ከአርበኞች ግንቦት 7 የሀገር ውስጥ አቀባበል ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

ከአርበኞች ግንቦት 7 የሀገር ውስጥ አቀባበል ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የአርበኞች ግንቦት 7 ለዴሞክራሲ እና ለአንድነት ንቅናቄ በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ያሉ አባላቱን እና በጎረቤት ሀገር ኤርትራ የሚገኙ አርበኛ ታጋዮችን በመያዝ በሀገር ውስጥ በመግባት በደንብ በሚያውቀው እና በሚናፍቀው ሠላማዊ እና በዜግነት ላይ በተመሠረተ የፖለቲካ ትግል ለመሳተፍ መወሰኑ ይታወቃል።

በዚሁ መሠረት፣ በንቅናቄው ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሚመሩ ከ250 በላይ የንቅናቄው አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች ጳግሜ 4 ቀን 2010 ዓ·ም ወደ አዲስ አበባ ይገባሉ።

መላው የአዲስ አበባ ነዋሪም ለዴሞክራሲ፣ ለፍትህ፣ ለእኩልነት እና ለሀገር አንድነት ሲሉ ከራሳቸው ጥቅም በላይ የሀገር እና ወገን ጥቅም አስቀድመው ሲታገሉ የነበሩ የህዝብ ልጆችን በዕለቱ በነቂስ በመውጣት እንዲቀበል እና የአቀባበል ሥነ—ሥርዓቱም የተሳካ እንዲሆን የበኩላችሁን እንድታደርጉ እንጠይቃለን።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.