የአማራን ሕዝብ ህልውና ለማዳን የሚታገለው አንድ ኃይል ብቻ ነው። ያም የአማራ ሕዝብ እና ልጁ ፋኖ ብቻ ነው!

ዛሬ በአማራ ስም እየነገዱ፣ የአማራን ደም የፖለቲካ ሸቀጣቸው ያደረጉ፣ ህዝቡን እያጭበረበሩ የሚኖሩ ሚዲያዎች እና ግለሰቦች “ከወያኔ ጋር መስራት፣ ከዘር አጥፊው ኦህዴድ / ብልጽግና ጋር መቆም ብቸኛ አማራጭ ነው” እያሉ ለማስመሰል እየሞከሩ ነው። ይህ ታላቅ ውሸት እና ህዝብን ለማደንዘዝ የተቀነባበረ ሴራ ነው።
እውነታው ግልጽ ነው።

1. ወያኔ ትህነግ ማነው?

ወያኔ የተመሰረተው አማራን በጠላትነት ፈርጆ ነው። ከ30 በላይ ዓመታት በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት የፈፀመ፣ ለፍርድ መቅረብ ያለበት ስብስብ ነው። የአማራ ሕዝብ ዛሬ ለደረሰበት የህልውና መጥፋት፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል መሰረቱን ያስቀመጠው እሱ ነው። አማራን በወንጀል የሚከስ፣ ፀረ አማራውን “ህገ-መንግስት”ተብዬውን ለማስቀጠል የሚታገል ፣ ለመገንጠል ሲል የአማራ አፅመ ርዕስቶች ወልቃይት፣ ጠለምት፣ ራያን ይዞ ለመገንጠል የሚፈልግ ኃይል ነው። ከእንዲህ ካለ ኃይል ጋር ትብብር በሚል የሚቀርብ ማንኛውም ጥሪ የአማራን ማጥፊያ ሴራ አካል ነው። ወያኔ አማራን አያድንም፣ ወያኔ የአማራ ጠላት ነው።

2. ኦህዴድ / ኦነግ / ኢህአዴግ / ብልጽግና ማነው?

እነዚህ ድርጅቶች የተመሰረቱት በአማራ ጥላቻ ላይ ነው። አጀንዳቸው የአማራን ሕዝብ የማጥፋት አጀንዳ ነው። ዛሬም በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ዋነኛ ፈጻሚዎች እነሱ ናቸው። የጎንደር ፣ የጎጃም የወሎን፣ የሸዋን፣ የአዲስ አበባን እና ሌሎች የአማራ አፅመ ርዕስቶች የመንጠቅ፣ የማስወገድ፣ የማጥፋት ዘመቻ እያካሄዱ ያሉት እነሱ ናቸው። ኦህዴድ ብልጽግና እና ኦነግ ኢትዮጵያን አፍርሶ በፍርስራሿ ላይ የኦሮሙማ ፕሮጀክት ለማስፈፀም የዘር ማጥፋት የሚፈፅሙ ወራሪዎች ናቸው። ከእነሱ ጋር መቆም ማለት የአማራን ህልውና አሳልፎ መስጠት ማለት ነው።

3. ብአዴን ማነው?

ከ30 ዓመታት በላይ በአማራ ላይ ለተፈፀሙት የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ዋነኛ ተጠያቂ፣ አማራን ጨቋኝ ብሎ የሚያምን፣ አማራን ለማጥፋት የተመሰረተ አሻንጉሊት ነው። የአማራን ስም ተሸክሞ የአማራን ጠላቶች የሚያገለግል ነው።

ስለዚህ መንገዱ ግልጽ ነው።

አማራን የሚያድነው ከጠላቶቹ ጋር የሚደረግ ትብብር ጥገኝነት አይደለም። አማራን የሚያድነው የህዝብ ለህዝብ ትብብር በሚል ወያኔን እና ፋሺስት አብይ አህመድን ይዞ የመምጣት ሴራ አይደለም።
አማራን የሚያድነው አንድ ኃይል ብቻ ነው – የአማራ ሕዝብ ራሱ፣ እና ከህዝቡ ሆድ የተወለደው፣ ከህዝቡ ጋር ቆሞ ለአማራ ሕዝብ ህልውና የሚታገለው ፋኖ።

አማራ ሆይ! ጠላትህን ለይ፣ ወዳጅህን ለይ። በአማራ ስም እየነገዱብህ ያሉትን ለይተህ እወቅ። ህልውናህ የሚረጋገጠው በራስህ አንድነት እና በፋኖ ትግል ብቻ መሆኑን እወቅ።

@Yebet Sira የቤት ሥራ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.