admin
የጋዜጠኞቹ እና ብሎገሮቹ የፍርድ ቤት ውሎ ”የጋዜጠኛ አስማማው ሁኔታ የችሎቱን ታዳሚ እንባ አራጭቷል” (ኣዲስ...
''የሥነልቡና ጫና ደርሶብኛል''
ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ
''ከሌሊቱ 8 ሰዓት እየተወሰድኩ ድብደባ፣ ማስፈራራት እና ወከባ ተፈጽሞብኛል''
አጥናፍ ብርሃኔ
''ለምርመራ የምጠቀምበት አንድ ኮምፒውተር ነው ያለኝ፤ ጊዜ ይሰጠኝ''
ፖሊስ
ቅዳሜ ግንቦት 9፣ 2006...
የምርጫ ሽርጉድ በ2015ቷ ኢትዮጵያ (ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
በ2015 በሚካሄደው ፓርላሜንታዊ “ምርጫ” መቅረብና መወሰን ያለበት አንድ ጥያቄ ይህ ነው፤ “የኢትዮጵያ ህዝቦች አሁን እ.ኤ.አ 2014 ያሉበት የኑሮሁኔታ ከቀድሞ 2010 ወይም 2005...
Nairobi terror attack leaves 12 dead (DAILY NATION)
The aftermath of twin blasts at the popular Gikomba market in Nairobi, where 12 people died and 78 others were injured on May 16,...
የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ክለላ ዛሬ በድብቅ ሊፈረም ነው! ከኣብርሃ ደስታ (መቀሌ)
የኢትዮ ሱዳን ዳር ድንበር በግልፅ የተከለለ እንዳልሆነ ይታወቃል። የኢትዮጵያ አርሶአደሮች የሚጠቀሙት መሬት የኢትዮጵያ እንደሆነ ሲወሰድ ሱዳናውያን የሚገለገሉበትም የሱዳን ነው ተብሎ ይታሰባል። ከቅርብ ግዜ ወዲህ...
”ሕገ መንግስቱን ሳያከብሩ – ማስከበር አይቻልም !” ከዞን 9 የተሰጠ መግለጫ
አንቀጽ 19 በተግባር ተጥሷል - ሕገ መንግስቱን ሳያከብሩ ማስከበር አይቻልም የታሳሪዎች የምርመራ ሂደትን አስመልክቶ ከዞን 9 የተሰጠ መግለጫ
አዘጋጅ Zone 9
ከታሰሩ 22 ቀናትን ያስቆጠሩት የዞን ዘጠኝ አባላትና ጋዜጠኞች በቤተሰብም ሆነ በሕግ ባለሞያ የመገናኘት መብታቸውን ለማግኘት 19 ቀናትፈጅቶባቸዋል፡፡ ከታሰሩ እስከ 17 ቀን ድረስ ማንም የቤተሰብ አባል ሳይጎበኛቸውና በወዳጅ ዘመዶች ሳይጠየቁ የከረሙ ሲሆን ከጠበቆች ጋርለመገናኘት ደግሞ 19 ቀናት ፈጅቷል፡፡ አሁንም ከጠበቆቻቸው ጋር መገናኘት ያልቻሉ ቀሪ እስረኞች አሉ፡።
በተለምዶው እነደሚደረገው የፓሊስ ማእከላዊ ምርመራ የቤተሰብ ጉብኝትን አይቻልም በሚል ቀላል ቃል የከለከለ ሲሆን ለጠበቆች ስብሰባ ላይነን የሚል ምክንያት ሲሰጥ ከርሟል፡፡ ይህ በመሆኑም የተነሳ የተያዙ ሰዎች መብት የሆነው የህገ መንግስቱ አንቀጽ 19 ሁለት ላይ ያለው የተያዙሰዎች ያለመናገር መብት ( the right to remain silent) በይፋ ተጥሶ ያለማንም የህግ ባለሞያ ምክር ለብዙ ቀናት ምርመራ ሲደረግባቸውቆይቷል፡፡
ምርመራቸውን ጨርሰዋል ተብለው የታሰቡ ታሳሪዎቸን ካልሆነም በስተቀር በምርመራ ወቅት የህግ ባለሞያ ለማግኘት አልተፈቀደላቸውም፡፡
መሰረቱ መሰረታዊ የሆነው ያለመናገር መብትና የሕግ ባለሞያ የማግኘት መብት መከልከሉ የተለመደውን ማእከላዊ ምርመራ የሚታማበትንየማስገደድ ምርመራ እውነተኛነት የሚያጋልጥ ነው፡፡ በተጨማሪም የአካልና የስነልቦና ጉዳት የማድረስ ምርመራ ሲፈጸምባቸው እነደነበረ የተያዙየዞን ዘጠኝ አባላት በተናገሩበት ወቅት ፍርድ ቤቱ የነዚህን ጉዳቶች መከልከል ላይ አስተያየት ከመስጠት ውጪ ይሄ ነው የሚባል እርምጃ እናማጣራት ለመውሰድ አልሞከረም፡፡
ማዕከላዊ ምርመራ ከዚህ በፊት የሚታወቅበት ድብደባ፣ ምግብና እንቅልፍ መከልከል፣ የስነልቦና ጫና እና ማስፈራሪያ የተለያዩ ዛቻዎችሁሉም በተያዙ የዞን ዘጠኝ አባላትና ጋዜጠኞች ላይ በተለያየ መልኩ እነደደረሰ ተረድተናል፡፡ ይህም ምርመራውን ተከትሎ የሚመጣውንማንኛውንም ማስረጃ በሕግም በሞራልም ተቀባይነት እነዳይኖረው እነደሚያደርግ እናውቃለን፡፡
ከታሳሪዎች የሚገኙ ማንኛውም መረጃዎች በከፍተኛ ተጽእኖ ስር እንደተሰጡ አንዲሁም ዝም የማለትና የሕግ ባለሞያ ምክር የማግኘት ሕገ-መንግስታዊ መብቶቻቸው ተጥሰው የተገኙ እንደሆኑ ዞን ዘጠኝ ያምናል፡፡ በወንጀል ህግ ስነስርአት መሰረት እነዚህ ያለህግ ባለሞያ ጉብኝትያለመናገር መብታቸው (የህገ መንግስቱ አንቀጽ 19) ተጥሶ የተገኙ መረጃዎች በዚህ ምክንያት ብቻ ተቀባይነት እነደማይኖራቸውም የአገሪትዋሕግ ይደነግጋል፡፡
በመሆኑም መንግስት ታሳሪዎቹን አንደፈታ እና ጉዳያቸው ሕገ መንግሰታዊ እና የወንጀል ህግ ሥነ-ስርአት ሕጉን ተከትሎ አንዲሆን እንዲያደርግናሌሎች እንዲያከብሩ የሚጠይቀውን...




























