>

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ ጀመሩ!

ልዩ ሃይል/አጋዚ ጋር ግብግብ ገጥሟል!

ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ትናንት ተቀስቅሷል! 

ሄቨን ዮሃንስ

ዛሬ ማክሰኞ ጥር 22 የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በወልድያ፣ ቆቦ፣ መርሳና ሌሎች ከተሞች ላይ ወያኔ እየፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋ በማውገዝ ነው። ወያኔ ሌባ ነው! የሚል መ ፈክር ጮክ ብለው እያሰሙ ነው። የተማሪው ተቃውሞ ዛሬ ከጧቱ 6:30 ጀምሮ በቴዎድሮስ ካምፓስ ነው የጀመረው። ተማሪዎቹን ለማፈን ከሚሞክሩ አጋዚዎች ጋር ግብግብ እንዳለና ተማሪው ባለው አቅሙ እራሱን ለመከላከል እየሞከሩ መሆኑ ተናግሯል። በተመሳሳይ መልኩ የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞውን ትናንት መጀመራቸው ታውቋል። እሁድ እለት ደግሞ በጎንደር ስታድየም ህዝቡ ለወልድያ ያለውን አጋርነት አረጋግጦ በወያኔ ላይ ደግሞ ቁጣውን አሰምቷል።

የመይሳው ልጆች የጎንደር ህዝብ እሁድ ለታ በእለተ ሰንበት ተሰብስበው ስለ ወልድያ ያላቸውን አጋርነት ተማምለው ከወልድያ ጎን እንቆማለን ብለዋል ።ዛሬ በወልድያ በመርሳ በቆቦ እንድሁ ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው ።የህዝብ ጥያቄ ይመለስ በድላ የሚቀየር ምንም ነገር የለም በዱላ የሚቀየርማ ቢሆን አህያ ሰው ሁና ነበር ደብዳቢዋ ደግሞ አህያ ይሆኑ ነበር ።ስለዚህ የሚያዋጣው መንግስት እውነተኛውን የህዝብ ጥያቄ መልስ መስጠት ብቻ ነው። ህዝብን በግድያ አያልቅም ሀሳብ ነው የማያልቅ የማይገደብ ሀሳብ ለዚህ ዋና ምሳሌ እስራእል ናት በጀርመኑ ናዚ ተጨፈጨፈች ምድረ በዳ ሆነችተመልሳም ከብዙ ዘመን በሓላ ሀገር ሆነች በጥንት በነብዩ ኤርሚያስ ዘመን በምርኮ በባቢሎን እጅ ወደቁ ለ70 አመታት ከዚያም መልሰው ሀገር መሰረቱ ለፈርኦን ግዞት የነበሩ ሲሄዱ 70 ነበሩ ሲመለሱ 600.000 ሽህ ሆኑ የማይፋቅ የታሪክ ተባሳ ብቻ ነው ማነስ በመብዛት ይተካል መሞት በመውለድ መንግስትም በመንግስት ይተካል ። 

ሄቨን ዮሃንስ

Filed in: Amharic