የሰለጠኑት ነፍሰ በላ የትግራይ  ጨካኝ ወታደሮች  በወልዲያ ከተማ የቃና ዘገሊላን  ሃይማኖታዊ በዓል  በማክበር ላይ የነበሩ ምዕመናን  ላይ ባካሄዱት ዘግናኝ  ጭፍጨፋ በደርዘን የሚቆጠሩ ንጹሐን የአማራ ልጆች በግፍ  መረፍረፋቸውንና  በመቶዎች የሚቆጠሩ ህጻናትና ሴቶች  እንዲሁም እድሜያቸው የገፋ  አዛውንቶች  ከፍተኛ  ጭካኔ  ተፈጽሞባቸው   በስቃይ ላይ  እንደሚገኙ  ከወልድያ  ሆስፒታልና ዩኒቨርሲቲ  በደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል። ልብ በሉ! ጨካኞቹ የትግራይ ወታደሮች አማራ ሲጨፈጭፉ የዋሉት ምዕመኑ የሃይማኖቱን ስነ ስርዓት ሊከውን በተገኘበት    በቤተክርስቲኑ ውስጥ ገብተው ነው።

ነፍሰ በላዎቹ የትግራይ ወታደሮች  አሸንጌን ተሻግረው ለጭፍጨፋ ወልድያ ምድር የተሰማሩበት ከትናንትና በስትያ ሲሆን  አማራን ለማጥቃት የሰለጠኑት  የትግራይ ወታደሮች ስምሪት  አላማም  የባለጊዜዎቹ ልጆች ወያኔ  አፋቸውን እንዲፈቱበት ያደረጋቸውን  የአማራ ስድብ ባለፈው ሰሞን ወልድያ ከተማ ለእንግድነት ለእግር ኳስ ጨዋታ  በመጡበት ወቅት  ስድነታቸውንና  ለከት የሌለው ማናለብኝነታቸውን  ሲያቀረሹ ዝም ማለትን  ያልፈቀደው እንግዳ ተቀባዩ ሕዝባች  የወሰዳውን  ማንነትን  የማስክበር እንቅስቃሴ  ለመበቀል መሆኑን ለማወቅ ችለናል።

ማምሻውንና እኩሌ ሌሊት ላይ ቀን ላይ ጭፍጨፋ ያካሄዱት የነበሩትን  የትግራይ ወታደሮች  ለማገዝና የቤት ለቤት አሰሳ ለማድረግ ተጨማሪ ነፍሰ በላ የትግራይ ወታደሮች እምቦቀቅላ የአማራ ህጻናትን ለመጨፍጨፍ  በተለምዶ «የሰሜን እዝ» ከሚባለው  የትግራይ ካምፕ  ወደ ወሎ ዘምተው   ወልድያ ከተማ ገብተው ለግዳጅ  መሰማራታቸው ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ለማወቅ ችለናል።

ማንነታችሁን ለመታደግ በትውልድ ቅያችሁ አደባባይ ወጥታችሁ ከትግራይ በመጡ አማራ ጠል ቅልብ ነፍሰ በሎች በግፍ ለወደቃችሁ  ሰማዕቶች  ከፍ ያለ ክብርና ሞገስ ይድረሳችሁ። በትግራይ ወታደሮች የፈሰሰው ደማችሁ  ማንነታችንን ለማክበር የፈሰሰ  የሁላችን ደም ነው። በመስዕዋትነታችሁና  በደማችሁ የጻፋችሁት ታሪክ  ከመቃብር በላይ  ከትውልድ  ጋር  ሁሉ ለዘላለም ይኖራል! ፈጣሪ አምላክ ነፍሳችሁን መንግሥተ ሰማያት ያዋርስልን!

Filed in: Amharic